Sunday, May 10, 2015

“ይሳካላችኋል ቤተክርስትያን” የክርስቶስ ህንጻ የትኛው ነው? ቤቱ ወይስ ምእመናው?

“ይሳካላችኋል ቤተክርስትያን” የክርስቶስ ህንጻ የትኛው ነው? ቤቱ ወይስ ምእመናው?
ysakalchuwal edited
ክፍል አንድ

“የክብር አባት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እርሱን በማወቅ የጥበብንና የመገለጥን መንፈስ እንዲሰጣችሁ እለምናለሁ።ይህም የልባችሁ ዓይኖች ሲበሩ የመጥራቱ ተስፋ ምን እንዲሆን በቅዱሳንም ዘንድ ያለው የርስት ክብር ባለ ጠግነት ምን እንዲሆን ለምናምን ከሁሉ የሚበልጥ የኃይሉ ታላቅነት ምን እንዲሆን ታውቁ ዘንድ ነው፤ ክርስቶስንም ከሙታን ሲያስነሣው ከአለቅነትና ከሥልጣንም ከኃይልም ከጌትነትም ሁሉ በላይና በዚህ ዓለም ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ሊመጣ ባለው ዓለም ደግሞ ከሚጠራው ስም ሁሉ በላይ በሰማያዊ ስፍራ በቀኙ ሲያስቀምጠው በክርስቶስ ባደረገው ሥራ የብርታቱ ጉልበት ይታያል፤ሁሉንም ከእግሩ በታች አስገዛለት ከሁሉ በላይም ራስ እንዲሆን ለቤተ ክርስቲያን ሰጠው።እርስዋም አካሉና ሁሉን በሁሉ የሚሞላ የእርሱ ሙላቱ ናት።”
ኤፌ 1:17_23
“እርሱ ሰላማችን ነውና፤ ሁለቱን ያዋሐደ በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ፤ ይህም ከሁለታቸው አንድን አዲስን ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ፥ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ ሁለታቸውን በአንድ አካል ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቅ ዘንድ ነው። መጥቶም ርቃችሁ ለነበራችሁ ለእናንተ ሰላምን፥ ቀርበው ለነበሩትም ሰላምን የምስራች ብሎ ሰበከ፤ በእርሱ ሥራ ሁላችን በአንድ መንፈስ ወደ አብ መግባት አለንና።እንግዲያስ ከእንግዲህ ወዲህ ከቅዱሳን ጋር ባላገሮችና የእግዚአብሔር ቤተ ሰዎች ናችሁ እንጂ እንግዶችና መጻተኞች አይደላችሁም። በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል፥ የማዕዘኑም ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤በእርሱም ሕንጻ ሁሉ እየተጋጠመ በጌታ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንዲሆን ያድጋል፤በእርሱም እናንተ ደግሞ ለእግዚአብሔር መኖሪያ ለመሆን በመንፈስ አብራችሁ ትሠራላችሁ።”
ኤፌ 2:14_22
83_100707_ds_ministermoneytn.jpg.CROP.original-original
በእነዚሀ የታመኑ የእግዚያብሔር ቃሎች መሰረት የእግዚያብሔር ህንጻ የቱ ነው? የሚታየው የቤቱ አካል ወይንስ ህዝበ ክርስቲያኑ? የእግዚያብሔር ቃል እንደሚያስተምረን እናም ብዙዎች አስተማሪዎች በተለያየ ግዜያቶች እንዳስተማሩት ይህ ከለይ ያሉት የመጽሀፍ ቅዱሳችን የእግዚያብሔር ቃሎች በትክክል የሚናገሩት ስለ ምእመናው የመንፈሳዊ ህይወት ጉዞ ማለትም ያለን መንፈሳዊ ህበረት : ከእግዚያብሔር ጋር ያለን ግኑኝነት : እርስ በእርስ ያለን ህብረት : እርስ በእርስ ያለን ፍቅር : የአምልኮአችን ሁኔታ : የእምነት ጽናታችንና የእምነት እድገታችን የሚታይበት የእምነት መሰራታችን በማይታየው በዋናው የህንጻ መሰረት ላይ ሲሆን የህንጻው ውጨኛው አካል ደግሞ ያመንበትንና የተማርነውን እምነት ሁሉም የሚያየውን የቅድስና ህይወታችንና የየእለት እንቅስቃሴያችን ማሳያ መስታወት ነው የውጨኛው አካላችን:: አለማውያን ቤት ሲሰሩ እንኳ በጣም የሚጠነቀቁትና ብዙ ገንዘብ የሚያወጡት ብዙ ግዜም የሚፈጅባቸው የሚሰሩት ቤት ውጨኛው አካል ላይ ሳይሆን መሰረቱ ላይ ነው መሰረቱ በደንብ ያልተሰራ ቤት አንድ ቀን መፍረሱ አይቀርም ሲፈርስ ደግሞ በህይወትና በንብረት ላይም ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል ከዚያም ባለፈ የስለ ልቦና ቀውሱም ያን ያህል ነው ለቤቱ ባለቤት ይህ በእንዲህ ሆኖ እንዳለ ወደ እኛ የዚህ ዘመን የክርስቶስ ህንጻ ስንመለስ የህንጻው መሀንዲሶች የሆኑት ነብያትና ሐዋርያት ቀየሰው የሰጡዋቸውን ፕላን የአሁኖቹ ግንበኞች ከፈረሱ ጋሪውን በማስቀደም ወይም ጌታ ኢየሱስ ለፈሪሳውያኖች እንዳለው የጽዋውን የወጪቱን ውጨኛውን ክፍል በማጥራት ላይ ይገኛሉ:: በአሁን ግዜ አንዳንድ ቤተክርስቲያን ስትሄዱ የህንጻ ግንባታ በየቦታው ጦፏል ህዝበ ክርስትያኑ ኑሮ አንገሽግሾት እራሱን ሊያረጋጋ እርሙን ቤተክርስቲያን ቢመጣ እነደ አምልኮ በመጀመሪያ የሚቀርብለት ያው ቤተክርስቲያኗ መሬት ገዝታ አሁን ደግሞ የህንጻ ማሰሪያ አንጡ ይባላል:: የት እንደገባ የማይታወቅ ምስኪን ክርስቲያን አሁን አሁን ለገንዘብ በባትሪ ይፈለጋል ምክንያቱም ህንጻ ተጀምሮዋላ የሚፈለገው ገንዘቡ ነው:: እንጂ ክርስቲያኑ አይደለም “የትም ፍጭው ዱቄቱን አምጭው” ይባል የለ ደግሞ በቤቱ ብቻ አያበቃም ዲኮር መደረግ አለበት ይባላል የውስጥ የማስጌጥ ሌላ ስራ ሌላ ልመና ሌላ ሮሮ እንደገና ይህም ያልቅና ዘመናይ መብራት ልክ እንደምሽት ክበብ ይግባ ይባላል እንደገና ሌላ ልመና ጣጣ ይህም እንደምንም ያልፍና የሙዚቃ መሳሪያ : የድምጽ ሲስተም : መብራት እየጠፋ ነው በሚል ጀነሬተር በቃ ይህ የመጨረሻ ነው ይባላል ይሄም እንደምንም ይፈጸማል ምእመናው ኡፈይ አለቀ ብሎ ሳይተነፍስ ቅርንጫፍ አጥቢያ ይባላል ይሄን ግዜ አብዛኛው ሞቅ ባለ የበረከት ቃል

“ይሳካልሀል/ሻል : ይከናወንልሀል/ሻል : ትበለጽጋለህ/ለሽ : በትዳር በልጅ በስራ በትምህርት ትባረካለህ/ለሽ” በሚል ስጋዊ ቅስቀሳ የገባ ስለሆነ ኢየሱስ ይሰጥሀል ብለውኝ ያለኝን ወሰዱብኝ በማለት ያጉረመርማል ከዚያም ከነ አንካቴው ክርስትና ይህ ነው እንዴ ብሎ የለየለት የአለም አለመኛ ይሆናል እከሌ ተመልሶ ባሰበት ይባላል እዛው በተጠመቀበት ቤተክርስትያን ማንም የሚፈልገው የለም እንደውም በተክርስቲያኗ ታወግዘዋለች ነገር ግን እረኞቹ አይናቸው አልበራም ይህ በቤታክርስቲ\ያን ምሬት የጠፋው ክርስትያን የከበረ የደም ዋጋ ስላለበት ጌታ ጠብቆት ወደ ቤቱ ይመልሰዋል እራሳቸውን እረኛ አድርገው የሾሙት እረኞች መንጋውን በትነው አሸሼ አግዳሜውን ያስነኩታል አንዳንዴ እነዚህን የእኛን ፓስተር ይሳካሎች የህዋ ምስክር ቄስ ነው የሚመስሉኝ ምክንያቱም የሚያስተምሩን ከአለም እንድንለይ ሳይሆን አለምን እንድናመልክ እንደ ጆቫ ምስክሮች ምድር ገነት ላይ እያስባሉን በአሁኑ ግዜ ይገኛሉ:: ለነገሩ የመጨረሻ ሰአት ስለሆነ እንዲህ አይነት ነገር እንዲከሰት የእግዚያብሔር ቃል ስለሚናገር
sin_724_482_80
“ስለ ክፉ ምኞት በዓለም ካለው ጥፋት አምልጣችሁ ከመለኮት ባሕርይ ተካፋዮች በተስፋ ቃል እንድትሆኑ፥ በእነዚያ ክብርና በጎነት የተከበረና እጅግ ታላቅ የሆነ ተስፋን ሰጠን። ስለዚህም ምክንያት ትጋትን ሁሉ እያሳያችሁ በእምነታችሁ በጎነትን ጨምሩ፥ በበጎነትም እውቀትን፥ በእውቀትም ራስን መግዛት፥ ራስንም በመግዛት መጽናትን፥ በመጽናትም እግዚአብሔርን መምሰል፥ እግዚአብሔርንም በመምሰል የወንድማማችን መዋደድ፥ በወንድማማችም መዋደድ ፍቅርን ጨምሩ።እነዚህ ነገሮች ለእናንተ ሆነው ቢበዙ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት ሥራ ፈቶችና ፍሬ ቢሶች እንዳትሆኑ ያደርጉአችኋልና፤ እነዚህ ነገሮች የሌሉት ዕውር ነውና፥ በቅርብም ያለውን ብቻ ያያል፥ የቀደመውንም ኃጢአቱን መንጻት ረስቶአል።”
ቃሉን ለሚያቅ አይደንቅም ነገር ግን በጌታ ቃል ቅንአት በድፍረት እንናገራለን እንገስጻለን ምክንያቱም ማንም ዳግም ውልደት ባገኘ ክርስትያን ላይ የጌታ ፍርድ እንዲፈረድ ስለማንፈልግ ጌታ ግን ሊፈርድ በደጅ ነው ያለው:: እባካችሁ ታላቁ መጸሐፋችን ስለናንተ ስጋውያን አለመኛ ራሳቸውን በራሳቸው ስለሾሙ እረኞች እንዲህ ይላል::
“የእስራኤልም አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና። በመካከላችሁ ያሉት ነቢያቶቻችሁና ምዋርተኞቻችሁ አያታልሉአችሁ፥ እናንተም የምታልሙትን ሕልም አትስሙ። በስሜ ሐሰተኛ ትንቢትን ይናገሩላችኋልና፤ እኔም አልላክኋቸውም። እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና። ሰባው ዓመት በባቢሎን በተፈጸመ ጊዜ እጐበኛችኋለሁ፥ ወደዚህም ስፍራ እመልሳችሁ ዘንድ መልካሚቱን ቃሌን እፈጽምላችኋለሁ። ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም። እናንተም ትጠሩኛለችሁ፥ ሄዳችሁም ወደ እኔ ትጸልያላችሁ፥ እኔም እሰማችኋለሁ።እናንተ ትሹኛላችሁ፥ በፍጹም ልባችሁም ከሻችሁኝ ታገኙኛላችሁ።”
ኤር 29:8_13”
snake
“ብዙ እረኞች የወይኑን ቦታዬን አጥፍተዋል፥ እድል ፈንታዬንም ረግጠዋል፤ የአምሮቴን እድል ፈንታ ምድረ በዳ አድርገውታል።”
ኤር 12:1o
“ይህን ከዚህ ውሰዱ፤ የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉት አላቸው።”
ጌታ ኢየሱስ
“ዳሩ ግን ባለ ጠጎች ሊሆኑ የሚፈልጉ በጥፋትና በመፍረስ ሰዎችን በሚያሰጥምና በሚያሰንፍ በሚጎዳም በብዙ ምኞትና በፈተና በወጥመድም ይወድቃሉ።”
1 ጢሞ 6:10
1aalove of money 971164_501034516638158_892926636_n
“ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነውና፥ አንዳንዶች ይህን ሲመኙ፥ ከሃይማኖት ተሳስተው በብዙ ሥቃይ ራሳቸውን ወጉ።”
1 ጢሞ 6:11
feature_mormon29__01__630x420
“እስከ መቼ በሰው ላይ ትቆማላችሁ? እናንተ ሁላችሁ እንዳዘነበለ ግድግዳ እንደ ፈረሰም ቅጥር ትገድላላችሁ።”
መዝ 61:3
“ነገር ግን ክብሬን ይሽሩ ዘንድ መከሩ፥ ሐሰትንም ይወድዳሉ፤ በአፋቸው ይባርካሉ፥ በልባቸውም ይረግማሉ።”

No comments:

Post a Comment