Sunday, October 2, 2016

የ“ዲያብሎስ” አዲሱ የአለም መንግስት ስርአት ( New world order) በኢትዮጵያ እኛ ሁላችን የዚህች ፕላኔት የመጨረሻ ዘመን ነዋሪዎች ነን!

አዲሱ የአለም መንግስት ስርአት ( New world order ) ለማግኘት፦ ከሰዎች አይምሮ ውስጥ ግለኝነትን፣ለቤተሰብ ባህል ታማኝ መሆንን፣የሀገር ፍቅር ስሜትን እና የሐይማኖት ስርአቶችን በሙሉ ማስወገድ እጅግ አስፈላጊ እና ዋናው ነገር ነው።” ብሮክ ቻይስሎም የቀድሞው የተባበሩት መንግስታት የጤና ድርጅት “WHO”  ዋና ዳይሬክተር
ክፉውን መልካም መልካሙን ክፉ ለሚሉ፥ ጨለማውን ብርሃን ብርሃኑንም ጨለማ ለሚያደርጉ፥ ጣፋጩን መራራመራራውንም ጣፋጭ ለሚያደርጉ ወዮላቸው!  በዓይናቸው ጥበበኞች በነፍሳቸውም አስተዋዮች ለሆኑ ወዮላቸው! የወይንጠጅ ለመጠጣት ኃያላን የሚያሰክረውንም ለማደባለቅ ጨካኞች ለሆኑ፤ በደለኛውን ስለ ጉቦ ጻድቅ ለሚያደርጉ፥ የጻድቁንምጽድቅ ለሚያስወግዱበት ወዮላቸው!” ኢሳ 5:20_23

(ፍቃዱ ጃዝ)

መስከረም 10,2009 ዓ.ም.
ክፍል ሁለት
ዛሬ በአለማችን ላይ አለማችን የሚያስተዳድሩት “ኢሊቶች” ( የዲያብሎስ ልጆች ) በአለማችን ላይ በፓለቲካዊ፣በኢኮኖሚያዊ እና በማህበራዊ አዲስ አይነት የመንግስት አሰራር እና አደረጃጀት ተግባራዊ አድርገዋል። ይህ አዲሱ የአለም የመንግስት አደረጃጀት እና አወቃቀር አዲሱ የአለም መንግስት ስርአት ( New world order ) ወይም አዲሱ የአለም መንግስት ( New world Government ) በመባል የሚታወቅ ሲሆን በአገራችን ኢትዮጵያን ጨምሮ በአለም ሁሉ ላይ እየተፈጠሩ ያሉትን ሰውሰራሽ የፓለቲካዊ፣የኢኮኖሚያዊ እና የማህበራዊ አሰቃቂ ስቆቃዊ ቀውሶች የዚህ ሊመሰረት ላለው ለአዲሱ የአለም መንግስት ስርአት ( New world order ) ዋና የፓለቲካ ትርፍ ግብአት መሆናቸውን ስንቶቻችን ነን በጥልቀት የምናውቀው? በአገራችን በኢትዮጵያ የበትረስልጣን ዙፋኑን በኀይል የተቆናጠጠው ገዥው መንግስት በየግዜው የሚያረቃቸው እና የሚያጸድቃቸው አፋኝ እና ጨቋኝ ህጎች የዚሁ አዲስ የሚመሰረተው የአለም መንግስት ህግ እንደሆነ ስንቶቻችን ነን የምናውቀው? ከአሁን ቡኋላ ይበልጥ ከምንግዜውም በላይ አፋኝ እና ጨቋኝ የኮሚኒስት ወታደራዊ ስርአት አገራችንን ኢትዮጵያ ጨምሮ በአለማችን ላይ በቅርቡ ሊነግስ እንደሆነ ስንቶቻችን ነን የምናውቀው? ከአሁን ቡኋላ በአለማችን ላይ ሰላም፣ፍቅር፣አንድነት፣ነጻነት እና እኩልነት የማይታሰብበት እና የማይገኝበት እንዲሁም በተቃራኒው የታላቅ መከራ ዘመን እንደሚሆን ስንቶቻችን ነን በጥልቀት የምናውቀው? አዲሱ የአለም መንግስት ስርአት ( New world order ) በአለማችን ላይ ከአሁን ቡኋላ በአለማችን ላይ ምን ሊሰራ አቅዷል? በአለም ላይ ያሉ ታዋቂ ሰዎች ስለ አዲሱ የአለም መንግስት ስርአት ( New world order ) ምን ይላሉ? መጽሐፍ ቅዱስ ስለ አዲሱ የአለም መንግስት ስርአት ( New world order ) ምን ይለናል? እኛ ሁላችን የመጨረሻው ዘመን ነዋሪዎች እንደሆንን ስንቶቻችን በጥልቀት ተረድተነዋል? የእነዚህን እና ሌሎችንም አንኳር የሁላችንም የውስጥ ጥያቄዎቻችንን በጥልቀት እንዳስሳለን በጥሞናና በትእግስት ይህንን መልእክት ያንብቡ ይጠቀሙበታል እንጂ አይጎዱበም። ያተርፋሉ እንጂ አይከስሩበትም ስለሆነም በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ በራዕይ መጽሐፍ ውስጥ በመጨረሻው ዘመን በክፉ ስራዋ ስለምትገለጠው በሴት ተመስላ ስለቀረበችው የግፍ ከተማ መነሻ በማድረግ በጥልቀት ወደ ውስጥ እንግባ።
ሰባቱንም ጽዋዎች ከያዙ ከሰባቱ መላእክት አንዱ መጥቶ። ና በብዙም ውኃዎች ላይ የተቀመጠችውን የታላቂቱን ጋለሞታፍርድ አሳይሃለሁ፤የምድርም ነገሥታት ከእርስዋ ጋር ሴሰኑ በምድርም የሚኖሩ ከዝሙትዋ ወይን ጠጅ ሰከሩ ብሎተናገረኝ።በመንፈስም ወደ በረሀ ወሰደኝ፤ የስድብም ስሞች በሞሉበት፥ ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶችም ባሉበት በቀይ አውሬላይ አንዲት ሴት ተቀምጣ አየሁ። ሴቲቱም በቀይና በሐምራዊ ልብስ ተጐናጽፋ በወርቅና በከበሩ ድንጋዮች በዕንቈችምተሸልማ ነበር፥ በእጅዋም የሚያስጸይፍ ነገር የዝሙትዋም ርኵሰት የሞላባትን የወርቅ ጽዋ ያዘች፤በግምባርዋም ምስጢር የሆነስም። ታላቂቱ ባቢሎን፥ የጋለሞታዎችና የምድር ርኵሰት እናት ተብሎ ተጻፈ።ሴቲቱም በቅዱሳን ደምና በኢየሱስ ምስክሮችደም ሰክራ አየኋት። ባየኋትም ጊዜ እጅግ ታላቅ ድንቅ አደነቅሁ። መልአኩም አለኝ። የምትደነቅ ስለ ምንድር ነው? የሴቲቱንምስጢርና የሚሸከማትን፥ ሰባት ራሶችና አስር ቀንዶች ያሉትን የአውሬውን ምስጢር እኔ እነግርሃለሁ። ያየኸው አውሬአስቀድሞ ነበረ፥ አሁንም የለም፥ ከጥልቁም ይወጣ ዘንድ አለው፥ ወደ ጥፋትም ይሄዳል፤ ስሞቻቸውም ከዓለም ፍጥረትጀምሮ በሕይወት መጽሐፍ ያልተጻፉ በምድር የሚኖሩ አውሬው አስቀድሞ እንደነበረ አሁንም እንደሌለ፥ ነገር ግን እንዳለሲያዩ ያደንቃሉ። ጥበብ ያለው አእምሮ በዚህ ነው። ሰባቱ ራሶች ሴቲቱ የተቀመጠችባቸው ሰባት ተራራዎች ናቸው፥ሰባትነገሥታት ደግሞ ናቸው፤ አምስቱ ወድቀዋል አንዱም አለ፥ የቀረውም ገና አልመጣም፤ ሲመጣም፥ ጥቂት ጊዜ ሊቆይይገባዋል። የነበረውና የሌለውም አውሬ ራሱ ደግሞ ስምንተኛው ነው ከሰባቱም አንዱ ነው፥ ወደ ጥፋትምይሄዳል።ያየሃቸውም አስሩ ቀንዶች ገና መንግሥትን ያልተቀበሉ አስር ነገሥታት ናቸው፥ ዳሩ ግን ከአውሬው ጋር ለአንድሰዓት እንደ ነገሥታት ሥልጣንን ይቀበላሉ። እነዚህ አንድ አሳብ አላቸው፥ ኃይላቸውንና ሥልጣናቸውንም ለአውሬውይሰጣሉ።እነዚህ በጉን ይወጋሉ፤ በጉም የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ስለ ሆነ እነርሱን ድል ይነሣል፥ ከእርሱም ጋር ያሉየተጠሩና የተመረጡ የታመኑም ደግሞ ድል ይነሣሉ። አለኝም። ጋለሞታይቱ የተቀመጠችባቸው ያየሃቸው ውኃዎች፥ ወገኖችናብዙ ሰዎች አሕዛብም ቋንቋዎችም ናቸው። ያየኃቸውም አስር ቀንዶችና አውሬው ጋለሞታይቱን ይጣላሉ፤ ባዶዋንናራቁትዋንም ያደርጓታል፥ ሥጋዋንም ይበላሉ፥ በእሳትም ያቃጥሉአታል። እግዚአብሔር አሳቡን እንዲያደርጉ አንድንም አሳብእንዲያደርጉ የእግዚአብሔርም ቃል እስኪፈጸም ድረስ መንግሥታቸውን ለአውሬው እንዲሰጡ በልባቸው አግብቶአልና።ያየሃትም ሴት በምድር ነገሥታት ላይ የምትነግሥ ታላቂቱ ከተማ ናት።” ራዕ 17
ዛሬ ዛሬ መጽሐፍ ቅዱስ በመጨረሻዋ ዘመን በክፋቷ ታላቅነት ተወዳዳሪ እና አቻ የማይገኝላት እና በጸያፍ የግፍ እርኩሰቷ የምትታወቀው እና የአለምን ነገስታት ወክላ በክፉ የምትገለጠው እንዲሁም የብዙዎቹ አንጋፋ የአለማችን ሰባኪዎች እና የመጽሐፍ ቅዱስ አጥኚዎች እንዲሁም ታላላቅ የእምነት አባቶች አዎ እሷ ነች ብለው የሚመሰክሩባት ታላቋ ጋለሞታ የምድር እርኩሰት የሆነችው “አሜርካ” እና ሸሪኮቿ “አውሮፓውያን” ከክፉ ጨካኝ አውሬ እጅግ የሚከፉትን አደገኛ የሽብር ተቋማቶችን እንደ ( አልቃይዳ፣አይሲስ፣አልኑስራ፣አልሸባብ እንዲሁም ሌሎችም ) የመሳሰሉትን አክራሪ የሽብር  ድርጅቶችን በይፋ እና በግልጽ ለክፉ ድርጊት ማስፈጸሚያቸው እንዲሆን አድርገው በረቀቀ መንገድ በመመስረት ባጠቃላይ ሰላማዊ የአለም ህዝቦችን ጨምሮ እንዲሁም  ምንም ነፍስ በማያውቁ ጨቅላ ህጻናቶችን ፣ወጣቶች፣እናቶች፣አባቶች እንዲሁም በእድሜ የገፉ አረጋውያን ከቀዬአቸው እየወሰዱ ከእንሰሳ በታች በሆነ ስብእና እጅግ ዘግናኝ ድርጊት የሰው ልጅ አይምሮ ያደርገዋል በማይባል አጸያፊ  የክፋት እርኩሰት ሴራ ስራ በጠራራ ፀሐይ ቄራ ከሚታረድ እንሰሳ በታች በሆነ ስብእና አሳርደው እያስገደሉ ያሉ ሲሆን እንዲሁም በተጨማሪ ታላቋ ጋለሞታ የምድር እርኩሰት የሆናችው “አሜርካ” እና ሸሪኮቿ “አውሮፓውያኖቹ” ከክፉ ጨካኝ አውሬ እጅግ የሚከፉትን እና የነሱን ሰይጣናዊ የክፋት ድርጊት የሚያስፈጽሙላቸውን አሸባሪ እና ፈላጭ ቆራጭ አምባገነን የአገር መሪዎችን በሚፈልጉት የአለም አገሮች ሁሉ ላይ በመሾም ለፈጠሩዋቸው አሸባሪ ቡድኖች እና ስልጣን ላይ ላስቀመጡዋቸው ከጨካኝም አውሬ እጅግ የሚከፉትን አምባገነን የህዝብ ጠላት ግፈኛ መሪዎች ታላቅ ፓለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ እገዛ በማድረግ በግፍና በጭካኔ የሰላማዊውን ህዝብ ደም በጠራራ ፀሐይ ይጠጡታል። ጨካኙ የናዚ መሪ አዶልፍ ሂትለር አስጸያፊ እና ዘግናኝ የሽብር ድርጊት ለፓለቲካ አላማ ዋና ቁልፍ ነገር እንደሆነ እንዲህ በማለት የአለም መሪዎች እንዲሰሩበት ይመክራል። ሽብር እጅግበጣም ጥሩ የፓለቲካ መሳሪያ ነው። ሰዎችን ከድንገተኛ አሰቃቂ ሞት በላይ የሚያስፈራቸው ምንም ነገር የለም ”
ዛሬ ዛሬ የአለም መንግስታት ለፓለቲካ ጥቅም ፍጆታቸው ያቋቋሟቸው የዲሞክራሲ እና የሰብአዊ መብቶች እንዲሁም የ“የመገናኛ  ብዙኀን አውታሮች በግለሰብ ስም ሆነ በኮርፓሬሽን የተቋቋሙትን መገናኛ ብዙኀን አውታሮችንም ይጨምራል” እንዲሁም በተጨማሪ የሐይማኖት ተቋማቶች በሙሉው ማለት ይቻላል የሰይጣናዊ ክፋት ስራ መሸፈኛ ካባ እና ጭምብል መሆናቸውን ባደባባይ በድርጊታቸው ራሳቸው መስክረው በግልጽ አሳይተውናል።
ዛሬ በሴሪያ፣በኢራቅ እንዲሁም በሊቢያ ሰላማዊ ህዝብ እና ሉአላዊ የሰው አገር ላይ ታላቋ ጋለሞታ የምድር እርኩሰት የሆናችው “አሜርካ” እና ሸሪኮቿ “አውሮፓውያኖቹ” የሚሰሩት ጸያፍ ዘግናኝ የግፍ ድርጊት መጠኑ ይብዛም ወይም ይነስ በአገራችን በኢትዮጵያ ላይም ድርጊቱን በመድገም ከመቼውም ግዜ በከፋ መልኩ እነሱ በሾሙት የስልጣን አገዛዝ አማካኝነት ምስኪኑ የአገራችን ህዝብ በየቀኑ በግፍ በጠራራ ፀሐይ እየተገደለ ፣ እየታሰረ እና እየተሰደደ አሰቃቂ የስቃይ የባርነት ህይወት በመኖር ላይ ይገኛል። ስለሆነም አገራችን ኢትዮጵያን ጨምሮ በአለም ላይ አዲስ ሰይጣናዊ መንግስት የግፍ አገዛዝ በግልጽ ለመመስረት ታላቋ ጋለሞታ የምድር እርኩሰት የሆናችው “አሜርካ” እና ሸሪኮቿ “አውሮፓውያኖቹ” ወደ መጨረሻው ጫፍ በፍጥነት ገስግሰው ደርሰዋል። ስለሆነም ሁላችንም ማወቅ ያለብን አንድ ነገር አለ ወደድንም ጠላንም ተቀበልንም አልተቀበልንም ሊገለጥ ያለውን አዲሱን የመጨረሻውን ዘመን የአለም መንግስት ስርአት ( New world order/ Illuminati ) ባህሪዎቹን እንዲሁም ታላላቆቹ አንጋፋ ቀደምት የአለም መሪዎች፣አለምን በኢኮኖሚያቸው የሚያስተዳድሩ የአለማችን የሀብት ቁንጮ ታላላቅ ግለሰቦች፣ ቀደምት አንጋፋ ፈላስፋዎች እና አንጋፋ ፓለቲከኞች፣ የሐይማኖት ተቋማቶች እንዲሁም በተጨማሪ ስላለፈው እና ስለሚመጣው እንዲሁም ስለመጨረሻው እና ስለሁሉም ነገር የሚናገረው ታላቁ መጽሐፍ የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ ስለዚህ እጅግ በክፋት ስለሚገለጠው የመጨረሻው የአለም መንግስት ስርአት ሁሉም የሚሉትን በየተራ የቃል ባህሪያቸውን ማወቅ ያለብን ሲሆን እንዲሁም በተጨማሪ የመፍትሄ ሀሳቦችን እና ድርጊቶችንም ጭምር በግላችንም ሆነ በጋራ ሀሳብ መቀያየር እንዳለብን በዚሁ አጋጣሚ እያሳሰብኩ የግለሰቦቹን እና የድርጅቶቹን የቃል ኩነቶች እና ታሪካዊ ያአፈጣጠራቸውን ሂደት እንደሚከተለው በቅደም ተከተል ተብራርቶ አቅርቤዋለሁ።
ኢሉሚናቲ ( Illuminati )
tumblr_inline_mo6y26nrDP1qz4rgp
“ኢሉሚናቲ ( Illuminati )” እነርሱ እንደሚሉት የቃሉ ትርጉም በላቲን “የተሰወረውን ጥበብ ፈልጎ ማግኘት” ማለት ሲሆን የአለማችን በነገሮች ሁሉ ቁንጮዎች ስብስብ “ኢሊት” ማለትም አንጋፋ እና ታዋቂ የአለማችን ነገስታቶች እና የሀገር መሪዎች፣ፓለቲከኞች፣በኢኮኖሚ፣በትምህርት፣በሐይማኖት እንዲሁም በተለያዩ የሙያ ዘርፍ ላይ አለማችንን የሚመሩ ጥቂት ግለሰቦች የዚህ  ምስጢራዊ ስብስብ ማህበር አባል ሲሆኑ እንዲሁም የማህበሩም ዋና መስራች ጀርመናዊው አዳምስ ዊሻፕት በመባል እንደሚታወቅ ኢንሳይክሎፒዲያ የታሪክ መረጃ በግልጽ ይተነትንልናል።
እንደ እውነቱ ከሆነ “ኢሉሚናቲ ( Illuminati )” እነርሱ እንደሚሉት “የተሰወረውን ጥበብ ፈልጎ ማግኘት” ማለት ሳይሆን በተቃራኒው በተሰወረ እጅግ በረቀቀ በክፋት ሴራዊ ድርጊት የታጀበ መናፍስታዊ ሀይሎች እየተመራ እውነተኛውን እና ትክክለኛውን የተፈጥሮውን ህግ በመቀየር በአለማችን ላይ በሚኖሩ ሰላማዊ ህዝቦች ላይ እንዲሁም እየኖርንበት ባለው ተፈጥሮአዊ ግኡዝ መኖሪያ ፕላኔታችን ላይ አሰቃቂ የግፍ የእርኩሰት እና ታላላቅ ጥፋት በመፈፀም የእግዚያብሔርን የተፈጥሮ ስራ ማበላሸት እና ማጥፋት ሲሆን በመጨረሻም  በ“ኢሉሚናቲ ( Illuminati )” በሚስጥር ማህበሩ አባላት በተመሰረተ አዲሱ የአለም መንግስት ስርአት ( New world order ) አማካኝነት በእግዚያብሔር መንግስት ላይ ግልጽ የመጨረሻ የአመጻ ጦርነት ማወጅ ነው። እንደ እውነቱ ከሆነ እነሆ የአመጻው ጦርነት ከዛሬ ከ2016 አመት በፊት ተጀምሮ እንሆ አሁን በእኛ ዘመን የጦርነቱ መቋጫ ጫፉ አፋፉ እና የፍሙ ወላፈን ላይ ደርሰናል። እንደ “ኢሉሚናቲ ( Illuminati )” የሚስጥር ማህበር መስራች አዳም ውሻፕት አገላለጽ “ኢሉሚናቲ ( Illuminati )” የተመሰረተበት ዋና አላማ ነጥቦቹን በሚስጥር ማህበሩ ማንፌስቶ እንዲህ በማለት ያብራራዋል፦
“ኢሉሚናቲ ( Illuminati )” የተፈለገው አዲሱ የአለም መንግስት ስርአት ( New world order ) መንግስትን ለመመስረት ሲሆን ይህ እንዲመሰረት የምንፈልገው አዲሱ የአለም ስርአት መንግስት ከመመስረቱ በፊት ግን ቀዳሚ የግድ መደረግ ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች ያሉ ሲሆን እነሱም ሰባቱ የ“ኢሉሚናቲ ( Illuminati )” መርሆች በመባል ይታወቃሉ። እነሱም፦
  1. አሁን እየተሰራባቸው ያሉትን የአለም የመንግስት የመዋቅር አሰራሮች እና አደረጃጀቶች በሙሉ የትኛውንም አስፈላጊውን ኋይል ተጠቅሞ ማፍረስ እና ማጥፋት። በተጨማሪም የእያንዳንዱን ግለሰብ ሀብት እና ንብረት እንዲሁም የየእለት የምግብ ፍጆታው ምግቡን ሁሉ ሳይቀር በተለያየ መንገድ መቆጣጠር። “የሀገርህን የነዳጅ ዘይት በቁጥጥርህ ስር ካደረክ ህዝቡን ትገዛዋለህ። ደግሞም የሀገሪቱን ምግብ በቁጥጥር ስር ካዋልክ እያንዳንዱን ግለሰብ ትገዛዋለህ” ሄነሪ ኪሲንጀር
  2. የግል ማናቸውንም ሀብት ማፍረስ እና ማጥፋት በተመሳሳዩ በግለሰብ ስም በመንግስት ባለቤትነት የሚተዳደሩ የግል ታላላቅ የንግድ ኮርፓሬሽኖች መፍጠር።
  3. በማናቸውም ሁናቴ የሀብት ውርስ እንዳይኖር የውርስ ህግ እና ስርአትን ማጥፋት። እዚህ ላይ ህይወትን መጠበቂያ ነፍጥ ጠመንጃንም ሁሉ ያካትታል። “ህዝብህ ላይ ለመንገስ ከፈለክ በመጀመሪያ ህዝቡን ትጥቁን (ነፍጡን) ማስፈታት አለብህ” አዶልፍ ሂትለር
  4. የአገርን የመውደድ እና የአንድነት ስሜት በተለያየ መንገድ እና ሁኔታ ከእያንዳንዱ ሰው ላይ ማጥፋት።
  5. ቤተሰብ የሚባለውን የተፈጥሮ ፍቅር ስብስብ ማጥፋት።
  6. ሀይማኖቶችን በሙሉ ማጥፋት። በተመሳሳዩ አዲሱ የአለም መንግስት ስርአት ሀይማኖትን ( New world Religion) አንድ የአለም ሀይማኖትን መፍጠር።
  7. በስተመጨረሻም አዲሱ የአለም መንግስት ስርአት ( New world order ) ይመሰረታል።
በዛሬ ግዜ አብዛኛው የአለም መንግስታት መሪዎች ኢትዮጵያን ጨምሮ የዚህ የጨለማ መናፍስታዊ የክፋት ሀያላን በሰለጠኑበት የዲያብሎስ  መንግስት አባላት ሲሆኑ አብዛኞቹ የአባልነት ልዩ መታወቂያነታቸውም በግፍ እና በጭቆና በሚመሩት ሉአላዊ አገር ሰንደቅ ባንድራ ላይ የዲያብሎስ መንግስት የመንፈሱ ዋና አርማ የሆነውን እና በምድረ አሜርካ በዲትሮይት ግዛት እንዲሁም በሌሎቹም ግዛቶች በግልጽ በሰይጣን ቤተክርስትያን ሀውልቱ ቆሞ የሚመለከው የ“ባፎሚት”(የፊየልን አናት ምስል የሚወክለው ባለአምስት ነጥብ ፔንቴግራም ኮከብ አርማ ) እንደ ኢትዮጵያ ባሉ የዲያብሎስ መንግስት ተወካይ በነገሱበት አገር ባንድራ ሰንደቅ ላይ የአምላካቸውን አርማ በትልቁ በጉልህ እንዲታይ አድርገው አትመውበት ለሁሉም እንዲታይ አድርገው እና ሁሉም እንዲቀበለው በተገኘው አጋጣሚ ያውለበልቡታል። የሰው ልጅ በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ ከእርሱም ጋር ቅዱሳን መላእክቱሁሉ፥ በዚያን ጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል፤አሕዛብም ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ፤ እረኛም በጎቹን ከፍየሎች እንደሚለይ እርስበርሳቸው ይለያቸዋል፥በጎችን በቀኙ ፍየሎችንም በግራው ያቆማቸዋል።” ማቴ 25:31-33 በተጨማሪም ይህ የባፎሚት አርማ ያለበትን ባንድራ ምንነት እያወቁ በሁሉም በአገራችን በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ የሁሉም የክርስትያን ቤተክርስትያኖች ውስጥ እንዲሁም በየመስኪዶች ጭምር በግልጽ ያለምንም ይሉኝታ እና እፍረት የቆመ ሲሆን እንደነዚህ ካሉት ነገሮች እንኳ ኢየሱስ ክርስቶስም በመጨረሻው ዘመን ስለሚገለጡት የበግ ልምድ ካላቸው ተኩላ የሀሰት አስተማሪዎችና ነቢያቶች እንድንጠነቀቅ አበክሮ እንዲህ በማለት አስጠንቅቆናል። የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውሥጣቸው ግን ነጣቂዎችተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ። ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ። ከእሾህ ወይን ከኩርንችትስ በለስይለቀማልንእንዲሁ መልካም ዛፍ ሁሉ መልካም ፍሬ ያደርጋል፥ ክፉም ዛፍ ክፉ ፍሬ ያደርጋል። መልካም ዛፍ ክፉ ፍሬማፍራት፥ ወይም ክፉ ዛፍ መልካም ፍሬ ማፍራት አይቻለውም።” ማቴ 7:15-18 ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም በመጨረሻ ዘመን በአለም ሁሉ ላይ ስለሚገለጡት የሀሰት ነቢያቶች እና አስተማሪዎች እንድንጠነቀቅ እንዲህ በማለት እርሱም እንደ ጌታ ኢየሱስ አበክሮ አስጠንቅቆናል። ኑሮዬ ይበቃኛል ለሚለው ግን እግዚአብሔርን መምሰል እጅግ ማትረፊያ ነው፤ ወደ ዓለምምንም እንኳ አላመጣንምና፥ አንዳችንም ልንወስድ አይቻለንም፤ ምግብና ልብስ ከኖረን ግን፥ እርሱ ይበቃናል። ዳሩ ግን ባለጠጎች ሊሆኑ የሚፈልጉ በጥፋትና በመፍረስ ሰዎችን በሚያሰጥምና በሚያሰንፍ በሚጎዳም በብዙ ምኞትና በፈተናበወጥመድም ይወድቃሉ። ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነውና፥ አንዳንዶች ይህን ሲመኙ፥ ከሃይማኖት ተሳስተውበብዙ ሥቃይ ራሳቸውን ወጉ። አንተ ግን፥ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፥ ከዚህ ሽሽ፤ ጽድቅንና እግዚአብሔርን መምሰልእምነትንም ፍቅርንም መጽናትንም የዋህነትንም ተከታተል።”1ጢሞ 6:6-11 “እግዚአብሔርን እንዲያውቁ በግልጥይናገራሉ፥ ዳሩ ግን የሚያስጸይፉና የማይታዘዙ ለበጎ ሥራም ሁሉ የማይበቁ ስለ ሆኑ፥ በሥራቸው ይክዱታል።” ቲቶ 1:16
አዲሱ የአለም መንግስት ስርአት (New world order/ Illuminati)
የመጨረሻው ዘመን የሚነሳውን አዲስ መንግስት ስርአት አነሳሱን እና ባህሪውን በማስመልከት በመጽሐፍ ቅዱስ የትንቢት መጽሐፎች በብዙ ክፍሎች ውስጥ የተገለጸ ሲሆን ስለ ነገስታት እና መንግስታት ጅማሬያቸውን እና ፍጻሜያቸውን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ በነብዩ ዳንኤል የተጻፈውን የትንቢት ፍጻሜ ራዕይ እየሱስ ክርስቶስ እንኳ ስለዘመኑ ፍጻሜ የነብዩ ዳንኤልን የትንቢት መጽሐፍ ጠቅሶ እንድናነብና እንድናስተውል እንዲህ በማለት አስጠንቅቆናል። እንግዲህ በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋትንርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ፥ አንባቢው ያስተውል፥በዚያን ጊዜ በይሁዳ ያሉት ወደ ተራራዎች ይሽሹ፥በሰገነትምያለ በቤቱ ያለውን ሊወስድ አይውረድ፥በእርሻም ያለ ልብሱን ይወስድ ዘንድ ወደ ኋላው አይመለስ። በዚያችም ወራትለርጉዞችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው። ነገር ግን ሽሽታችሁ በክረምት ወይም በሰንበት እንዳይሆን ጸልዩ፤በዚያን ጊዜ ከዓለምመጀመሪያ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ያልሆነ እንግዲህም ከቶ የማይሆን ታላቅ መከራ ይሆናልና። ማቴ 24:15-21
አንተ፥ ንጉሥ ሆይ፥ ታላቅ ምስል አየህ፤ ይህም ምስል ታላቅና ብልጭልጭታው የበዛ ነበረ፥ በፊትህም ቆሞ ነበር፤ መልኩምግሩም ነበረ። የዚህም ምስል ራስ ጥሩ ወርቅ፥ ደረቱና ክንዶቹም ብር፥ ሆዱና ወገቡም ናስ፥ጭኖቹም ብረት፥ እግሮቹም እኩሉብረት እኩሉም ሸክላ ነበረ። እጅም ሳይነካው ድንጋይ ከተራራው ተፈንቅሎ ከብረትና ከሸክላ የሆነውን የምስሉን እግሮችሲመታና ሲፈጭ አየህ። የዚያን ጊዜም ብረቱና ሸክላው፥ ናሱና ብሩ ወርቁም በአንድነት ተፈጨ፥ በመከርም ጊዜ በአውድማላይ እንዳለ እብቅ ሆነ፤ ነፋስም ወሰደው፥ ቦታውም አልታወቀም፤ ምስሉንም የመታ ድንጋይ ታላቅ ተራራ ሆነ ምድርንምፈጽሞ ሞላ ሕልሙ ይህ ነው፤ አሁንም ፍቺውን በንጉሡ ፊት እንናገራለን። አንተ፥ ንጉሥ ሆይ፥ የሰማይ አምላክመንግሥትንና ኃይልን፥ ብርታትንና ክብርን የሰጠህ የነገሥታት ንጉሥ አንተ ነህ። በሚቀመጡበትም ስፍራ ሁሉ የሰውልጆችንና የምድር አራዊትን የሰማይ ወፎችንም በእጅህ አሳልፎ ሰጥቶሃል፥ ለሁሉም ገዥ አድርጎሃል፤ አንተ የወርቁ ራስ ነህ።ከአንተም በኋላ ከአንተ የሚያንስ ሌላ መንግሥት ይነሣል፤ ከዚያም በኋላ በምድር ሁሉ ላይ የሚገዛ ሌላ ሦስተኛ የናስመንግሥት ይነሣል። አራተኛውም መንግሥት ሁሉን እንደሚቀጠቅጥና እንደሚያደቅቅ ብረት ይበረታል፤ እነዚህንም ሁሉእንደሚፈጭ ብረት ይቀጠቅጣል ይፈጭማል። እግሮቹና ጣቶቹም እኩሉ ሸክላ እኩሉም ብረት ሆኖ እንዳየህ፥ እንዲሁየተከፋፈለ መንግሥት ይሆናል፤ ብረቱም ከሸክላው ጋር ተደባልቆ እንዳየሁ፥ የብረት ብርታት ለእርሱ ይሆናል። የእግሮቹምጣቶች እኩሉ ብረት እኩሉም ሸክላ እንደ ነበሩ፥ እንዲሁ መንግሥቱ እኩሉ ብርቱ እኩሉ ደካማ ይሆናል። ብረቱም ከሸክላውጋር ተደባልቆ እንዳየህ፥ እንዲሁ ከሰው ዘር ጋር ይደባለቃሉ፤ ነገር ግን ብረት ከሸክላ ጋር እንደማይጣበቅ፥ እንዲሁ እርስበርሳቸው አይጣበቁም። በእነዚያም ነገሥታት ዘመን የሰማይ አምላክ ለዘላለም የማይፈርስ መንግሥት ያስነሣል፤ ለሌላሕዝብም የማይሰጥ መንግሥት ይሆናል፤ እነዚያንም መንግሥታት ሁሉ ትፈጫቸዋለች ታጠፋቸውማለች፥ ለዘላለምምትቆማለች።ድንጋዩም እጅ ሳይነካው ከተራራ ተፈንቅሎ ብረቱንና ናሱን ሸክላውንና ብሩን ወርቁንም ሲፈጨው እንዳየህ፥እንዲሁ ከዚህ በኋላ የሚሆነውን ታላቁ አምላክ ለንጉሡ አስታውቆታል፤ ሕልሙም እውነተኛ ፍቺውም የታመነ ነው።” ዳን 2:31_45
እንደ መጽሐፍ ቅዱስ እውነተኛ መረጃ መሰረት አዲሱ የአለም መንግስት ስርአት ( New world order/ Illuminati ) የተመሰረተው ከኖህ የጥፋት ውሀ በኋላ ኅያሉ አዳኝ የጥፋት ሰው እንዲሁም የታላቂቱ ባቢሎን የጥፋት እርኩሰት ከተማ እና ግንብ የመሰረተ እና ያነጸው ንጉስ ናምሩድ ሲሆን ንጉስ ናምሩድ ዘሩ ከግዙፎቹ “ኔፍሌምስ” ተብለው በመጽሐፍ ቅዱስ ከሚጠሩት ዘሩ ከወደቁት የመላክት ዘር እንደሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ አጥኝዎች ይናገራሉ። ኩሽም ናምሩድን ወለደ፤ እርሱምበምድር ላይ ኃያል መሆንን ጀመረ።እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ኃያል አዳኝ ነበረ፤ ስለዚህም። በእግዚአብሔር ፊት ኃያልአዳኝ እንደ ናምሩድ ተባለ። የግዛቱም መጀመሪያ በሰናዖር አገር ባቢሎን፥ ኦሬክ፥ አርካድ፥ ካልኔ ናቸው።” ዘፍ 10:8-10   አዳኙ ናምሩድ የአመጽ ሰው እንደ እርሱ ያለ ኅያል አዳኝ እንደሌለ በመጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ተጽፎ እናነባለን። ኅያሉ አዳኝ ናምሩድ የሚያድነው የዱር እንሰሳዎችን ወይም ሀይለኛ አውሬዎችን ሳይሆን የሰው ልጆችን ነብስ እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱሳችን በግልጽ ያስተምረናል። ኅያሉ አዳኝ ናምሩድ የአመጽ ሰው የአለማችን የመጀመሪያው ንጉስ እና አሁን አለማችን እየተዳደረችበት ያለውን የመንግስት የአገዛዝ ስርአት ህግ ያረቀቀ ታላቅ የጥፋት ሰው እንደሆነ የታሪክ ተመራማሪዎች ይናገራሉ። ኅያሉ አዳኝ የጥፋት ሰው ናምሩድ የሚታወቅባቸው አያሌ ታላላቅ ስሞች ያሉት ሲሆን ከሚታወቅባቸውም ስሞች መካከል የፀሐዩ ንጉስ፣ቅዱስ ኒኮላስ፣ኦዴን፣ዩል እንዲሁም ሳንታክላውስ ( የገና አባት) እንዲሁም በተጨማሪ የናምሩድ ሚስት እና እናት ሰመራሚስ የምትባል ሲሆን የሰማይዋ ንግስት በመባል የምትታወቅ እና በክፉ ፀያፍ የእርኩሰት ድርጊት እንደምትመለክ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ይነግረናል። እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አጥኝዎች መረጃ መሰረት ኅያሉ አዳኝ የጥፋት ሰው ናምሩድ አባቱን ገሎ እናቱን ሰመራሚስን እንዳገባ እና ሚስቱ እናቱም ጭምር እንደሆነች የመጽሐፍ ቅዱስ አጥኝዎቹ በአጽኖት ይነግሩናል። ያስቈጡኝዘንድ፥ ለሰማይ ንግሥት እንጐቻ እንዲያደርጉ ለሌሎችም አማልክት የመጠጥ ቍርባን እንዲያፈስሱ ልጆች እንጨትይሰበስባሉ፥ አባቶችም እሳት ያነድዳሉ፥ ሴቶችም ዱቄት ይለውሳሉ።” ኤር 7:18
ኅያሉ አዳኝ የጥፋት ሰው ናምሩድ በግዜው የአለምን አንድ መንግስት ለመመስረት በነበረው ጽኑ ፍላጎት የባቢሎንን ታወር የገነባ ሲሆን እግዚያብሔርም የልቡን ሀሳብ አውቆ የከተማውን ግንብ የሚሰሩትን ሰዎች ቋንቋቸውን ቀያይሮ ሀሳቡን እንዳጨናገፈበት በመጽሐፍ ቅዱስ ያስተምረናል። እንሆ በእኛ ዘመን የተጨናገፈውን የባቢሎን ግንብን አሁን በዚህ ባለንበት ዘመን በእርሱ የእርኩስ መንፈስ ሀይል ባሉ እና በሚንቀሳቀሱ የአለም ነገስታት እነሆ የባቢሎንን ታወር በእዚህ ዘመን አልቆ የአምላካቸው ኅያሉ አዳኝ የጥፋት ሰው የንጉስ ናምሩድን ሀሳብ የሆነውን አዲሱ የአለም መንግስት ስርአት ( New world order/ Illuminati ) ለመመስረት እየተዘጋጁ ሲሆን ያኔ የናምሩድ የክፋት አሰራር በምድር ሁሉ ላይ በግልጽ በህግ እና ስርአት ወጥቶለት በኋይል እና በግፍ ለጥቂት ግዜ እንደሚሰራ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። “ኢሉሚናቲ ( Illuminati )” የሚስጥር ስብስብ ማህበር አባላት በሙሉ ማለትም አንጋፋ እና ታዋቂ የአለማችን ነገስታቶች እና የሀገር መሪዎች፣ፓለቲከኞች፣በኢኮኖሚ፣በትምህርት፣በሐይማኖት እንዲሁም በተለያዩ የሙያ ዘርፍ ላይ የሚገኙ ግለሰቦች በተለያዩ ምክንያት የሚጠቀሙባቸው የሶስት መአዘን የፒራሚድ ቅርጾች በተጨማሪ እንዲሁም በእጅ ጣቶች አማካኝነት በመጠቀም በተለይ ዘፋኞች እና ታዋቂ ግለሰቦች የሚያሳዩት የሶስት ማእዘን ልዩ ምልክት አላማው በእግዚያብሔር ትእዛዝ የተቋረጠውን የባቢሎንን ግንብ እኛ ዛሬ ሶስት መአዘን ቅርጽ ሆነን ልክ እንደ ግብጻውያን ፒራሚድ ድንጋይ ተባብረን እንደ ቀድሞው በቋንቋ አንድ ሆነን ገንብተን እንጨርሰዋለን። ካዛም የመሪያችን እና የአምላካችንን የናምሩድ ሀሳብ እውን ይሆናል ማለት ሲሆን የግብጽን ፒራሚድን ጨምሮ በአለም ላይ የሚሰሩት የመታሰቢያ ሀውልቶች በሙሉ ምክንያታቸው በጅምር ሳያልቅ የተቋረጠውን የናምሩድን የታላቂቱ ባቢሎንን ግንብ የራእይ ሀሳብ ለመዘከር እና ለማስፈጸም ጭምርም ነው። ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች።ከምሥራቅም ተነሥተው በሄዱ ጊዜበሰናዖር ምድር አንድ ሜዳ አገኙ፤ በዚያም ተቀመጡ። እርስ በርሳቸውም። ኑ፥ ጡብ እንሥራ፥ በእሳትም እንተኵሰውተባባሉ። ጡቡም እንደ ድንጋይ ሆነላቸው፤ የምድርም ዝፋት እንደ ጭቃ ሆነችላቸው። እንዲህም። ኑ ለእኛ ከተማና ራሱወደ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንሥራ፤ በምድር ላይ ሳንበተንም ስማችንን እናስጠራው አሉ። እግዚአብሔርም የአዳም ልጆችየሠሩትን ከተማና ግንብ ለማየት ወረደ። እግዚአብሔርም አለ። እነሆ፥ እነርሱ አንድ ወገን ናቸው፥ ለሁሉም አንድ ቋንቋአላቸው፤ ይህንም ለማድረግ ጀመሩ፤ አሁንም ያሰቡትን ሁሉ ለመሥራት አይከለከሉም። ኑ፥ እንውረድ፤ አንዱ የአንዱን ነገርእንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው።እግዚአብሔርም ከዚያ በምድር ሁሉ ላይ በተናቸው፤ ከተማይቱንም መሥራትተዉ።ስለዚህም ስምዋ ባቢሎን ተባለ፥ እግዚአብሔር በዚያ የምድርን ቋንቋ ሁሉ ደባልቋልና፤ ከዚያም እግዚአብሔር በምድርሁሉ ላይ እነርሱን በትኖአቸዋል።”   ዘፍ 11:1-9
picture12-1
አዲሱ የአለም መንግስት ስርአት ( New world order/ Illuminati ) በመዋቅር ደረጃ ተዋቅሮ ስራ የጀመረ ሲሆን ስራ ሲጀምር የተሰጠው ስም የ“ተባበሩት መንግስታት” ሲባል አሁን በጥቂት ግዜያቶች ውስጥ ዋናውን ስም ማለትም አዲሱ የአለም መንግስት ስርአት ( New world order/ Illuminati ) ወይም አንድ የአለም መንግስት ( New world Government ) እንደሚባል ታላላቆቹ የአለማችን የአገር መሪዎች ፣ የፓለቲካ እና የኢኮኖሚ ባለሙያዎች በየግዜው በሚያቀርቡት መግለጫዎቻቸው እና በተለያዩ አጋጣሚዎች ላይ ያስታውቃሉ። አዲሱ የአለም መንግስት ስርአት ( New world order/ Illuminati ) ተባባሪ አህጉራዊ መዋቅር ያለው ሲሆን ዋና የመንግስቱ ጽህፈት ቤት የሚገኘው ታላቋ ጋለሞታ የምድር እርኩሰት በሆነችው በሀገረ “አሜርካ” የአለም የንግድ ማእከል ዋና እምብርት በሆነችው በኒውዮርክ ከተማ የቀድሞው ተባበሩት መንግስታት ዋና ቢሮ ውስጥ ሲሆን በአውሮፓ ደግሞ የአውሮፓ ልብ በምትባለውና የአውሮፓ የህብረቱ መሰብሰቢያ ዋና ቢሮ በሆነው በቤልጅየም ብራስልስ ሲሆን በቤልጅየም ብራስልስ የሚገኘው የአውሮፓ ህብረት ዋና መስሪያ ቤት የህንጻው ዲዛይን ንጉስ ናምሩድ ሊገነባው ካሰበው እና በእግዚያብሔር ትእዛዝ ከጅምር የቀራው የባቢሎን ግንብ ጋር አንድ አይነት መሆኑ ደግሞ ነገሮች ሁሉ ያደባባይ ሚስጥር መሆናቸውን ቀርቶ ያደባባይ እውነት መሆናቸውን በግልጽ ያሳያል። የአውሮፓ ህብረት የህብረቱ ዋና መሪ ቃል “የብዝህ አንድነት” በመባል ይታወቃል። እንዲሁም በተጨማሪ በአህጉረ አፍሪካ ደግሞ የአፍሪካ ህብረት ዋና መሰብሰቢያ ቢሮ በሆነው በኢትዮጵያ ዋና ከተማ በአዲስ አበባ የሚገኘው አፍሪካ ህብረት ዋና ጽህፈት ቤት የአዲሱ የአለም መንግስት ስርአት ( New world order/ Illuminati ) ወይም አንድ የአለም መንግስት ( New world Government) የአፍሪካ አህጉር ቅርንጫፍ ዋና ማስፈጸሚያ ሲሆን የህብረቱም ዋና መሪ ቃል “የተባበሩት ጠንካራ አፍሪካ” በመባል የሚታወቅ ሲሆን አገራችን ኢትዮጵያም አሁን በስልጣን ላይ ያለው ገዥው መንግስት ከሁሉም የህብረቱ አባል አገሮች በተሻለ የታማኝነት ብቃት በበላይ የስልጣን ሿሚዎች ተረጋግጦ የበላይነቱን እና የተሰሚነቱን ድርሻ ትልቅ ስልጣን ከታላቁ ዘንዶ ከአውሬው ተሰጥቶታል። እንዲሁም በተጨማሪ በሩቅ ምስራቅ ኤሺያ አባል አገራት ማህበር ዋና መቀመጫ ሆኖ በሚገኘው በኢንዶኔዥያ ዋና ከተማ በጃካርታ ሲሆን የማህበሩ መሪ ቃልም “ አንድ ራዕይ፣አንድ ማንነት፣አንድ ህብረተሰብ” በመባል ይታወቃል። እንዲሁም በላቲን አሜርካ የደቡብ አሜርካ ህዝቦች ህብረት በመባል የሚታወቅ ሲሆን የህብረቱም ዋና መቀመጫ ጽህፈት ቤት የሚገኘው ደግሞ “ኩዊቶ” ኢኳዶር ውስጥ ሲሆን ሁሉም በአለም የሚገኙ የየአህጉራቱ ማህበራቶች በሙሉ በፓለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ በጣም በጠበቀ ቁርኝት አንድ ላይ የተሳሰሩ ሲሆን ፒራሚዱ ጫፍ ላይ ላለው የአዲሱ የአለም መንግስት ስርአት ( New world order/ Illuminati ) ወይም አንድ የአለም መንግስት ( New world Government) ዋና አጋር ተደርገው እንዲንቀሳቀሱ ታላቅ ተስፋ እና አመኔታ ተጥሎባቸዋል። በተጨማሪም የአዲሱ የአለም መንግስት ስርአት ( New world order/ Illuminati ) ወይም አንድ የአለም መንግስት ( New world Government) ዋና የኢኮኖሚ እና የፍይናንስ ተቋም የሆኑት የአለም ባንክ እና አለም አቀፉ የገንዘብ አስተዳደር ተቋም አይኤምኤፍ ለአባላት እና አጋር አገራት የሾሟቸው አምባገነን መሪዎች በህዝብ አመጽ እንዳይወድቁ አስፈላጊውን ባጀት በብድር ስም እና በእርዳታ ስም ስልጣንን ላይ ለማቆየት ድጎማ ያደርጋሉ። የአገራችን በኢትዮጵያ የሚገኘው ፈላጭ ቆራጭ ጨቋኝ ስርአትም በአፍሪካ አህጉር ውስጥ ከግብጽ ቀጥሎ ትልቁን የእርዳታ እና የብድር አገልግሎት ከሚያገኙት አገሮች በዋና ተርታ ተሰልፈዋል።
የአዲሱ የአለም መንግስት ስርአት ( New world order/ Illuminati ) ወይም አንድ የአለም መንግስት ( New world Government) እየኖርንባት ባለችበት ፕላኔታችን ላይ ምን እየሰራ ነው  በቀጣይነትስ ምንለመስራት አቅዷል  
የአዲሱ የአለም መንግስት ስርአት ( New world order/ Illuminati ) ሲቋቋም ሶስት አይነት ራዕዮችን አንግቦ የመጣ ያለ ሲሆን እነሱም፦
1ኛ አንድ የአለም መንግስትን የሚያስተዳድረው መንግስትን ( New world Government)  ማቋቋም። በአለማችን ሁሉ ላይ ተግባራዊ ማድረግ።
2ኛ አንድ የአለም መገበያያ ገንዘብን (world Currency ) ማቋቋም። እንዲሁም በአለማችን ሁሉ ላይ ተግባራዊ ማድረግ።
3ኛ አንድ የአለም ሐይማኖትን (world Religion) ማቋቋም። እንዲሁም በአለማችን ሁሉ ላይ ተግባራዊ ማድረግ። ዋና አቋሞቹ ሲሆን ሁሉም የአለማችን ክፍል ለማለት ይቻላል ህግና ስርአቶቹን በአሁኑ ሰአት ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
እንደ እውነቱ ከሆነ የሁለተኛው የአለም ጦርነት መነሻው ዋናው ምክንያት የአዲሱ የአለም መንግስት ስርአት ( New world order/ Illuminati ) ወይም አንድ የአለም መንግስት ( New world Government) አለምን በፓለቲካ፣በኢኮኖሚ እና በማህበራዊ በማቀናጀት በአንድ መንግስት ጥላ ስር አድርጎ የመግዛት የይገባኛል ጥያቄ ሲሆን ይህም የጥቅም እና ገናና ሆኖ የአለምን ህዝብ በግድ ረግጦ የመግዛት ጦርነት ሊባል ይችላል። በግዜው በጦርነቱ የተሳተፉ ኋያላን አገሮች ሁሉም የሚስጥር ማህበሩ የኢሉሚናቲ ( Illuminati )” ዋና አባል ሀገራት ሲሆኑ በግዜው የኮሚኒስት ናዚ መሪ የነበረው እና አለምን ባንድ መንግስት ጥላ እንድትተዳደር ታላቁን እና ዘግናኙን ከ45ሚሊዮን በላይ ሰው ያለቀበትን ሁለተኛውን የአለም ጦርነትን የጀመረው አዶልፍ ሂትለር ዋና አላማ እና እቅድ የዚሁ የአዲሱ የአለም መንግስት ስርአት ( New world order/ Illuminati ) ለመመስረት ሲሆን ጦርነቱም የአለም የኢሊቶች እና የባንከሮች ጦርነት በመባል ሲታወቅ በስተመጨረሻም የአዲሱ የአለም መንግስት ስርአት ( New world order/ Illuminati ) ዳግም ለመመስረት በለስ የቀናት አሜርካም የሁለተኛውን የአለም ጦርነትን “መልካሙ ጦርነት” (Good War) በማለት አወድሳዋለች። እንደ ዶክተር ጆን ኮልማን እንደ እኤአ 1993 የትንታኔ ጽሁፍ መሰረት ብዛታቸው 300 አባላት የሆኑ የሚስጥር ማህበሩ የኢሉሚናቲ ( Illuminati )” ኮሚቴዎች ማለትም የአለማችን የነገሮች ሁሉ ቁንጮ ማለትም (በፓለቲካ፣በኢኮኖሚ እና በማህበራዊ ) አለማችንን የሚያስተዳድሩት ግለሰቦች ባለ21 ነጥብ ጎል አዲሱ የአለም መንግስት ስርአት ( New world order/ Illuminati ) እስከ መጨረሻው በአለም ሁሉ ላይ የሚሰራበትን ህገ መንግስት ህገ ደንብ አርቅቀው በስራ ላይ አውለውታል። ስለሆነም ዛሬ እየኖርንባት ባለችው ፕላኔት ላይ በፓለቲካዊ፣በኢኮኖሚያዊ እና በማህበራዊ እየተከሰቱ ያሉት ከፍተኛ ቀውሶች በሙሉ የዚሁ አዲሱ የአለም መንግስት ስርአት ( New world order/ Illuminati ) ምስረታ ዋና አካል እና የፓለቲካ ግብአት መሆናቸው ልብ ሊባል ይገባል።
ባለ21 ነጥቡ ጎል የሚስጥር ማህበሩ የኢሉሚናቲ ( Illuminati )”በአለም ላይ በፓለቲካዊ፣በኢኮኖሚያዊ እና በማህበራዊ ኩነቶች ሆነው እንዲሰራባቸው የተዋቀሩት መዋቅሮች እያንዳንዱን ከዚህ በታች እንደሚከተለው በዝርዝር ተዘርዝሮ ይነበባል፦
  1. አንድ የአለም መንግስትን ( One world Government ) መመስረት እንዲሁም በአዲሱ የአለም መንግስት ስርአት ( New world order ) ስር የሚተዳደር እና መንግስት የሚቆጣጠረው በአንድ አይነት የመንግስት ስርአት በመዘርጋት የአለም አብያተ ቤተክርስትያንን መምራት አዲሱ የአለም መንግስት ስርአት ( New world order ) እኤአ 1920 እስከ 1930 ድረስ የአለም አብያተ ቤተክርስትያኖችን እንደ አዲስ በራሱ ስርአት እና ህግ ቀርጾ ስራ ላይ ያዋለ ሲሆን በአሁኑ ዘመን በአለም ላይ የሚገኙ ቤተክርስትያኖች በሙሉ በአዲሱ የአለም መንግስት ስርአት ( New world order ) መንግስት ስርአት ህግ መሰረት እየተመሩ ይገኛሉ። ለዚህም ነው በዚህ ዘመን ያለ የአለማችን ክርስትያን ማህበረሰብ በተዝናና አለማዊ የክርስትና ህይወት በመኖር ህይወቱን ለሰይጣን መስዋዕት አድርጎ ለስጋዊ ህይወት ብቻ እየኖረ ይገኛል።
  2. በአለም ህዝቦች ላይ በፓለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ውጫዊ ቀውሶች እና ስቆቃዎች በመፍጠር ከእያንዳንዱ የአለማችን ነዋሪ አይምሮ እና ልቦና ላይ የአገር እና የማንነት ስሜትን ማጥፋት። እንዲሁም በተቃራኒው እያንዳንዱ የአለም ማህበረሰብ እራሱን ግሎባሊስት (አለም አቀፍ) ዜጋ አድርጎ እንዲቀበለው እና የአዲሱ የአለም መንግስት ስርአት ( New world order/ Illuminati ) የመንግስት ህግን በየትኛውም መንገድ ተቀብሎ ተግባራዊ እንዲያደርገው ማድረግ።
  3. በሐይማኖቶች ላይ ታላቅ የረቀቀ እና የተቀናጀ ችግሮችን መፍጠር በተለይ የክርስትና እምነት ማጥፋት ከላይ በመጀመሪያው እንደተገለጸው። በአዲሱ የአለም መንግስት ስርአት ( New world order/ Illuminati ) ህግ ስር አንተዳደርም ያሉትን አብያቤተክርስትያንን ማጥፋት።
  4. እያንዳንዱን ግለሰብ አይምሮውን መቆጣጠር ታላቅ ችሎታ ያለውን እጅግ ዘመናዊ ኮምፒዩተራይዝድ መሳሪያ እንደ ታዋቂው አሜርካዊው ፓለቲካ ሳይንቲስት እና ጂኦእስትራቴጂስቱ “ዘቢግኒው ብራዘእዝኢንኪይ” ( Zbignew Brzezinski ) “ቴክንትሮኒክ” ( Technetronic ) ብሎ የሚጠራውን እጅግ ዘመናዊ ሳይንሳዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የሰዎችን አይምሮ ሁሉ መቆጣጠርና ሰዎችን እንደገና እንደሮቦት በመፍጠር በአለማችን ላይ የቴክኖሎጂ ሽብር ማወጅ።
  5. ታላላቅ የአለማችን ኢንዱስትሪዎችን ሆነ ተብሎ እንዲከስሩ በማድረግ መዝጋት። እንዲሁም የኒውክለርን ለኤሌክትሪክ ኀይል ማመንጫ  ፍጆታ መጠቀምን ማቆም። የቀሩትን ጥቂት ኢንዱስትሪዎች እና አገልግሎት መስጫ ተቋማቶችን በሙሉ ኮምፒውተራይዝድ በማድረግ የሰው ልጅን ውድ ጭንቅላት ያለ ስራ ዋጋ ቢስ ማድረግ። እንዲሁም በተጨማሪ በሰሜን አሜርካ እና በአውሮፓ በአዲሱ የንግድ ስምምነት መሰረት በጣም በወረደ የሰራተኛ የቅጥር ዋጋ ሰዎችን እንደ ባሪያ ስራ ማሰራት (ልክ እንደቀድሞው እንደ ባሪያ አሳዳሪ ዘመን እንደነበረው ስርአት ማለት ነው) እንዲሁም ከስራ የተፈናቀለው ባለሙያ ሰራተኛ ስራ ባለማግኘቱ በታላቅ ብስጭት የተነሳ  ለአደገኛ አደንዛዥ እጽ ማለትም ለሄሮይን፣ለኦፒየም፣ኮኬይን እና ለአደገኛ የአልኮል መጠጦች እራሱን ባሪያ አድርጎ አሳልፎ እንዲሰጥ ማድረግ በስተመጨረሻም ህይወቱን በገዛ እጁ ያጠፋታል። ዋናው የኢሉሚናቲ ( Illuminati ) ፍላጎትም ይህንን እንዲያደርግ እድሉን እና ሁኔታዎችን ለእያንዳንዱ የአለም ህብረተሰብ ማመቻቸት ነው። ምክንያቱም በየትኛውም አጋጣሚ የሰዎች ሞት ለህዝብ ቅነሳ ወሳኝ አማራጭ የሌለው መፍትሄ ነው ተብሎ በኢሉሚናቲ ( Illuminati ) ማህበረተሰብ ዘንድ ይታመናልና።
  6. በስተመጨረሻም አደገኛ አደንዛዥ እጾችን መጠቀም በህግ ይፈቀዳል። እንዲሁም በስነጥበብ ስም በግሉ ልቅ የወሲብ ፊልምን መስራት እና ማሰራጨት በህግ ይፈቀዳል። ብዙ የአለም ማህበረሰቦችም ህጉን በደስታ ተቀብለውት በአሁኑ ሰአት ዋናው የኑሮ ዘይቤ አድርገውት ይዝናኑበታል።
  7. በአለማችን ላይ ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር ብዛት ያለባቸው ከተሞች ላይ ማንኛውንም አይነት ዘዴ በመጠቀም የህዝብ ቁጥርን መቀነስ።
  8. ሁሉንም ሳይንሳዊ ግኝቶችን በሙሉ በእያንዳንዱ ነገሮች ላይ ጥቅም ላይ ማዋል። በተመሳሳዩ የተፈጥሮ ማንኛውንም ማእድንና ንጥረ ነገር ካለምንም ስስት እስከመጨራሻው ድረስ መጠቀም።
  9. በበለጸጉ አገሮች አማካኝነት በማናቸውም ሁኔታ እና አጋጣሚ ሰው ሰራሽ ጦርነቶችን፣በሽታዎችን፣ረሀቦችን እና ልዩ ልዩ ሰው ሰራሽ የተፈጥሮ አደጋዎችን በሶስተኛ አለም ደሀ አገሮች ላይ በማሰራጨት እስከ እኤአ 2050 ድረስ 3ቢሊዮን የአለም ህዝብ በዚህ መካኒዝም መቀነስ “የሚበሉ ሰዎች አይጠቅሙም” የሚባለውን ጥሪ ተግባራዊ መደረግ አለበት። 300 አባላት ያቀፈው የኢሉሚናቲ ( Illuminati )” የሚስጥር ማህበሩ ኮሚሽነር ሳይሩስ ቫአንሴ (Cyrus Vanceበጽሁፉ እንደገለጸው “የሚበሉ ሰዎች አይጠቅሙም” ለህዝብ ቅነሳ የምንጠቀመው ድርጊቶች እንዴት የዘር ማጥፋት ተብሎ ሊወሰድ ይችላል በማለት የሚከራከር ሲሆን በዩኤስ አሜርካ እስከ እኤአ 2050 ድረስ 100 ሚሊዮን ህዝብ መቀነስ እንዳለበት ግሎባል 2000 ሪፓርት የሚያመለክት ሲሆን በሪፓርቱም የቀድሞው የዩኤስ አሜርካ ፕሬዝዳንት ጀምስ አርል ካርተር እና ሰክረተሬት እስቴት ኤድዋን ሙስኪይ ሀሳቡን ተቀብለውት አጽድቀውታል።
  10. የህዝቡን ኢኮኖሚ አቅም በማዳከም እንዲሁም ዋጋ ቢስ በማድረግ እንዲሁም በተጨማሪም ብዛት ያላቸውን ታታሪ ባለሙያ ሰራተኞን ከስራ በመቀነስ እና ስራቸውን እንዲያቆሙ በማድረግ በማንኮታኮት ቅስማቸውን መስበር። እንዲሁም አገር ተረካቢ ወጣቶችን ሆነ ተብሎ በአደገኛ አደንዛዥ እጽ እና የአልኮል ተጠቃሚ በማድረግ እንዲሁም በሮክ ሙዚቃ ታጅበው አደገኛ የአመጽ ህይወት እንዲኖሩ ሁኔታዎችን ማመቻቸት። በስተመጨረሻም ወጣቶቹን ከወላጆቻቸው ጋር እንዳይስማሙ በማድረግ ቤተሰብን ማፍረስ።
  11. በሁሉም ስፍራ እያንዳንዱን ሰው እንቅስቃሴውን መቆጣጠር እንዲሁም በተጨማሪ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ህዝቡ ላይ የፓለቲካ፣የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ከባድ ቀውሶችን በመፍጠር እነዛ የተፈጠሩ ቀውሶችን መልሶ መቆጣጠር። ያን ግዜ ህዝቡ በተፈጠረው ነገር ግራ አጋብቶ የሞራል ውድቀት ማስከተል ህዝቡም በተፈጠረው ነገር የሞራል ውድቀት ስለገጠመው አማራጭም ስለሚያጣ ያኔ አርፎ አድርግ የተባለውን እያደረገ በፍርኋት ተገዝቶ ይኖራል።
  12. አዲስ የባእድ ያልተለመዱ ልማዳዊ ድርጊቶችን መፍጠር እንዲሁም የሮክስታር ጋንግስተሮችን በመላው አሜርካ እና በአውሮፓ ማሰራጨት በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ እነዚህ የተፈጠሩ አዲስ ባእዳዊ ልማዶች እና ሮክስታር ጋንግስተሮችን ህብረተሰቡ እንዲቀበላቸው እና ልማድ እንዲያደርጋቸው ማስተዋወቅ።
  13. በክርስትና እምነት አስተምሮ ውስጥ እውነተኛውን ትምህርት በባእድ የሀሰት ትምህርቶች መበረዝ እንዲሁም እውነተኛውን አስተምሮ ማጥፋት። በተለይ ህገ ፂዮናዊቷን እስራኤል የምትባለውን ሀገር “በእግዚያብሔር የተመረጠ ታላቅ ህዝብ” የሚለውን ቃል የተለያየ ስም በመስጠት እና ጥላሸት በመቀባት እስራኤል የምትባል አገር በአለም ህዝብ ዘንድ እንድትጠላ ማድረግ። እንዲሁም በተጨማሪ የክርስትያን ቤተክርስትያኖችን ላይ በከፍተኛ የገንዘብ ባጀት በመመደብ እና የገንዘብ ድጎማ በማድረግ ቤተክርስቲያኖችን ወደሚፈለገው አቅጣጫ መቀልበስ።
  14. ያልተለመዱ ጨቋኝ እና ፈላጭ ቆራጭ የሆኑ የሽብር ተቋማቶችን በሀይማኖት ካባ ስም በመሸፈን በመላው አለም ማሰራጨት እንደ ሙስሊም ብራዘርሁድ ወይም ሙስሊም አክራሪያን (አይሲኤስ፣አልቃይዳ፣አልኑስራ እና አለሸባብ)
  15. “የሐይማኖቶች እኩልነት” በመላው አለም በህግ ማስረጽ በተለይ በክርስትና ሀይማኖት ስም የተፈጠሩትን የሀሰት የክርስትና ሀይማኖቶችን በየአለማቱ ማሰራጨት እንዲሁም በሀይማኖት ስም ግጭቶችን በህብረተሰቡ ውስጥ መፍጠርና እነዛ የተፈጠሩ ግጭቶችን ህዝቡ እስኪመረው ድረስ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጁት የመገናኛ አውታሮች እና በማህበራዊ ድረገጾች አማካኝነት ማሰራጨት ልክ እንደ አይሲኤስ የሰዎችን አንገት ሲገዘግዙ የሚያሳይ እጅግ ዘግናኝ ምስል ጭምር ማለት ሲሆን በዚህም የአለም ህዝብ ላይ የሽብር ፍርሀትን ማሰራጨት።
  16. በምክንያት የአለምን ኢኮኖሚ ባጠቃላይ ማፈራረስ። እንዲሁም በተጨማሪ በአለም ህዝብ ላይ የፓለቲካዊ ኪሳራ ግራ የሚያጋባ ውዥንብር መፍጠር።
  17. በሀገሪቱ ውስጥ ያሉትን የሰፈር፣የክልል እና የፌደራሉን የፓሊስ አባላት በሙሉ በሌላ ኋይል መቆጣጠር።
  18. እጅግ ግዙፍ ድጋፍ እና ትልቅ እገዛ ለግዙፎቹ እንደ የተባበሩት መንግስታት (UN)፣እንደ አለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF)፣ እንደ አለም ባንክ እና አለም አቀፉ ፍርድ ቤት የመሳሰሉት ተቋማቶች ላይ ማድረግ በተለይ ለተባበሩት መንግስታት ልዩ ድጋፍ ማድረግ ምክንያቱም ሁሉም ግዙፍ ተቋማቶች የሚተዳደሩት በእርሱ አይምሮ ውስጥ ስለሆነ
  19. ወደ ሁሉም የአለም ሀገሮች ሁሉ ላይ በጥልቀት በመግባት መንግስታቸውን መገልበጥ እንዲሁም የአገር ሉአላዊነት ስሜትን በሁሉም መንግስታት ውስጥ ማጥፋት እንዲሁም ህዝቡ የራሱን መንግስት እንዳይወክል ከህዝቡ ልብ እና አይምሮ ውስጥ ያገር ሉዋላዊነት ስሜት ማጥፋት።
  20. በአለም ሁሉ ላይ እንደ አይሲኤስ፣አልቃይዳ፣አልኑስራ እና አለሸባብ ሌሎችም የሽብር ተቋማቶችን ፈጥሮ በእያንዳንዱ አገር ማሰራጨት። የሽብር ድርጊቶችን በሰላማዊው ህዝብ ላይ ማከናወን።
  21. የትምህርት ስርአቱን ባጠቃላይ በሞናፓል መቆጣጠር እንዲሁም ተማሪዎቹን ለስርአቱ ታማኝ አገልጋይ አድርጎ መቅረጽ እንዲሁም የትምህርት አሰጣጥ ሲስተሙ በአብዛኛው የሚያተኩረው በአይምሮ እና ልቦናዊ ስልጠና ላይ ሳይሆን ገንዘብ እና ስራ የሚያስገኙ ሙያዊ እውቀቶች ላይ ብቻ ያተኩራል።
አንጋፋ የአለም መሪዎች ፣ ፓለቲከኞች ፣ አለምን በሀብት እና በኢኮኖሚ የሚያስተዳድሩ ባለሀብቶች፣የሀይማኖት መሪዎች እና ታላላቅ የአለማችን ግለሰቦች ስለ አዲሱ የአለም መንግስት ስርአት ( New world order/ Illuminati ) ምን ይላሉ
የአለማችንን ፓለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ተቋሟቶችን ሁሉ ጀርባ ሆነው በገንዘባቸው ሀይል ተቋማቶቹን መስርተው የሚያስተዳድሩት እንዲሁም የአገራችን የኢትዮጵያን ጨምሮ በመላው አለም የሚገኙ የብሄራዊ ባንኮችን የሚያስተዳድሩት እንዲሁም አውዳሚ አሰቃቂ ባውሎጂካል በሽታዎች እና የኒውክልየር ቦምብ አምራች እና ባለቤት የሆኑት እንዲሁም የአደገኛ ዘግናኝ ጦርነቶችን እና በሽታዎችን በአለማችን ሁሉ ላይ እርሻዎችን የሚያርሱ እና የሚያሳርሱ የአለማችን ባንከር ትሪሊየነር የሆኑት የአዲሱ የአለም መንግስት ስርአት ( New world order/ Illuminati ) ዋና ቀንደኛ አቀኝቃኝ እና ደጋፊ፦
  1. የ“ኢሉሚናቲ ( Illuminati )” አባሉ እና “ሮስቻይልድ ፋሚሊ” በመባል የሚታወቀውን የአለማችን ቁጥር አንድ እጅግ ግዙፉን የባንኪንግ አገልግሎት መስራች እና ባለቤት “ሜዬር አምስቼል ሮስቻይልድ” ስለ አዲሱ የአለም መንግስት ስርአት ( New world order/ Illuminati ) መመስረት በማስመልከት ከዛሬ 300 አመት በፊት እንዲህ ብሎ ነበር፦ “እነዚያ ለሮስቻይልድ የሚመስሉት ትንሽ እዳዎች ናቸው። በቀጣይነትም በአለም ኢኮኖሚ ላይ ሁል ግዜ ተጽእኖ መፍጠር ነው። ይህንን ደግሞ እናውቃለን። በአውሮፓ ህብረት አገሮች እያንዳንዱ የፓለቲካ እንቅስቃሴ ከአራት መአዘን ቀለበት ጀርባ ሆነን እውን እንደምናደርገው እንዲሁም ወደ ፊትም አንድ እርምጃ እንደምናስኬደው እናውቃለን ይህም አንድ እርምጃ አንድ የአለም መንግስትን ( One world Government ) መመስረት ይሆናል።”
  2. “እኛ ሁላችን ዋናውን የፓለቲካ፣የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ታላቅ ቀውስ በአለም ላይ እንዲከሰት እንፈልጋለን። ያኔ አገሮች አዲሱ የአለም መንግስት ስርአት ( New world order ) ይቀበሉታል” ግሎባሊስቱ መልቲ ቢሊየነር እንዲሁም ባንከር ዴቪድ ሮክፌለር
  3. ምንም እንኳ እኛ ጥቂቶቹ እንደምናምነው (የሮክፌለር ቤተሰብ) ለዩኤስ አሜርካ ጥቅም የሚስጥር መስመር ተወካይ ሰራተኞች እንደሆንን ነው። በባህሪያችን የእኔ ቤተሰብ እና እኔ “ኢንተርናሽናሊስት” ነን። እንዲሁም ማንኛውንም በዙሪያችን ካሉት ነገሮች ሁሉ እጅግ ተቃራኒ የሆነ ነገር በአለም ላይ ለመስራት በሚስጥር ስምምነት አለን። (በዚሁ አጋጣሚ ለማሳሰብ የምፈልገው ዴቪድ ሮክፌለር እና ቤተሰቡ በአለም ላይ የሚደረጉ ዘግናኝ ጦርነቶችን እንዲከሰቱ ያደረገ ሰው ሲሆን በቅርቡ የተከሰተውን አሰቃቂውን የ“ዚካ” ቫይረስ ባለቤትም ጭምር ነው።) እንዲሁም የተቀናጀ አለማቀፋዊ የፓለቲካ እና የኢኮኖሚ መሰረትም አለን ይህም አንድ የአለም መንግስት ( One world Government ) በመባል ይታወቃል። ፍቃዳችሁ ከሆነ ያ ክፍያችሁ ይሆናል። እና በጥፋትነቴ ቆሜያለሁ አይፀፅተኝም እንዲያውም ባደረኩት ነገር ሁሉ ኮርቼበታለሁ” ግሎባሊስቱ መልቲ ቢሊየነር እንዲሁም ባንከር ዴቪድ ሮክፌለር
  4. “እንደ እውነቱ ከሆነ እየሰራነው ያለነው አዲሱ የወልዲ መከላከያ ክትባት እና ጽንስን ማስወረድ ለጤና አገልግሎት ታላቅ ስራ ነው። ምናልባት በዚህ አገልግሎት በአለም ላይ ከ10 እስከ 15 ፐርሰንት የስነ ህዝብ ቁጥር ሊቀንስ ይችላል።” የማይክሮሶፍት መስራቹ መልቲ ቢሊየነር ቢልጌትስ
  5. “የመጨረሻው ጎል የአለም ህዝብ እያንዳንዱ RFID ማይክሮ ችፕስ መቀበል አለባቸው። ሁሉንም ህብረተሰብ ክፍል ተቆጣጥሮ ለመያዝ ባንከሮች ይፈልጋሉ እንዲሁም በተመሳሳዩ የአለማችን ተቆጣጥሮ ለመያዝ ኢሊቶች ይፈልጋሉ።” ኒኮላስ ሮክፌለር
  6. “ እኔ የምለው ወደ እውነቱ እዚህ ስንመጣ ሂትለር እጅግ በጣም ጥሩ ሀሳብ ያለው አብዮተኛ ነበር። ነገር ግን በእርሱ ግዜ ወደ ፊት ርቆ ሊሰራ አልቻለም። ነገር ግን እንደምትገምቱት ከሆነ እርሱ እንደ ፌስብክ ያሉትን ነገሮችን ቢያገኝ ኖሮ ኳሷን እያስጮኀ በአለማችን ለሶስተኛው ባለሀብት ጀርባ ሆኖ ድጋፍ አያደርግምን?” ማርክ ዙክርበግ የፌስቡክ መስራች እና መልቲ ቢሊየነር እንዲሁም በአሜርካው የደህንነት ተቋም በሆነው በሲአይኤ የፌስቡክ ዳይሬክተር
  7. “በውስጥ ትእዛዝ አንድ የአለም መንግስትን ( One world Government ) ለመደምደም እኛ 3ኛ የአለም ጦርነት እንዲኬያሄድ እንፈልጋለን። በጦርነቱም ከአለም ህዝብ 90% ማስወገድ አለብን። ይህ ለሰው ልጅ የስነ ህዝብ ቁጥር መቀነሻ ጥሩ መፍትሄ ይሆናል። በስተመጨረሻም የህዝብ ተቃውሞዎችን በሙሉ እጃቸውን ይሰጣሉ። ከዚያም እኛ ወደ ፊት በመገስገስ የኢንዱስትሪ ብልት የሆነውን አለም አቀፍ የፊውዳል ስርአትን ፕላኔታችንን እናድን በሚል ስም እንፈጥራለን።” ጄፍ ሮስቻይልድ ኢንተርፕሩነር እና መልቲ ቢሊየነር
  8. “ወንዶችን፣ሴቶችን እንዲሁም ህጻናትን ባሪያ አድርጎ ለመግዛት እዚህ አገር ሊደረግ ያለ ትልቅ ሴራዊ የሽፍጥ ድርጊት አለ። እርሱም የሚጠብቀው የእኔን ከዚህ በጣም ከሚታወቀው ቢሮ መልቀቅን ነው። ያኔ ያ! የተደበቀ ሴራዊ ሽፍጥ በግልጽ ይሰራል” የቀድሞው የአሜርካው ፕሬዚዳንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ ከመገደላቸው ከሰባት ቀን በፊት የተናገሩት
  9. “ብሔራዊ ህብረተሰብን በመጠቀም እና አብዮት በማስነሳት አዲሱ የአለም መንግስት ስርአት ( New world order) ይመሰረታል!” አዶልፍ ሂትለር
  10. “ከአንድ በላይ የሆኑ ትናንሽ አገሮችን እንዴት መደገፍ ይቻላል፡ ትልቅ ሀሳብ ነው። አዲሱ የአለም መንግስት ስርአት ( New world order ) የተሰበጣጠረን ህዝብ አንድ ላይ ለማቀፍ እንዲሁም ለመምራት በትክክለኛው ምክንያት ተለይቶ ሲኖር የነበረውን የአለማችን የሰው ዘር በሙሉ ሰላም እና ደህንነት፣ነጻነት እና የመመሪያ ህግና ስርአት አስገኝቷል። የቀድሞው የአሜርካው ፕሬዚዳንት ጆርጅ ቡሽ ትልቁ
  11. “የኢራቁ ጦርነት በትብብር ወደ ፊት እንድንጓዝ ትንሽ አጋጣሚ አስገኝቷል። የዚህ ችግር በመቋጫው ወቅት ከአዲሱ የአለም መንግስት ስርአት ( New world order ) ጋር ስብጥር ፈጥሮ አንድ ይሆናል” የቀድሞው የአሜርካው ፕሬዚዳንት ጆርጅ ቡሽ ትንሹ
  12. “ያለ ደም ዋጋ እንዲሁም በስተመጨረሻም የቃል እና የገንዘብ ታላቅ ክፍያ ሳንከፍል አዲሱ የአለም መንግስት ስርአት ( New world order ) ማግኘት አንችልም።” አርተር ስቹልዚንገር
  13. “አዲሱ የአለም መንግስት ስርአት ( New world order ) ለማግኘት፦ ከሰዎች አይምሮ ውስጥ ግለኝነትን፣ለቤተሰብ ባህል ታማኝ መሆንን፣የሀገር ፍቅር ስሜትን እና የሐይማኖት ስርአቶችን በሙሉ ማስወገድ እጅግ አስፈላጊ እና ዋናው ነገር ነው።” ብሮክ ቻይስሎም የቀድሞው የተባበሩት መንግስታት የጤና ድርጅት “WHO” ዋና ዳይሬክተር
  14. “አዲሱ የአለም መንግስት ስርአት ( New world order ) እንዴት ነው የምናገኘው” ሄነሪ ኪሲንጀር ታዋቂው የፓለቲካ ሳይንቲስት እና ዲፕሎማት
ቤተክርስስትያኖች አዲሱ የአለም መንግስት ስርአት ( New world order/ Illuminati ) ጋር ያላቸው ፓለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቁርኝት
paster-dawit
በዛሬ ግዜ በግልጽ በአለማችን ላይ በክርስቶስ ስም የተከፈቱ ቤተክርስትያኖች በሙሉ ማለት ይቻላል አዲሱ የአለም መንግስት ስርአት ( New world order/ Illuminati ) ጋር ከመቼውም ግዜ በተለየ መልኩ እጅና ጓንት ሆነው በልማት፣በኢኮኖሚያዊ እና በማህበራዊ ነገሮች ሁሉ ሲሰሩ ይታያል። ሁሉም በክርስትያን ስም በር ከፍተው የሚሰሩ ቤተክርስቲያኖች ሁሉ መሰፈርቱን አሟልተው ከመንግስት ህጋዊ ፈቃድ ማውጣት ይጠበቅባቸዋል። ያ! ማለት በሌላ አነጋገር ሁሉም ቤተክርስትያኖች በሙሉ በመንግስት ቁጥጥር ስር ሲሆኑ ተጠሪነታቸውም ለእግዚያብሔር ሳይሆን ፈቃዱን ለሰጣቸው አካል ለመንግስት መሆኑን ብዙ ግዜ በድርጊታቸው እንዲሁም በቃላቸው እናያለን። ለዚህም ነው እንደቀድሞው ዘመን በወንጌል ምክንያት ሞት፣እስራት፣ስቃይ እንዲሁም ስደት የቆመው ምክንያቱም ሁላችንም እንደምናውቀው በየቤተ-እምነቱ ደጃፍ እና ጉባኤ ውስጥ አስጸያፊውን የመንግስት ባንድራ ሲያውለበልቡት ታዩታላችሁ እንዲሁም ከመጽሐፍ ቅዱስ በተቃራኒው ስለ መንግስት ስለሰራው ልማት በየተጠሩበት የመንግስት ስብሰባ እና በየአዳራሾቻቸው ውስጥ ያሞጋግሳሉ፣ያደንቃሉ፣ይባርካሉ፣ይጸልያሉ፣ለልማት ገንዘብ ያዋጣሉ፣የልማት አውታሮችን ጎብኝተው ባርከው ይመጣሉ፣በልማት ስም የሩጫ ፌስት በአሎችን ያዘጋጃሉ። ኧኅ ………..ብላ ብላ ብላ……….. ሌላም ሌላም፣ በሀገሪቱ ውስጥ መንግስት በሀይል ከጨካኝ የጫካ አውሬ እጅግ ጨካኝ ሆኖ በብዙ ችግር ያለውን የህዝቡን ደም በጠራራ ጸሐይ አፍሶ ሲጠጣ እነዛ ስለ በውስጣቸው ቅንጣት ፍቅር ሳይኖራቸው ስለ ክርስቶስ ፍቅር ሲሰብኩ የምናውቃቸው ትላልቅ ደጋፊ ያላቸው ቱጃር የወንጌል ሰባኪዎች በዚህ ቀውጢ ታላቅ የንስሀ ብሄራዊ ጸሎት በሚያስፈልግበት ሰአት እነሱ የት እንዳሉና ምን እንደሚሰሩ አይታወቅም አንዳንዶቹ ጎረምሳ ወንጌላውያን ከቃሉ መርጠው በማውጣት የሐዋርያው ጳውሎስን የሮሜ 13 መልእክቱን እንደወረደ በመተርጎም እና ለፓለቲካ ፍጆታ በማዋል ሲያመቻምቹት ይስተዋላል። ሮሜ 13 የሚለው እንደዚህ ነው ነፍስ ሁሉ በበላይላሉት ባለ ሥልጣኖች ይገዛ። ከእግዚአብሔር ካልተገኘ በቀር ሥልጣን የለምና፤ ያሉትም ባለ ሥልጣኖች በእግዚአብሔርየተሾሙ ናቸው። ስለዚህ ባለ ሥልጣንን የሚቃወም የእግዚአብሔርን ሥርዓት ይቃወማል፤ የሚቃወሙትም በራሳቸው ላይፍርድን ይቀበላሉ። ገዥዎች ለክፉ አድራጊዎች እንጂ መልካም ለሚያደርጉ የሚያስፈሩ አይደሉምና። ባለ ሥልጣንንእንዳትፈራ ትወዳለህን? መልካሙን አድርግ ከእርሱም ምስጋና ይሆንልሃል፤ለመልካም ነገር ለአንተ የእግዚአብሔር አገልጋይነውና። በከንቱ ግን ሰይፍ አይታጠቅምና ክፉ ብታደርግ ፍራ፤ ቍጣውን ለማሳየት ክፉ አድራጊውን የሚበቀል የእግዚአብሔርአገልጋይ ነውና።ስለዚህ ስለ ቍጣው ብቻ አይደለም ነገር ግን ስለ ሕሊና ደግሞ መገዛት ግድ ነው።ስለዚህ ደግሞትገብራላችሁና፤ በዚህ ነገር የሚተጉ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸውና።ለሁሉ የሚገባውን አስረክቡ፤ ግብር ለሚገባውግብርን፥ ቀረጥ ለሚገባው ቀረጥን፥ መፈራት ለሚገባው መፈራትን፥ ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ።እርስ በርሳችሁ ከመዋደድበቀር ለማንም ዕዳ አይኑርባችሁ፥ ሌላውን የሚወድ ሕግን ፈጽሞታልና።” ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ሁሉንም ክፍል በደንብ ስናነበው እንዲሁም ከሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች የቃሉን ትርጉም ጋር ስናመሳክረው ክፍሉ የሚለው መንግስት ለሚያወጣው የቀረጥ ግብር ክፍያ ህግን ተግባራዊ እንድናደርግ እና እንድንፈጽም የሚያሳስብ ሲሆን በዚህ ህግ መሰረት ኢየሱስ ክርስቶስ እና ደቀመዛሙርቶቹ እንኳ ለቄሳር ግብር እንዲከፍሉ ተጠይቀው ሲከፍሉ ተጽፎ እናነባለን። በተለይ ሁሉም የፕሮቴስታንት የመንግስት ደጋፊ ቤተክርስትያኖች እንደሚያስተምሩት ነፍስ ሁሉ በበላይ ላሉት ባለ ሥልጣኖች ይገዛ።ከእግዚአብሔር ካልተገኘ በቀር ሥልጣን የለምና፤ ያሉትም ባለ ሥልጣኖች በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው።” የሚለውን ቃል እንደወረደ የምንጠቀምበት ከሆነ ሰዶማዊ መሆን ግዴታችን ይሆን ነበር ማለት ነው! መጥመቁ ዮሐንስ ስለ እውነት የሄሮድስን ክፉ ስራ ስለተቃወመ አንገቱ እንደተቆረጠ ተጽፎ እባነባለን። በዚህ ዘመን ያሉም የቤተክርስትያን አስተማሪዎች እውነት ተናግረን አንገታችን እንደ መጥምቁ ዮሐንስ ከሚቀላ የእግዚያብሔርን ቃል ባለስልጣኖቹ እንደሚፈልጉት አስተምረን የእነርሱ ወዳጅ ብንሆን ይሻላል ብለው ያመኑ ይመስላል። ነገር ግን ሐሰተኞች ነቢያት ደግሞ በሕዝቡ መካከል ነበሩ እንዲሁም በመካከላችሁደግሞ ሐሰተኞች አስተማሪዎች ይሆናሉ፤ እነርሱም የዋጃቸውን ጌታ እንኳ ክደው የሚፈጥንን ጥፋት በራሳቸው ላይ እየሳቡየሚያጠፋ ኑፋቄን አሹልከው ያገባሉ፤ ብዙዎችም በመዳራታቸው ይከተሉአቸዋል በእነርሱም ጠንቅ የእውነት መንገድይሰደባል። ገንዘብንም በመመኘት በተፈጠረ ነገር ይረቡባችኋል፤ ፍርዳቸውም ከጥንት ጀምሮ አይዘገይም ጥፋታቸውምአያንቀላፋም።” 2 ጴጥ 2:1-3 በመጽሐፍ ቅዱሳችን በምሳሌ መጽሐፍ ውስጥ በብዙ ክፍል ክፉ የሚሰሩትን ግፈኞች ደፍሮ መገሰጽ እንደሚያስፈልግ እንዲህ በማለት ይናገራል፦ የተገለጠ ዘለፋ ከተሰወረ ፍቅር ይሻላል።” ምሳ 27፡5  “ሰውንመፍራት ወጥመድ ያመጣል፤ በእግዚአብሔር የሚታመን ግን እርሱ ይጠበቃል።”ምሳ 29፡25  በተጨማሪ የትኛውም በክፉ የግፍ ሀጢያት ስራ የተሰማራ ግለሰብ ሆነ የመንግስት ማንኛውም ባለስልጣንም ሆነ የታወቀ የቤተክርስትያን መሪ ከእኩይ ተግባሩ እንዲታረም እንዲሁም ንስሀ እንዲገባ በግልጽ ሊነገረው እንደሚያስፈልግ ባይነገረው ግን እና በሀጢያቱ ምክንያት ቢሞት ሁላችንም ተጠያቂዎች እንደሆንን መጽሐፍ ቅዱሳችን እንዲህ በማለት አስጠንቅቆ ያስተምረናል፦ የአፌን ቃል ስማ ከእኔምዘንድ አስጠንቅቃቸው። እኔ ኃጢአተኛውን። በእርግጥ ትሞታለህ ባልሁት ጊዜ፥ አንተም ባታስጠነቅቀው ነፍሱም እንድትድንከክፉ መንገዱ ይመለስ ዘንድ ለኃጢአተኛው አስጠንቅቀህ ባትነግረው፥  ኃጢአተኛ በኃጢአት ይሞታል፤ ደሙን ግን ከእጅህእፈልጋለሁ። ነገር ግን አንተ ኃጢአተኛውን ብታስጠነቅቅ እርሱም ከኃጢአቱና ከክፉ መንገዱ ባይመለስ፥ በኃጢአቱይሞታል፥ አንተ ግን ነፍስህን አድነሃል። ደግሞ ጻድቁ ከጽድቁ ተመልሶ ኃጢአት በሠራ ጊዜ እኔ በፊቱም ዕንቅፋትን ሳደርግ፥እርሱ ይሞታል፤ አንተም አላስጠነቀቅኸውምና በኃጢአቱ ይሞታል ያደረጋትም ጽድቅ ነገር አትታሰብለትም፤ ደሙን ግንከእጅህ እፈልጋለሁ።ነገር ግን ኃጢአት እንዳይሠራ ጻድቁን ብታስጠነቅቅ እርሱም ኃጢአት ባይሠራ፥ ተጠንቅቆአልና በእርግጥበሕይወት ይኖራል፤ አንተም ነፍስህን አድነሃል።” ሕዝ 3:1721
መጽሐፍ ቅዱስ ስላለንበት የመጨረሻ ዘመን ምን ይለናል?
የእግዚያብሔር እውነተኛ የነጠረ ቃል የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ አለም ሳይፈጠር ጀምሮ እስከ አለም ፍጻሜ ከዚያም ቡኋላ ያሉ ኩነቶች በሙሉ አንድ በአንድ በጥልቀት እና በስፋት በግልጽ የሚዳስስልን ሲሆን ከእኛ የሚጠበቀው በጽሞና እና በረጋ መንፈስ በጥንቃቄ እያነበብን እንዲፈታልን የምንፈልገውን ነገሮች የያዘውን ክፍል ለማግኘት ኢንተርኔት ላይ የሚገኝ የመጽሐፍ ቅዱስ ማጣቀሻ ማውጫ መጠቀም እጅግ ተመራጭ ነው። ምክንያቱም 1ኛ የኢንተርኔት መልስ በጣም ፈጣን ነው። 2ኛ በኢንተርኔት አማካኝነት የብዙ የእግዚያብሔር ሰዎችን ከተለያየ አቅጣጫ ለአንድ ጥያቄ ብዙ አማራጭ መልሶች በቀላሉ ማግኘት ይቻላል። 3ኛው እና ዋናው ስለመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን ለማወቅ በአቅራቢያዎ ምንም የሚረዳዎት ሰው ከሌለ የኢንተርኔት መረጃ ጥሩ ተመራጭ መፍትሄ ነው። ስላለንበት ግዜ የሚነግሩንን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ሁሉ ጠንቅቀን ካወቅን መጽሐፍ ቅዱስን እያነበብን እና የአለማችንን ፓለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ክስተቶችን ከተለያዩ አቅጣጫዎች የምናገኘውን መረጃ (ቤተክርስትያን የሚደረጉትንም ድርጊቶች ሁሉ ይጨምራል) መሰረት ያለንበትን ግዜ እና ሰአቱን ማወቅ እንችላለን።
ስለሆነም ከቤተክርስትያን እንኳ ብንጀምር የእግዚያብሔር ስም የሚጠራባት ቤተክርስትያን እና አገልጋዮች በምን ሁናቴ ላይ እንዳሉ ምልክቶቹን ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስናነብ እና እየተደረገ ያለውን ነገር ማለትም ያየነውን እና የሰማነውን ነገሮች ስናስተያይ ቤተክርስትያን ያለችበትን ሁኔታ እና ግዜው ሰአቱን በግልጽ እናውቃለን፦
የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውሥጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ።ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ። ከእሾህ ወይን ከኩርንችትስ በለስ ይለቀማልንእንዲሁ መልካም ዛፍ ሁሉ መልካም ፍሬያደርጋል፥ ክፉም ዛፍ ክፉ ፍሬ ያደርጋል። መልካም ዛፍ ክፉ ፍሬ ማፍራት፥ ወይም ክፉ ዛፍ መልካም ፍሬ ማፍራትአይቻለውም።” ማቴ 7:15_18
ስለዚህም ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ። በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም። በዚያ ቀን ብዙዎች። ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢትአልተናገርንምን፥ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን፥ በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምንይሉኛል። የዚያን ጊዜም።ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ።” ማቴ 7:20_27
እንደ እነዚህ ያሉ ሰዎች የክርስቶስን ሐዋርያት እንዲመስሉ ራሳቸውን እየለወጡ፥ ውሸተኞች ሐዋርያትና ተንኮለኞችሠራተኞች ናቸውና። ይህም ድንቅ አይደለም፤ ሰይጣን ራሱ የብርሃንን መልአክ እንዲመስል ራሱን ይለውጣልና። እንግዲህአገልጋዮቹ ደግሞ የጽድቅን አገልጋዮች እንዲመስሉ ራሳቸውን ቢለውጡ ታላቅ ነገር አይደለም፤ ፍጻሜአቸውም እንደሥራቸው ይሆናል።” 2 ቆሮ 1113_15
ነገር ግን ሐሰተኞች ነቢያት ደግሞ በሕዝቡ መካከል ነበሩ እንዲሁም በመካከላችሁ ደግሞ ሐሰተኞች አስተማሪዎች ይሆናሉ፤እነርሱም የዋጃቸውን ጌታ እንኳ ክደው የሚፈጥንን ጥፋት በራሳቸው ላይ እየሳቡ የሚያጠፋ ኑፋቄን አሹልከው ያገባሉ፤ብዙዎችም በመዳራታቸው ይከተሉአቸዋል በእነርሱም ጠንቅ የእውነት መንገድ ይሰደባል። ገንዘብንም በመመኘት በተፈጠረነገር ይረቡባችኋል፤ ፍርዳቸውም ከጥንት ጀምሮ አይዘገይም ጥፋታቸውም አያንቀላፋም።” 2 ጴጥ 2:1_3
እግዚአብሔርን እንዲያውቁ በግልጥ ይናገራሉ፥ ዳሩ ግን የሚያስጸይፉና የማይታዘዙ ለበጎ ሥራም ሁሉ የማይበቁ ስለ ሆኑ፥በሥራቸው ይክዱታል።” ቲቶ 1:16
ኑሮዬ ይበቃኛል ለሚለው ግን እግዚአብሔርን መምሰል እጅግ ማትረፊያ ነው፤ ወደ ዓለም ምንም እንኳ አላመጣንምና፥አንዳችንም ልንወስድ አይቻለንም፤ ምግብና ልብስ ከኖረን ግን፥ እርሱ ይበቃናል። ዳሩ ግን ባለ ጠጎች ሊሆኑ የሚፈልጉበጥፋትና በመፍረስ ሰዎችን በሚያሰጥምና በሚያሰንፍ በሚጎዳም በብዙ ምኞትና በፈተና በወጥመድም ይወድቃሉ። ገንዘብንመውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነውና፥ አንዳንዶች ይህን ሲመኙ፥ ከሃይማኖት ተሳስተው በብዙ ሥቃይ ራሳቸውን ወጉ። አንተግን፥ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፥ ከዚህ ሽሽ፤ ጽድቅንና እግዚአብሔርን መምሰል እምነትንም ፍቅርንም መጽናትንምየዋህነትንም ተከታተል።” 1 ጢሞ 6:6_11
ፍርድ ከእግዚአብሔር ቤት ተነሥቶ የሚጀመርበት ጊዜ ደርሶአልና፤ አስቀድሞም በእኛ የሚጀመር ከሆነ ለእግዚአብሔርወንጌል የማይታዘዙ መጨረሻቸው ምን ይሆንጻድቅም በጭንቅ የሚድን ከሆነ ዓመፀኛውና ኃጢአተኛው ወዴት ይታይዘንድ አለው?” 1 ጴጥ 4:17-18
ከሴሰኞች ጋር እንዳትተባበሩ በመልእክቴ ጻፍሁላችሁ። በጠቅላላው የዚህን ዓለም ሴሰኞችን፥ ወይም ገንዘብን የሚመኙትንነጣቂዎችንም፥ ወይም ጣዖትን የሚያመልኩትን አላልሁም፤ ይህስ ቢሆን ከዓለም ልትወጡ ይገባችሁ ነበር። አሁን ግንወንድሞች ከሚባሉት አንዱ ሴሰኛ ወይም ገንዘብን የሚመኝ ወይም ጣዖትን የሚያመልክ ወይም ተሳዳቢ ወይም ሰካር ወይምነጣቂ ቢሆን ከእርሱ ጋር እንዳትተባበሩ እጽፍላችኋለሁ፤ እንደነዚህ ካለው ጋር መብል እንኳን አትብሉ። በውጭ ባሉ ሰዎችላይ መፍረድ ምን አግዶኝ? በውስጥ ባሉ ሰዎች ላይ እናንተ አትፈርዱምን? በውጭ ባሉቱ ግን እግዚአብሔርይፈርድባቸዋል። ክፉውን ከመካከላችሁ አውጡት።” 1 ቆሮ 5:9_13
እናንተ ትበድላላችሁ ታታልሉማላችሁ፥ ያውም ወንድሞቻችሁን። ወይስ ዓመፀኞች የእግዚአብሔርን መንግሥትእንዳይወርሱ አታውቁምን? አትሳቱ፤ ሴሰኞች ቢሆን ወይም ጣዖትን የሚያመልኩ ወይም አመንዝሮች ወይም ቀላጮችወይም ከወንድ ጋር ዝሙት የሚሠሩ ወይም ሌቦች ወይም ገንዘብን የሚመኙ ወይም ሰካሮች ወይም ተሳዳቢዎች ወይምነጣቂዎች የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።” 1 ቆሮ 6:8_10
ራሳቸው የጥፋት ባሪያዎች ሆነው። አርነት ትወጣላችሁ እያሉ ተስፋ ይሰጡአቸዋል፤ ሰው ለተሸነፈበት ለእርሱ ተገዝቶ ባሪያነውና። በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት ከዓለም ርኵሰት ካመለጡ በኋላ ዳግመኛ በእርስዋተጠላልፈው የተሸነፉ ቢሆኑ፥ ከፊተኛው ኑሮአቸው ይልቅ የኋለኛው የባሰ ሆኖባቸዋል። አውቀዋት ከተሰጣቸው ከቅድስትትእዛዝ ከሚመለሱ የጽድቅን መንገድ ባላወቋት በተሻላቸው ነበርና። ውሻ ወደ ትፋቱ ይመለሳል፥ ደግሞ። የታጠበች እርያበጭቃ ለመንከባለል ትመለሳለች እንደሚባል እውነተኞች ምሳሌዎች ሆኖባቸዋል።” 2 ጴጥ 2:19_22
ፍሬም ከሌለው ከጨለማ ሥራ ጋር አትተባበሩ፥ ይልቁን ግለጡት እንጂ፥ እነርሱ በስውር ስለሚያደርጉት መናገር እንኳነውር ነውና፤ ሁሉ ግን በብርሃን ሲገለጥ ይታያል፤ የሚታየው ሁሉ ብርሃን ነውና። ኤፌ 5:11_12
ራሳችንን ብንመረምር ግን ባልተፈረደብንም ነበር፤ ነገር ግን በተፈረደብን ጊዜ ከዓለም ጋር እንዳንኮነን በጌታእንገሠጻለን።”    1 ቆሮ 11:31_32
ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፥ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም። በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅርሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው። ኃጢአትን አላደረግንም ብንል ሐሰተኛ እናደርገዋለን ቃሉም በእኛውስጥ የለም።” 1 ዮሐ 1:8_10
ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል፤ አንተም እውቀትን ጠልተሃልና እኔ ካህን እንዳትሆነኝ እጠላሃለሁ፤የአምላክህንም ሕግ ረስተሃልና እኔ ደግሞ ልጆችህን እረሳለሁ። እንደ ብዛታቸው መጠን ኃጢአት ሠሩብኝ፤ እኔም ክብራቸውንወደ ነውር እለውጣለሁ።” ትንቢተ ሆሴ 4:6_7
ምድር ከአመንዝሮች ተሞልታለችና፥ ከመርገምም የተነሣ ምድር አልቅሳለች፤ የምድረ በዳ ማሰማርያ ደርቆአል፤ አካሄዳቸውክፉ ነው፥ ብርታታቸውም ቅን አይደለም። ነቢዩና ካህኑም ረክሰዋልና፥ በቤቴም ውስጥ ክፋታቸውን አግኝቻለሁ፥ ይላልእግዚአብሔር። ስለዚህ መንገዳቸው በጨለማ እንዳለች እንደ ድጥ ስፍራ ትሆንባቸዋለች፥ እነርሱም ፍግምግም ብለውይወድቁባታል፤ እኔም በምጐበኛቸው ዓመት ክፉ ነገርን አመጣባቸዋለሁና፥ ይላል እግዚአብሔር።” ኤር 23:10_12
የሰው ልጅ ሆይ፥ ትንቢት ተናገር፥ በእስራኤል እረኞች ላይ ትንቢት ተናገር፥ እረኞችንም እንዲህ በላቸው። ጌታእግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ራሳቸውን ለሚያሰማሩ ለእስራኤል እረኞች ወዮላቸውእረኞች በጎችን ያሰማሩ ዘንድአይገባቸውምንጮማውን ትበላላችሁ ጠጕሩንም ትለብሳላችሁ፥ የወፈሩትን ታርዳላችሁ፤ በጎቹን ግን አታሰማሩም።የደከመውን አላጸናችሁትም የታመመውንም አላከማችሁትም የተሰበረውንም አልጠገናችሁትም የባዘነውንምአልመለሳችሁትም የጠፋውንም አልፈለጋችሁትም በኃይልና በጭቈናም ገዛችኋቸው። እረኛንም በማጣት ተበተኑ፥ ለምድርምአራዊት ሁሉ መብል ሆኑ፥ ተበተኑም። በጎቼ በተራሮች ሁሉና በረዘሙ ኮረብቶች ሁሉ ላይ ተቅበዝብዘዋል፥ በጎቼም በምድርፊት ሁሉ ላይ ተበትነዋል፤ የሚሻም የሚፈልግም አልነበረም። ስለዚህ፥ እረኞች ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤  ጌታእግዚአብሔር እንዲህ ይላል። እኔ ሕያው ነኝና እረኛ ስለሌለ እረኞቼም በጎቼን ስላልፈለጉ እረኞችም ራሳቸውን እንጂ በጎቼንስላላሰማሩ፥ በጎቼ ንጥቂያ ሆነዋልና፥ በጎቼም ለምድር አራዊት ሁሉ መብል ሆነዋልና::” ሕዝ 34:2_8
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። እናንተም መንጋዬ ሆይ፥ እነሆ፥ በበግና በበግ መካከል፥ በአውራ በግና በአውራ ፍየልምመካከል፥ እፈርዳለሁ። የቀረውን ማሰማርያችሁን በእግራችሁ የረገጣችሁት፥ በመልካሙ ማሰማርያ መሰማራታችሁባይበቃችሁ ነውን? የቀረውንስ ውኃ በእግራችሁ ያደፈረሳችሁት፥ ጥሩውን ውኃ መጠጣታችሁ ባይበቃችሁ ነውን? በጎቼምበእግራችሁ በረገጣችሁት ይሰማራሉ በእግራችሁም ያደፈረሳችሁትን ይጠጣሉ። ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህይላቸዋል። እነሆ፥ እኔ በወፈሩት በጎችና በከሱት በጎች መካከል እፈርዳለሁ። እስክትበትኑአቸው ድረስ በእንቢያና በትከሻስለምትገፉአቸው የደከሙትንም ሁሉ በቀንዳችሁ ስለምትወጉአቸው፥ ስለዚህ መንጋዬን አድናለሁ፥ ከእንግዲህ ወዲህምንጥቂያ አይሆኑም፤ በበግና በበግ መካከልም እፈርዳለሁ።” ሕዝ 34:17_22
እነሆ፥ በምድር ላይ ራብን የምሰድድበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ እርሱም የእግዚአብሔርን ቃልከመስማት እንጂ እንጀራን ከመራብና ውኃን ከመጠማት አይደለም። ከባሕርም እስከ ባሕር ድረስ፥ ከሰሜንም እስከ ምሥራቅድረስ ይቅበዘበዛሉ፤ የእግዚአብሔርን ቃል ለመሻት ይርዋርዋጣሉ፥ አያገኙትምም። በዚያ ቀን መልካካሞች ደናግልጐበዛዝትም በጥም ይዝላሉ።” አሞ 8:11_13
 “የአፌን ቃል ስማ ከእኔም ዘንድ አስጠንቅቃቸው። እኔ ኃጢአተኛውን። በእርግጥ ትሞታለህ ባልሁት ጊዜ፥ አንተምባታስጠነቅቀው ነፍሱም እንድትድን ከክፉ መንገዱ ይመለስ ዘንድ ለኃጢአተኛው አስጠንቅቀህ ባትነግረው፥  ኃጢአተኛበኃጢአት ይሞታል፤ ደሙን ግን ከእጅህ እፈልጋለሁ። ነገር ግን አንተ ኃጢአተኛውን ብታስጠነቅቅ እርሱም ከኃጢአቱናከክፉ መንገዱ ባይመለስ፥ በኃጢአቱ ይሞታል፥ አንተ ግን ነፍስህን አድነሃል። ደግሞ ጻድቁ ከጽድቁ ተመልሶ ኃጢአት በሠራጊዜ እኔ በፊቱም ዕንቅፋትን ሳደርግ፥ እርሱ ይሞታል፤ አንተም አላስጠነቀቅኸውምና በኃጢአቱ ይሞታል ያደረጋትም ጽድቅነገር አትታሰብለትም፤ ደሙን ግን ከእጅህ እፈልጋለሁ።ነገር ግን ኃጢአት እንዳይሠራ ጻድቁን ብታስጠነቅቅ እርሱም ኃጢአትባይሠራ፥ ተጠንቅቆአልና በእርግጥ በሕይወት ይኖራል፤ አንተም ነፍስህን አድነሃል።” ሕዝ 3:17_21
እንዲሁም ስላለንበት የመጨረሻው ዘመን አገራችን ኢትዮጵያን ጨምሮ ስለአለም አጠቃላይ የፓለቲካ እና የኢኮኖሚ ሁኔታ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን እያነበብን እና የግዜውን የፓለቲካዊ፣የኢኮኖሚያዊ እና የማህበራዊ ድርጊቶችን ከተለያዩ አቅጣጫዎች ከምናገኛቸው መረጃዎች ጋር እያመሳከርን የደረስንበትን ዘመን እና ሰአቱን ለማወቅ እንችላለን፦
ምድር ደም ባመጣው በደል፥ ከተማም በግፍ ተሞልታለችና ሰንሰለት ሥራ። ከአሕዛብ ዘንድ ከሁሉ የሚከፉትን አመጣለሁቤቶቻቸውንም ይወርሳሉ፤ የኃያላንንም ትዕቢት አጠፋለሁ፥ መቅደሶቻቸውም ይረክሳሉ። ጥፋት መጥቶአል፤ ሰላምም ይሻሉእርሱም አይገኝም። ድንጋጤ በድንጋጤ ላይ ይመጣል፥ ወሬም ወሬውን ይከተላል፥ ከነቢዩም ዘንድ ራዕይን ይሻሉ፤ ከካህኑምዘንድ ትምህርት፥ ከሽማግሌዎችም ዘንድ ምክር ይጠፋል። ንጉሡም ያለቅሳል፥ አለቃም ውርደትን ይለብሳል፥ የምድርምሕዝብ እጅ ትንቀጠቀጣለች፤ እንደ መንገዳቸውም መጠን አደርግባቸዋለሁ፥ በፍርዳቸውም መጠን እፈርድባቸዋለሁ፤ እኔምእግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።” ትንቢተ ሕዝቅኤል 7:23-27
 “ክፉውን መልካም መልካሙን ክፉ ለሚሉ፥ ጨለማውን ብርሃን ብርሃኑንም ጨለማ ለሚያደርጉ፥ ጣፋጩን መራራመራራውንም ጣፋጭ ለሚያደርጉ ወዮላቸው!  በዓይናቸው ጥበበኞች በነፍሳቸውም አስተዋዮች ለሆኑ ወዮላቸው! የወይንጠጅ ለመጠጣት ኃያላን የሚያሰክረውንም ለማደባለቅ ጨካኞች ለሆኑ፤ በደለኛውን ስለ ጉቦ ጻድቅ ለሚያደርጉ፥ የጻድቁንምጽድቅ ለሚያስወግዱበት ወዮላቸው!” ኢሳ 5:20_23
የእግዚአብሔር ቀን ቅርብ ነው፥ የደመና ቀን፥ የአሕዛብ ጊዜ ይሆናል። ሰይፍ በግብጽ ላይ ይመጣል፥ ሁከትም በኢትዮጵያይሆናል፤ የተገደሉትም በግብጽ ውስጥ ይወድቃሉ፥ ብዛትዋንም ይወስዳሉ፥ መሠረትዋም ይፈርሳል። ኢትዮጵያና ፉጥ ሉድምየተደባለቀም ሕዝብ ሁሉ ኩብም ቃል ኪዳንም የገባችው ምድር ልጆች ከእነርሱ ጋር በሰይፍ ይወድቃሉ። እግዚአብሔርእንዲህ ይላል። ግብጽን የሚደግፉ ይወድቃሉ፥ የኃይልዋም ትዕቢት ይወርዳል፤ ከሚግዶል ጀምሮ እስከ ሴዌኔ ድረስ በእርስዋውስጥ በሰይፍ ይወድቃሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። ባድማም በሆኑ አገሮች መካከል ባድማ ይሆናሉ፥ ከተሞችዋም በፈረሱከተሞች መካከል ይሆናሉ።እሳትንም በግብጽ ባነደድሁ ጊዜ ረዳቶችዋም ሁሉ በተሰበሩ ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁያውቃሉ።” ሕዝ 30:3-8
ቆመ፥ ምድርንም አወካት፤ ተመለከተ፥ አሕዛብንም አናወጠ፤ የዘላለምም ተራሮች ተቀጠቀጡ፥ የዘላለምም ኮረብቶችቀለጡ፤ መንገዱ ከዘላለም ነው። የኢትዮጵያ ድንኳኖች ሲጨነቁ አየሁ፤ የምድያም አገር መጋረጃዎች ተንቀጠቀጡ።”እንባቆም 3:5-7
አምባውም እንዲፈርስ በብርቱ ላይ የድንገት ጥፋት የሚያመጣውን ፈልጉ፤ ስሙ እግዚአብሔር ነው።በበሩ አደባባይየሚገሥጸውን ጠሉ፥ እውነትም የሚናገረውን ተጸየፉ። ድሀውንም ደብድባችኋልና፥ የስንዴውንም ቀረጥ ከእርሱወስዳችኋልና ከተጠረበ ድንጋይ ቤቶችን ሠርታችኋል፥ ነገር ግን አትቀመጡባቸውም፤ ያማሩ የወይን ቦታዎች ተክላችኋል፥ነገር ግን ከወይን ጠጃቸው አትጠጡም። ጻድቁን የምታስጨንቁ፥ ጉቦንም የምትቀበሉ፥ በበሩም አደባባይ የችጋረኛውን ፍርድየምታጣምሙ እናንተ ሆይ፥ በደላችሁ እንዴት እንደ በዛ፥ ኃጢአታችሁም እንዴት እንደ ጸና እኔ አውቃለሁና።ስለዚህ ክፉዘመን ነውና በዚያ ዘመን አስተዋይ የሚሆን ዝም ይላል።በሕይወት ትኖሩ ዘንድ መልካሙን እንጂ ክፉውን አትፈልጉ፤እንዲህም እናንተ እንደ ተናገራችሁ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሆናል። ክፉውን ጥሉ፥ መልካሙንምውደዱ፥ በበሩም አደባባይ ፍርድን አጽኑ፤ ምናልባት የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ለዮሴፍ ቅሬታ ይራራ ይሆናል። ስለዚህጌታ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። በየአደባባዩ ሁሉ ላይ ዋይታ ይሆናል፤ በየመንገዱም ሁሉ ላይ ወዮ ወዮይባላል፤ ገበሬዎቹም ወደ ልቅሶ፥ አልቃሾቹም ወደ ዋይታ ይጠራሉ። በመካከልህ አልፋለሁና በወይኑ ቦታ ሁሉ ልቅሶይሆናል፥ ይላል እግዚአብሔር።የእግዚአብሔርን ቀን ለምትፈልጉ ወዮላችሁ! የእግዚአብሔርን ቀን ለምን ትፈልጋላችሁ?ጨለማ ነው እንጂ ብርሃን አይደለም። ከአንበሳ ፊት እንደ ሸሸ ድብም እንዳገኘው ሰው፥ ወይም ወደ ቤት ገብቶ እጁንበግድግዳ ላይ እንዳስደገፈና እባብ እንደ ነደፈው ሰው ነው። የእግዚአብሔር ቀን ብርሃን ሳይሆን ጨለማ አይደለምን? ፀዳልየሌለውም ድቅድቅ ጨለማ አይደለምን?ዓመት በዓላችሁን ጠልቼዋለሁ ተጸይፌውማለሁ፤ የተቀደሰውም ጉባኤአችሁ ደስአያሰኘኝም። የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁና የእህሉን ቍርባናችሁን ብታቀርቡልኝም እንኳ አልቀበለውም፤ ለምስጋናመሥዋዕት የምታቀርቡልኝን የሰቡትን እንስሶች አልመለከትም። የዝማሬህንም ጩኸት ከእኔ ዘንድ አርቅ፤ የመሰንቆህንም ዜማአላደምጥም። ነገር ግን ፍርድ እንደ ውኃ፥ ጽድቅም እንደማይደርቅ ፈሳሽ ይፍሰስ።” ሕዝ5:9-24
እርሱም በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፥ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው። ንገረን፥ ይህ መቼ ይሆናል?የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድር ነውአሉት።ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው። ማንም እንዳያስታችሁተጠንቀቁ።ብዙዎች። እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፤ ብዙዎችንም ያስታሉ።ጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰሙ ዘንድአላችሁ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠበቁ፥ አትደንግጡ፤ ዳሩ ግን መጨረሻው ገና ነው።ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትምበመንግሥት ላይ ይነሣልና፥ ራብም ቸነፈርም የምድርም መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል፤ እነዚህም ሁሉ የምጥ ጣርመጀመሪያ ናቸው። በዚያን ጊዜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጡአችኋል ይገድሉአችሁማል፥ ስለ ስሜም በአሕዛብ ሁሉ የተጠላችሁትሆናላችሁ። በዚያን ጊዜም ብዙዎች ይሰናከላሉ እርስ በርሳቸውም አሳልፈው ይሰጣጣሉ እርስ በርሳቸውም ይጣላሉ፤ብዙሐሰተኞች ነቢያትም ይነሣሉ ብዙዎችንም ያስታሉ፤ ከዓመፃም ብዛት የተነሣ የብዙ ሰዎች ፍቅር ትቀዘቅዛለች።እስከ መጨረሻየሚጸና ግን እርሱ ይድናል።” ማቴ24፡3-13
እነርሱም። መምህር ሆይ፥ እንግዲህ ይህ መቼ ይሆናልይህስ ይሆን ዘንድ እንዳለው ምልክቱ ምንድር ነውብለውጠየቁት። እንዲህም አለ። እንዳትስቱ ተጠንቀቁ፤ ብዙዎች። እኔ ነኝ፥ ዘመኑም ቀርቦአል እያሉ በስሜ ይመጣሉና፤ እነርሱንተከትላችሁ አትሂዱ። ጦርንና ሁከትንም በሰማችሁ ጊዜ አትደንግጡ፤ ይህ አስቀድሞ ይሆን ዘንድ ግድ ነውና፥ ነገር ግንመጨረሻው ወዲያው አይሆንም።በዚያን ጊዜ እንዲህ አላቸው። ሕዝብ በሕዝብ ላይ፥ መንግሥትም በመንግሥት ላይይነሣል፤ታላቅም የምድር መናወጥና በልዩ ልዩ ስፍራ ቸነፈር ራብም ይሆናል፤ የሚያስፈራም ነገር ከሰማይም ታላቅ ምልክትይሆናል።” ሉቃ 21:7-11
ነገር ግን በመጨረሻው ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን እንዲመጣ ይህን እወቅ።ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ ይሆናሉና፥ ገንዘብንየሚወዱ፥ ትምክህተኞች፥ ትዕቢተኞች፥ ተሳዳቢዎች፥ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥ የማያመሰግኑ፥ ቅድስና የሌላቸው፥ ፍቅርየሌላቸው፥ ዕርቅን የማይሰሙ፥ ሐሜተኞች፥ ራሳቸውን የማይገዙ፥ ጨካኞች፥ መልካም የሆነውን የማይወዱ፥ ከዳተኞች፥ችኩሎች፥ በትዕቢት የተነፉ፥ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ ይሆናሉ፤ የአምልኮት መልክ አላቸው ኃይሉን ግንክደዋል፤ ከእነዚህ ደግሞ ራቅ።” 2ጢሞ3:1_5
 “አንድም አውሬ ከባሕር ሲወጣ አየሁ፤ አሥር ቀንዶችና ሰባት ራሶች ነበሩት፥ በቀንዶቹም ላይ አሥር ዘውዶች በራሶቹም ላይየስድብ ስም ነበረ።ያየሁትም አውሬ ነብር ይመስል ነበር፥ እግሮቹም እንደ ድብ እግሮች፥ አፉም እንደ አንበሳ አፍ ነበሩ።ዘንዶውም ኃይሉንና ዙፋኑን ትልቅም ሥልጣን ሰጠው።ከራሶቹም ለሞት እንደ ታረደ ሆኖ አንዱን አየሁ፥ ለሞቱ የሆነውምቍስል ተፈወሰ። ምድርም ሁሉ አውሬውን እየተከተለ ተደነቀ፥ለዘንዶውም ሰገዱለት፥ ለአውሬው ሥልጣንን ሰጥቶታልና፤ለአውሬውም። አውሬውን ማን ይመስለዋል፥ እርሱንስ ሊዋጋ ማን ይችላል? እያሉ ሰገዱለት።ታላቅንም ነገርና ስድብንየሚናገርበት አፍ ተሰጠው፥ በአርባ ሁለት ወርም እንዲሠራ ሥልጣን ተሰጠው።እግዚአብሔርንም ለመሳደብ ስሙንናማደሪያውንም በሰማይም የሚያድሩትን ሊሳደብ አፉን ከፈተ።ቅዱሳንንም ይዋጋ ዘንድ ድልም ያደርጋቸው ዘንድ ተሰጠው፥በነገድና በወገንም በቋንቋም በሕዝብም ሁሉ ላይ ሥልጣን ተሰጠው። ከዓለምም ፍጥረት ጀምሮ በታረደው በግ ሕይወትመጽሐፍ ስሞቻቸው ያልተጻፉ በምድር የሚኖሩ ሁሉ ይሰግዱለታል። ጆሮ ያለው ቢኖር ይስማ። ይማረክ ዘንድ ያለው ማንምቢኖር ወደ ምርኮነት ይሄዳል፤ በሰይፍ የሚገድል ማንም ቢኖር ራሱ በሰይፍ እንዲገደል ይገባዋል። የቅዱሳን ትዕግሥትናእምነት በዚህ ነው። ሌላም አውሬ ከምድር ሲወጣ አየሁ፥ የበግ ቀንዶችን የሚመስሉ ሁለት ቀንዶችም ነበሩት እንደ ዘንዶምይናገር ነበር። በፊተኛውም አውሬ ሥልጣን በእርሱ ፊት ሁሉን ያደርጋል። ለሞቱ የሆነውም ቍስል ተፈወሰለት ለፊተኛውአውሬ ምድርና በእርሱ የሚኖሩት እንዲሰግዱለት ያደርጋል። እሳትንም እንኳ ከሰማይ ወደ ምድር በሰው ፊት እስኪያወርድድረስ ታላላቆችን ምልክቶች ያደርጋል።በአውሬውም ፊት ያደርግ ዘንድ ከተሰጡት ምልክቶች የተነሣ በምድር የሚኖሩትንያስታል፤ የሰይፍም ቍስል ለነበረውና በሕይወት ለኖረው ለአውሬው ምስልን እንዲያደርጉ በምድር የሚኖሩትን ይናገራል።የአውሬው ምስል ሊናገር እንኳ ለአውሬውም ምስል የማይሰግዱለትን ሁሉ ሊያስገድላቸው፥ ለአውሬው ምስል ትንፋሽእንዲሰጠው ተሰጠው። ታናናሾችና ታላላቆችም ባለ ጠጋዎችና ድሆችም ጌታዎችና ባሪያዎችም ሁሉ በቀኝ እጃቸው ወይምበግምባራቸው ምልክትን እንዲቀበሉ፥ የአውሬውም ስም ወይም የስሙ ቍጥር ያለው ምልክት የሌለበት ማንም ሊገዛ ወይምሊሸጥ እንዳይችል ያደርጋል። ጥበብ በዚህ አለ። አእምሮ ያለው የአውሬውን ቍጥር ይቍጠረው፤ ቍጥሩ የሰው ቍጥርነውና፥ ቍጥሩም ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት ነው።” ራዕ 13
አንተ እጅግ የተወደድህ ነህና በልመናህ መጀመሪያ ላይ ትእዛዝ ወጥቶአል፥ እኔም እነግርህ ዘንድ መጥቻለሁ፤ አሁንም ነገሩንመርምር፥ ራእዩንም አስተውል። ዓመፃን ይጨርስ፥ ኃጢአትንም ይፈጽም፥ በደልንም ያስተሰርይ፥ የዘላለምን ጽድቅ ያገባ፥ራእይንና ትንቢትን ያትም፥ ቅዱሰ ቅዱሳኑንም ይቀባ ዘንድ በሕዝብህና በቅድስት ከተማህ ላይ ሰባ ሱባዔ ተቀጥሮአል።ስለዚህእወቅ አስተውልም፤ ኢየሩሳሌምን መጠገንና መሥራት ትእዛዙ ከሚወጣበት ጀምሮ እስከ አለቃው እስከ መሢሕ ድረስ ሰባትሱባዔና ስድሳ ሁለት ሱባዔ ይሆናል፤ እርስዋም በጭንቀት ዘመን ከጎዳናና ከቅጥር ጋር ትሠራለች። ከስድሳ ሁለት ጊዜ ሰባትምበኋላ መሢሕ ይገደላል፥ በእርሱም ዘንድ ምንም የለም፤ የሚመጣውም አለቃ ሕዝብ ከተማይቱንና መቅደሱን ያጠፋሉ፤ፍጻሜውም በጐርፍ ይሆናል፥ እስከ መጨረሻም ድረስ ጦርነት ይሆናል፤ ጥፋትም ተቀጥሮአል። እርሱም ከብዙ ሰዎች ጋርጽኑ ቃል ኪዳን ለአንድ ሱባዔ ያደርጋል፤ በሱባዔውም እኵሌታ መሥዋዕቱንና ቍርባኑን ያስቀራል፤ በርኵሰትም ጫፍ ላይአጥፊው ይመጣል፤ እስከ ተቈረጠውም ፍጻሜ ድረስ መቅሠፍት በአጥፊው ላይ ይፈስሳል።” 9:23-27
ወንድሞች ሆይ፥ ስለ ዘመናትና ስለ ወራት ምንም እንዲጻፍላችሁ አያስፈልጋችሁም፤የጌታ ቀን፥ ሌባ በሌሊት እንደሚመጣ፥እንዲሁ ይመጣ ዘንድ ራሳችሁ አጥብቃችሁ አውቃችኋልና።ሰላምና ደኅንነት ነው ሲሉ ያን ጊዜ ምጥ እርጕዝን እንደሚይዛትጥፋት በድንገት ይመጣባቸዋል ከቶም አያመልጡም።” 1 ተሰ 5:1-3
መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊምስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ።” ኤፌ 6:12
መደምደሚያ ፦ እኔ በዚህ ሰአት የእግዚያብሔር ቃል በግልጽ እንደሚናገረው እና በአለም ላይ እየተደረገ ያለውን ወደፊትም በቀጣይነት የሚደረጉትን ነገሮች ባጠቃላይ በጥልቀት በብዙ አቅጣጫ እና እውቀት ስመረምር እግዚያብሔር ረድቶኝ አንድ የመረዳት እውቀት ውሳኔ ላይ ደረስኩኝ እርሱም ምንድ ነው እኛ ሁላችን የመጨረሻ ዘመን ነዋሪዎች እንደሆንን አወኩኝ ስለሆነም በታላቁ ንጉስ እና ጠቢብ በሆነው በሰለሞን ቃል የዛሬው መልእክቴን እቋጫለሁ።
ፌዘኞች ከተማቸውን ያቃጥላሉ፤ ጠቢባን ግን ቍጣን ይመልሳሉ።” ምሳ 298
ደምን ለማፍሰስ የሚሹ ሰዎች ፍጹሙን ሰው ይጠላሉ፥ ደግሞም የቅኑን ሰው ነፍስ ይሻሉ።” ምሳ 2910
ሰውን መፍራት ወጥመድ ያመጣል፤ በእግዚአብሔር የሚታመን ግን እርሱ ይጠበቃል።”ምሳ 2925
ብዙ ሰዎች የሹምን ፊት ይሻሉ፤ የሰው ፍርድ ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።” ምሳ 2926
ብዙ ጊዜ ተዘልፎ አንገቱን ያደነደነ ድንገት ይሰበራል፥ ፈውስም የለውም።” ምሳ 291
ማራናታ!!!