Sunday, October 2, 2016

የ“ዲያብሎስ” አዲሱ የአለም መንግስት ስርአት ( New world order/ Illuminati ) በኢትዮጵያ

የ“ዲያብሎስ” አዲሱ የአለም መንግስት ስርአት ( New world order/ Illuminati ) በኢትዮጵያ
“እኛ ሁላችን ዋናውን የፓለቲካ፣የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ታላቅ ቀውስ በአለም ላይ እንዲከሰት እንፈልጋለን። ያኔ አገሮች አዲሱ የአለም መንግስት ስርአት ( New world order ) ይቀበሉታል” ግሎባሊስቱ መልቲ ቢሊየነር ዴቪድ ሮክፌለር
 አቤቱ፥ የተቀደስህ አምላኬ ሆይ፥ አንተ ከዘላለም ጀምሮ አልነበርህምንእኛ አንሞትም፤ አቤቱ፥ ለፍርድ ሠርተኸዋል፥ለተግሣጽም አድርገኸዋል።ዓይኖችህ ክፉ እንዳያዩ ንጹሐን ናቸው፥ ጠማምነትንም ትመለከት ዘንድ አትችልም፤ አታላዮችንስለምን ትመለከታለህኃጢአተኛውስ ከእርሱ ይልቅ ጻድቅ የሆነውን ሲውጠው ስለ ምን ዝም ትላለህ?ሰዎችንም እንደ ባሕርዓሣዎች፥ አለቃም እንደሌላቸው ተንቀሳቃሾች ለምን ታደርጋቸዋለህ?”ዕንባቆም1፡12-14

መስከረም 6,2009 ዓ.ም.
“ብሔራዊ ህብረተሰብን በመጠቀም እና አብዮት በማስነሳት አዲሱ የአለም መንግስት ስርአት ( New world order ) ይመሰረታል!” በአለም ላይ የማናቸውም ነገሮች ምክንያታዊ ጅማሬዎች መነሻ፣መድረሻ እና መጨረሻ ከበቂ ማስረጃዎች ጋር ያለው ሲሆን በዚህ አለም ላይ  ከሰው ልጅ አይምሮ እና አይን የተደበቀ እና የተሰወረ ምንም ነገር የለም። ስለሆነም ነገሮችን ሁሉ በጥልቀት ለማወቅ እና ዘለቄታዊ መፍትሄ ለማምጣት እያንዳንዱን ድርጊታዊ የተሰወረ ሴራን በጥልቀት እና በእውቀት መቆፈር ያስፈልጋል።
በአሁኑ ሰአት አገራችን ኢትዮጵያን ጨምሮ አለማችን ባጠቃላይ ማለት ይቻላል ከሌላው ግዜ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ እጅግ በከፋ ታላቅ አሰቃቂ የጥፋት ቀውስ በፓለቲካዊ፣በኢኮኖሚያዊ እና በማህበራዊ ኩነቶች በክፍኛ ሁናቴ እየታመሰች ትገኛለች። ሁሉም የአለም ህብረተሰብ ክፍል ሁሌም ለማለት ይቻላል ደጋግሞ የሚያወራው የተወራውን እና የተደረገውን መልሶ መላልሶ እንደገደል ማሚቶ ማስተጋባት እንጂ የተፈጸመውን እና እየተፈጸመ ያለውን ሁሉንም ነገሮች የተደበቀ የሽፍጥ ሴራዊ አጀንዳ ዋና ምክንያታቸውን ለማወቅ እና ወደ መፍትሄ ሀሳብ ለመድረስ በተለያየ የእውቀት መነጽር ተጠቅሞ ከውጭም ሆነ ከውስጥ አይቶ እና መርምሮ በማስረጃ በማስደገፍ ለባለድርሻ አካሉ ማድረስ እና ማስታወቅ አልተቻለም። እዚህ ላይ የነጮቹ የአይምሮአዊ የተፈጥሮ የምርመራ ልቀት ከእኛ ፊደላዊያን የሊህቃን እውቀት ጋር ሲነጻጸር ሰማይ ከምድር የሚርቀውን ያህል እጅግ በአስተሳሰብ እውቀት ተራርቀናል።
በእኛ በኢትዮጵያኖች ማህበረሰብ ዘንድ አንድ ድርጊት ሲፈጸም ስለተፈጸመው ነገር በመጀመሪያ ድርጊቱ መፈጸሙን ያወጀው አካልን ተከትሎ ያየውም ያላየውም፣የሰማውም ያልሰማውም የሆነውን ተቀብሎ ሁሉም ነገር እውነት ነው ብሎ ሳያመዛዝን በደመነፍስ አምኖ እርሱም በተራው ሌላውን ለማሳመን በተራው ያስተጋባል። ይሁን እንጂ ድርጊቱ የተፈጠረበት ዋናው ምክንያት ምንድር ነው? ከድርጊቱ መፈጸም ጀርባ ድብቅ አላማው ምንድር ነው? ከድርጊቱ መፈጸም ጀርባ የነማን እጆች አሉበት? ዋና አላማቸውስ ምንድ ነው? ከድርጊቱ መፈጸም በኋላ ምን ሊከሰት ይችላል? የመጨረሻ የድርጊቱ መፈጸም መደምደሚያው ምንድ ነው? በመጨረሻም የተፈጸመውን ድርጊት እና ፈጻሚውን እንዴት ነው መወገድ የሚችሉት? ይህንን ለማድረግስ በቂ ኅይል እና ድጋፍ ይገኛል ወይ? እነማን ናቸው ድጋፍ የሚያደርጉት? ምን ያህልስ ይታመናሉ?  ወዘተረፈ ተብሎ በፓለቲካዊ፣በኢኮኖሚያዊ እና በማህበራዊ ህይወት ቀውስ ዙሪያ የተፈጠሩ ድርጊቶችንና ጥፋቶችን በሙሉ ማንኛውንም ወሳኝ ቁልፍ ጥያቄዎችን መጠየቅ በእኛ ማህበረሰብ ውጉዝከመአርዮስ ነው። ለዚህም ነው ወንድማችን ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በአንድ መጣጥፉ ላይ “የጋማ ከብቶች ወሬ ነው” ያለውን ያስታውሰኛል። የአይምሮ ልሂቃኖችም “የማይጠይቅ ሰው ምንም ነገር አያውቅም” ብለው የሚናገሩት ለእዚህም ጭምር ይመስለኛል። በእኛ ማህበረሰብ ሙያዊ እውቀት እና አይምሮአዊ እውቀት ልዩነታቸው አይታወቅም። በእኛ ማህበረሰብ ሙያዊ እውቀት ማለትም እንደ ህክምና፣ኢንጂነሪንግ፣ስነጥበብ እና ሳይንሳዊ ቴክኖሎጂ የመሳሰሉት ባለሙያዎችን ሁሉንም ነገር ያውቃሉ። ለሁሉም ነገሮች መፍትሄ ያመጣሉ ብለን ስለምናምን ከስማቸው በፊት ያለውን የሙያ መጠሪያ ስም(ሎሬት፣ፕሮፌሰር፣ዶክተር፣ኢንጂነር፣ካፕቴን፣ፓይለት) ተብሎ ሲጠራ ሙያቸውን እና ስማቸውን እንኳ በቅጡ ሳናውቅ በሌሉበት ከመቀመጫችን ተነስተን ጮኀን እናጨበጭብላቸዋለን። እውነቱ ግን ሌላ ነው ሙያዊ እውቀት እንኳ በየግዜው ካልታደሰ ምንም ነገር አይሰራም። ቢሰራም እንኳ አመርቂ ውጤት አያመጣም። ምክንያቱም ሙያዊ የፈጠራ ሳይንሳዊ የምጥቀት እውቀቶች በየግዜው እራሳቸውን እያሳደጉ እና እያሻሻሉ ቀርበዋልና። በእኛ ፊደል የቆጠረው “ኢሊት” ማህበረሰብ ዘንድ ግን እንደዛ አይደለም እንደምንም አንዴ የሚፈለገው ሙታዊ የትምህርት ማእረግ ከተገኘ ቡኅላ ሁሉም ነገር እዚያው ላይ ያበቃል። አስመራቂውም አካል አሁን አውቀኋል ብሎ ይመርቃል። ተመራቂውም ከአሁን ጀምሮ ሁሉን አውቄያለው ከአሁን ቡኋላ ምንም አይነት ሙያዊ እውቀት አያስፈልገኝም ብሎ ይመረቃል። ለዚህም ነው በዛሬ ግዜ በሀገራችን አያሌ የሰው ልጅ ነፍሶች በየቀኑ በእውቀት ማነስ ህክምና ምክንያት ህይወታቸውን የሚያጡት እጅግ ትላልቅ የኮንስትራክሽን መሰረተ ልማቶች በእውቀት ማነስ ምክንያት ሰዎች አናት ላይ ሲፈርሱ እና የዝናብ ውሃ ጠርጎ ሲወስዳቸው የምናየው በሁሉም የሙያ አገልግሎት የእውቀት ማጣት በሰው ልጆች ውድ ህይወት እና በአገር ኢኮኖሚ ላይ ያመጣውን ቀውስ ጥቂት አይምሮ ያላቸው ሰዎች ተረድተውት ታዝበውታል። እንዲሁም ጥቂቶች በቀድሞ በደጉ ዘመን የተፈጠሩ አሁንም አንዳንዶች በህይወት ያሉ ጥቂት በሙያዊ እና በአእምሮአዊ እውቀታቸውን ተጠቅመው ለሀገራቸው ባደረጉት የጎላ ስራ እጅግ የተከበሩ ሰዎች እንዳሉ እናውቃለን።
አይምሮአዊ እውቀት ግን ከሙያዊ እውቀት በእጅጉ ይለያል። በአይምሮአዊ እውቀት ባብዛኛው የሚያተኩረው ሁሉንም ነገሮች የአይምሮን እና ልቦናን አጣምሮ በመጠቀም የተለያዩ ጥያቄዎችን በመጠቀም በጥልቀት ቆፍሮ መበርበር እና መፈተሽ ማለት ሲሆን እንዲሁም በተጨማሪ አይምሮአዊ እውቀት ስለሚደረገው፣ስለሚባለው እንዲሁም ስለማናቸውም ነገሮችን አምኖ ለመቀበልም ሆነ ላለመቀበል በቂ የተረጋገጠ መረጃ ይፈልጋል።
ይህንን ከላይ ለመነሻ ከልኩ ዘንዳ ወደ ዋናው የዛሬ መልእክቴ ስመለስ ሀገራችን ኢትዮጵያ ከመቼውም ግዜያቶች እጅግ በከፋ ሁናቴ በፓለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊ እና በማህበራዊ አሰቃቂ የውድቀት ከፍተኛ ቀውሶች ውስጥ ትገኛለች። ሁሉም ነገር ከዛሬ ነገ ይሻሻላል ተብሎ ሲታሰብ እና ተስፍ ሲጣልበት ነገሮች በተቃራኒው ከድጡ ወደ ማጡ ሂደትን በፍጥነት አልፈው የአንጦርጦስ የህይወት ጉዞ ወደ ሲኦል በሚመስል መልክ አኳኋን ሁኔታ ላይ ትገኛለች። ሁላችንም በያከንበት ግራ ገብቶን እና የምንይዘው የምንጨብጠው ነገር አጥተን ነገሮችን በቁጭት እና በሀዘን ስሜት ተብሰክስከን በትካዜ እየተመለከትን ብቻ እንገኛለን።
ይህንን የጭቆና የግፍ የአገዛዝ ቀንበርን ከሀገራችን ከኢትዮጵያ የሚበላው ካጣው ምስኪን ወገናችን ላይ ተሰብሮ እንዲወድቅልን እና ነጻ እንዲያወጡን ላለፉት 25 አመታት በሀገር ውስጥም ሆነ በዓለም ዙሪያ በየቀኑ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ በየአደባባዩ ያለመሰላቸት ተሰልፈን ጮኀናል። በተጨማሪም ትላልቅ አገራዊ እና አለም አቀፋዊ የመፍትሄ ስብሰባዎችን በየግዜው አድርገናል። ሁሉንም እንቅስቃሴዎቻችንን እና ጬኀታችንንም በሙሉ ለአለም አቀፉ ማህበረተሰብ እና የሰብአዊ መብት ተሟጓች ተቋሟቶች ለሁሉ ስቆቃችንን እንዲያሳውቁልን እና እንዲያስተጋቡልን እንዲሁም እንዲያማልዱልን ግዙፎቹን እና አለም አቀፎቹን መገናኛ አውታሮች ሁል ግዜ ተማጽነናል። ነገር ግን ነገሮች ከመባሳቸው ውጭ ምንም መፍትሄ የለም። ይባስ ብለው ተስፋ የጣልንባቸው አለም አቀፉ ማህበረተሰብ ከምንግዜውም በተለየ አምባገነን ገዣችንን በፓለቲካዊ፣በኢኮኖሚያዊ እና በማህበራዊ ኩነቶች ድጋፋቸውን በግልጽ በመስጠት የተሸከምነውን የእንጨት ቀንበር ወደ ብረት ቀንበር በመቀየር የስቆቃችንን ቀንበር መሸከም ከምንችለው ክብደት በላይ እጅግ አከበዱብን። ባለፈው አመት በሀገራችን በኢትዮጵያ ታሪክ በአይነቱ እና በአስፈሪነቱ ለመጀመሪያ ግዜ የተከሰተውን የረሀብ አደጋ ምክንያት በዛው እግረመንገዱን የገዣችን የአገዛዝ ስርአት ያበቃል ብለን ስንጠብቅ ( በአለማችን በፓለቲካ ታሪክ ጽኑ ረሀብ አንድ ሀገር ከገባ የዛ አገር መንግስት የገባው ረሀብ ስርአቱን ይጥለዋል ተብሎ ስለሚታመን ደግሞም በቀድሞው የሀገራችን ሁለት ስርአቶች ለመውደቃቸው እረሀቦቹ እንደ ዋና ምክንያት ሁሌም ስለሚነሱ) አለም አቀፉ ማህበረተሰብ ሀይላቸውን ሁሉ ተጠቅመው ስርአቱ እንዳይወድቅ ታድገዋቸዋል። አሁንም መፍትሄ አልመጣም። ስቆቃው ግን ከአንድ ሺህ ግዜ እጥፍ በላይ ጨምሮዋል። ስለዚህ ምንድ ነው መፍትሄው? በሰላማዊ መንገድ ህዝባዊ እንቢተኝነትን በሀገሩ ሁሉ ላይ ማድረግ ይህም ተደረገ። አይደለም የሰው ልጅ ጨካኝ አውሬ እንኳ የገዛ ወገኑ ላይ የማያደርገውን ድርጊት መንግስት መርጦኛል ባለው ከአብራኩ በወጣው ወገኑ ላይ በቀን በጠራራ ፀሐይ ባደባባይ ቁጥራቸው በመቶዎች በሚቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ከህጻን እስከ አረጋውያን ሳይመርጥ በግፍ የንጹሐንን ደም በየቦታው እና በሀገሩ ሁሉ ላይ አፈሰሰ። ይህንንም በመቃወም አሁንም ከሌላው ግዜ በተለየ ቀድሞ በዘር እና በጎሳ ተለያይተን የነበርን አሁን ግን እንደ አዲስ ሆነን ጮኀን ጬኀታችንንም በሙሉ ለአለም አቀፉ ማህበረተሰብ እና የሰብአዊ መብት ተሟጓች ተቋሟቶች ሁሉ እንዲያሳውቁልን እና እንዲያስተጋቡልን እንዲሁም እንዲያማልዱልን ግዙፎቹን አለም አቀፎቹን መገናኛ አውታሮች በድጋሚ ተማጸንን። ነገር ግን ነገሮች ከመባሳቸው ውጭ ምንም መፍትሄ የለም።
አሁንም አለም አቀፉ ማህበረተሰብ ስቆቃችንን እንዲያውቅልን እና ነጻ እንዲያወጣን ተስፋ አደረግን በማህበራዊ ሚዲያዎች አማካኝነት እውነተኛ ምንጩ የማይታወቅ ቢታወቅም ምንም መፍትሄ የማያመጣ ቀቢፀ የተስፋ ወሬ ተናፈሰ “አሜርካ የኢትዮጵያ ጉዳይ ያሳስበኛል አለች” እንዲሁም “አውሮጳ ህብረት ለኢትዮጵያ መንግስት የምንሰጠውን እርዳታ እናቆማለን አሉ” ብላ ብላ ብላ …………………..ብላ ብላ
ኦኦ! እንዴት የሰው ልጅ ከባለፈው ታላቅ የታሪክ ስህተት አይማርም? የኛ ነገር ያስተሳሰብ እውቀታችን ጉድ የሚያስብል ነገር እኮ ነው! የጉድም ጉድ፦ የሰውን ልጅ ደም እየጠጡ ያደጉት እና አሁንም በግፍ ደም እየኖሩ ያሉት አሜሪካኖቹ እና አውሮጳውያኖቹ አይደሉም እንዴ? ለዚህ ከክፉ እጅግ ለሚከፋው የባርነት የስቃይ ህይወት እንድንኖር ያደረጉን የአማልክት ስእል መልክ ያላቸው እና ቆዳቸው እንዲሁም ፀጉራቸው እንደበረዶ የነጡት ውስጣቸው ግን እጅግ ክፉ የክፉም ክፉ ከድቅድቅ ጨለማ ይበልጥ እጅግ የሚጠቁረው አሜሪካኖቹ እና አውሮጳውያኖቹ አይደሉም እንዴ ለዚህ ያበቁን? ስሙኝማ ሌላው ሌላው ቢቀር በኢተዮጵያ የዲሞክራሲያዊ ጉዞ ታሪክ የመጀመሪያው የተባለለትን የምርጫ 1997 ቱን የሰፊው የኢትዮጵያን ህዝብ የምርጫ ድምጹን አሰርቀው የሰላም ተስፋውን ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ያጨለሙበት ወርቅ ቅቦቹ እና ባለ ነጭ ጸጉሮቹ አሜሪካኖቹ እና አውሮጳውያኖቹ አይደሉም እንዴ? አይ! አለማስተዋል ደመነፍሳዊ ያስተሳሰብ ህይወት ዘይቤ ማለት ይሄ ነው! እንዴት እውነተኛ ሰው የሆነ ሰው ከሰይጣን ሰላምን፣ነጻነትን፣ፍትህን፣ፍቅርን፣ብልጽግናን፣አንድነትን እና ፈውስን ላለፉት 25ዓመት ይጠብቃል? የሰይጣንን መንግስት ሰላም እና ደስታ እንዲያመጣልን ለለፉት 25ዓመት ደክመን የጠበቅንበትን ግዜ ለአንድ አመት ለሚሆን ግዜ እውነተኛውን የሰላም፣የፍቅር፣የምህረት፣የበረከት እና የጥበብ አምላክ የሆነውን እግዚያብሔርን ታግሰን እና መፍትሄ እንዲሆነን ብንጠብቅ ኖሮ ያኔ ገና ከችግሮቻችን ነጻ ወጥተን እኛም ለሌሎች እንተርፍ ነበር ብዬ እኔ በግሌ አምናለሁ። ወገኖቼ እስቲ ለትንሽ ደቂቃ ቆም ብላችሁ እነዚህን ሁሌም ተስፋ የምናደርጋቸውን አሜሪካኖቹ እና አውሮጳውያኖቹን ሌላው ቢቀር በአለም ላይ በዚህ ሰአት እያደረጉ ያሉትን ነገሮች በማስተዋል ተመልከቱ! እነሱ አይደሉም እንዴ በሰላም፣በደስታ እና በፍቅር ሲኖር የነበረውን የሴሪያ፣የኢራቅ እንዲሁም የሊቢያን ህዝብ ኑሮውን የሲኦል ህይወት ያደረጉበት ተመልከቱ ይህ ማለት በአገራችን በኢትዮጵያ ህዝብ ላይም ተደግሞ እየተሰራ ያለው የሽፍጥ ፓለቲካዊ ሴራ ዋና ተዋናዮቹ ዛሬ ፍቅር፣ሰላም፣ፍትህ እና ነጻነት እንዲያመጡልን ደጅ የምንጠናቸው እና የምናቆለጳጵሳቸው አሜሪካኖቹ እና አውሮጳውያኖቹ አይደሉም እንዴ? ደግሞስ አሁን በሀገራችን በኢትዮጵያ የሰላማዊውን ንፁሃን ዜጎች የወገኖቹን ደም በግፍ እያፈሰሰ ለ25 አመት የነገሰውን ስርወ መንግስት ፈጥረው የሾሙትስ እነሱ አይደሉም እንዴ? ጓዶች! አሜሪካኖቹ እና አውሮጳውያኖቹ ፓለቲከኞች አይደለም ለኛ ለራሳቸው ዜጋ እንኳ ጠላቶች እንደሆኑ እውነቱን ስንቶቻችን ነን የምነውቅ? በደጉ ዘመን ግዜ በዲሞክራሲ እና በሰብአዊነት ጭምብል የምትታወቀዋ አሜርካ በየቀኑ ሰላማዊ ዜጋዎቿን በፓሊስ ባደባባይ እራሷ ባስታጠቀቻቸው ፓሊሶች ሲገደሉ ብዙ ግዜ በአለማቀፎቹ መገናኛ አውታሮች እና በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ተመልክተናል። ዜጋዎች ለፓለቲካ ጥቅም ትርፍ ፍጆታ ሲባል ብቻ በአሜርካ መንግስት የደህንነት ቢሮ በራሱ ሰላማዊ ዜጎች ላይ የተቀነባበረ የሽብር አሰቃቂ ጥቃት አደጋ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን በአሰቃቂ ሁኔታ ሲሰው በተለያዩ ግዜ አይተናል። እንዲሁም ለፓለቲካዊ ትርፍ ፍጆታ የሚውል በሶሻል ኢንጅነሮች የተቀነባበረ ሳይኮሎጂካል ጥቃት በሴቶች፣በህጻናት እና በነጻነት መብት ስም በሰላማዊ ዜጋቸው ውስጥ በማስረጽ የቤተሰብን ህይወት አመሰቃቅለው እራሳቸው ባስገቡት አደገኛ የአደንዛዥ እጽ ሰላማዊውን ህይወቱን በሶሻል ኢንጅነሮች የክፋት ሴራ የተናጋበት ዜጋ የእጽ ተጠቃሚ አድርገውት በአስከፊ አሟሟት ገለውታል። ወጣቶችም በነጻነት እና በስነጥበብ ስም ልቅ ወሲብ ሲያደርጉ የሚያሳይ የቪዲዮ ምስላቸውን ያለምንም ከልካይ እፍረት በድፍረት እና በደስታ በኢንተርኔት በነጻ ሲያሰራጩት እግዚኦ! አውጣኝ ጌታዬ! ሁል ግዜ ያስብላል። በምድረ አውሮጳም እንደዛው!
በዚህ እየኖርንባት ባለችው ፕላኔታችን ላይ የሰው ልጆችን ሁሉ አይምሮአቸውን እና ልቦናቸውን እንዲሁም መንፈሳቸውን ይዞ የሚመራ ሁለት አይነት መንፈሶች አሉ። እነዚህ ሁለት መንፈሶች “ቅዱስ” መንፈስ እና “ክፉ” መንፈስ በመባል ይታወቃሉ። ሁለቱም መንፈሶች በአንዴ በአንድ ሰው ህይወት ውስጥ በተአምር አብረው ተዳብለው ሊኖሩ አይችሉም። ሁሉም ሰዎች ከሁለቱ በአንዱ መንፈስ ብቻ ይመራሉ። ከሁለቱ አንዱ “ቅዱስም” ሆነ “ክፉ” መንፈስ ያለበት ሰው በውስጡ ያለው መንፈስ ምን አይነት እንደሆነ የሚታወቀው ግለሰቡ ተለሳልሶ ወይም ተቆጥቶ በሚናገረው ቃል ሳይሆን ግለሰቡ በሚያደርገው ድርጊታዊ ስራ ብቻ ነው። ለዚህም ነው መጽሐፍ ቅዱስ አንድን ሰው ማመን ያለብን በቃሉ ሳይሆን በድርጊቱ ብቻ እንደሆነ ብዙ ግዜ አበክሮ የሚያስጠነቅቀን።
የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውሥጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ።ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ። ከእሾህ ወይን ከኩርንችትስ በለስ ይለቀማልንእንዲሁ መልካም ዛፍ ሁሉ መልካም ፍሬያደርጋል፥ ክፉም ዛፍ ክፉ ፍሬ ያደርጋል። መልካም ዛፍ ክፉ ፍሬ ማፍራት፥ ወይም ክፉ ዛፍ መልካም ፍሬ ማፍራትአይቻለውም።
ማቴ 7:15-18 ስለዚህም ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ። በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም። በዚያ ቀን ብዙዎች። ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢትአልተናገርንምን፥ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን፥ በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምንይሉኛል። የዚያን ጊዜም።ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ።” ማቴ 7:20-27  
እኔ በግሌ በእግዚያብሔር እውነተኛ ቃል ላይ የፀና የማያወላውል ጽኑ እምነት አለኝ። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ባጠቃላይ ስለሁሉም ነገር በግልጽ ተጽፎ ይገኛል። እግዚያብሔር የዚህን አለም ፓለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊውን አደረጃጀት የሚያስተዳድረው ዲያብሎስ እንደሆነ በመጽሐፍ ቅዱሳችን ላይ በግልጽ እንዲህ ተጽፎ እናነባለን ዲያብሎስም ረጅም ወደ ሆነተራራ አውጥቶ የዓለምን መንግሥታት ሁሉ በቅጽበት አሳየው።ዲያብሎስም። ይህ ሥልጣን ሁሉ ክብራቸውም ለእኔተሰጥቶአል ለምወደውም ለማንም እሰጠዋለሁና ለአንተ እሰጥሃለሁ፤ ስለዚህ አንተ በእኔ ፊት ብትሰግድ፥ ሁሉ ለአንተ ይሆናልአለው። ኢየሱስም መልሶ። ለጌታ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፎአል አለው።” ሉቃ4:5-8
ከላይ ኢየሱስ ክርስቶስ በዲያብሎስ በተፈተነ ግዜ ከፈታኙ ከዲያብሎስ ጋር የነበረውን ንግግራቸውን ነው ያነበብነው። ኢየሱስ ክርስቶስም ዲያብሎስን ነገስታትን እንድትሾም ስልጣን አልተሰጠህም ብሎ አላለውም ምክንያቱም እንደተሰጠው ያውቃልና ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተማሪዎች እና ሰባኪዎች የሐዋርያው ጳውሎስን የሮሜ 13 መልእክቱን እንደወረደ በመተርጎም እና ለፓለቲካ ፍጆታ በማዋል ሲያመቻምቹት ይስተዋላል። ሮሜ 13 የሚለው እንደዚህ ነው ነፍስ ሁሉ በበላይ ላሉት ባለ ሥልጣኖች ይገዛ።ከእግዚአብሔር ካልተገኘ በቀር ሥልጣን የለምና፤ ያሉትም ባለ ሥልጣኖች በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው። ስለዚህ ባለሥልጣንን የሚቃወም የእግዚአብሔርን ሥርዓት ይቃወማል፤ የሚቃወሙትም በራሳቸው ላይ ፍርድን ይቀበላሉ። ገዥዎችለክፉ አድራጊዎች እንጂ መልካም ለሚያደርጉ የሚያስፈሩ አይደሉምና። ባለ ሥልጣንን እንዳትፈራ ትወዳለህን? መልካሙንአድርግ ከእርሱም ምስጋና ይሆንልሃል፤ለመልካም ነገር ለአንተ የእግዚአብሔር አገልጋይ ነውና። በከንቱ ግን ሰይፍአይታጠቅምና ክፉ ብታደርግ ፍራ፤ ቍጣውን ለማሳየት ክፉ አድራጊውን የሚበቀል የእግዚአብሔር አገልጋይ ነውና።ስለዚህስለ ቍጣው ብቻ አይደለም ነገር ግን ስለ ሕሊና ደግሞ መገዛት ግድ ነው።ስለዚህ ደግሞ ትገብራላችሁና፤ በዚህ ነገር የሚተጉየእግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸውና።ለሁሉ የሚገባውን አስረክቡ፤ ግብር ለሚገባው ግብርን፥ ቀረጥ ለሚገባው ቀረጥን፥መፈራት ለሚገባው መፈራትን፥ ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ።እርስ በርሳችሁ ከመዋደድ በቀር ለማንም ዕዳ አይኑርባችሁ፥ሌላውን የሚወድ ሕግን ፈጽሞታልና።” ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ሁሉንም ክፍል በደንብ ስናነበው እንዲሁም ከሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች የቃሉን ትርጉም ጋር ስናመሳክረው ክፍሉ የሚለው መንግስት ለሚያወጣው የቀረጥ ግብር ክፍያ ህግን ተግባራዊ እንድናደርግ እና እንድንፈጽም የሚያሳስብ ሲሆን በዚህ ህግ መሰረት ኢየሱስ ክርስቶስ እና ደቀመዛሙርቶቹ እንኳ ለቄሳር ግብር እንዲከፍሉ ተጠይቀው ሲከፍሉ ተጽፎ እናነባለን። በተለይ ሁሉም የፕሮቴስታንት የመንግስት ደጋፊ ቤተክርስትያኖች እንደሚያስተምሩት ነፍስ ሁሉ በበላይ ላሉት ባለ ሥልጣኖች ይገዛ። ከእግዚአብሔር ካልተገኘ በቀርሥልጣን የለምና፤ ያሉትም ባለ ሥልጣኖች በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው።” የሚለውን ቃል እንደወረደ የምንጠቀምበት ከሆነ “ሰዶማዊ” መሆን ግዴታችን ይሆን ነበር ማለት ነው! መጥመቁ ዮሐንስ ስለ እውነት የሄሮድስን ክፉ ስራ ስለተቃወመ አንገቱ እንደተቆረጠ ተጽፎ እባነባለን። በዚህ ዘመን ያሉም የቤተክርስትያን አስተማሪዎች እውነት ተናግረን አንገታችን እንደ መጥምቁ ዮሐንስ ከሚቀላ የእግዚያብሔርን ቃል ባለስልጣኖቹ እንደሚፈልጉት አስተምረን የእነርሱ ወዳጅ ብንሆን ይሻላል ብለው ያመኑ ይመስላል። ነገር ግን ሐሰተኞች ነቢያት ደግሞ በሕዝቡ መካከል ነበሩ እንዲሁም በመካከላችሁ ደግሞ ሐሰተኞችአስተማሪዎች ይሆናሉ፤ እነርሱም የዋጃቸውን ጌታ እንኳ ክደው የሚፈጥንን ጥፋት በራሳቸው ላይ እየሳቡ የሚያጠፋ ኑፋቄንአሹልከው ያገባሉ፤ ብዙዎችም በመዳራታቸው ይከተሉአቸዋል በእነርሱም ጠንቅ የእውነት መንገድ ይሰደባል። ገንዘብንምበመመኘት በተፈጠረ ነገር ይረቡባችኋል፤ ፍርዳቸውም ከጥንት ጀምሮ አይዘገይም ጥፋታቸውም አያንቀላፋም።” 2 ጴጥ 2:1-3
ዛሬ በአለማችን ላይ አለማችንን የሚያስተዳድሩት “ኢሊቶች” ( የዲያብሎስ ልጆች ) በአለማችን ላይ በፓለቲካዊ፣በኢኮኖሚያዊ እና በማህበራዊ አዲስ አይነት የመንግስት አሰራር እና አደረጃጀት ተግባራዊ አድርገዋል። ይህ አዲሱ የአለም የመንግስት አደረጃጀት እና አወቃቀር አዲሱ የአለም መንግስት ስርአት ( New world order ) ወይም አዲሱ የአለም መንግስት ( New world Government ) በመባል የሚታወቅ ሲሆን በአገራችን ኢትዮጵያን ጨምሮ በአለም ሁሉ ላይ እየተፈጠሩ ያሉትን ሰው ሰራሽ የፓለቲካዊ፣የኢኮኖሚያዊ እና የማህበራዊ አሰቃቂ ስቆቃዊ ቀውሶች የዚህ ሊመሰረት ላለው ለአዲሱ የአለም መንግስት ስርአት ( New world order ) ዋና እና አስፈላጊ የፓለቲካ ትርፍ ግብአት መሆናቸውን ስንቶቻችን ነን በጥልቀት የምናውቀው? በአገራችን በኢትዮጵያ የበትረስልጣን ዙፋኑን በኀይል የተቆናጠጠው ገዥው መንግስት በየግዜው የሚያረቃቸው እና የሚያጸድቃቸው አፋኝ እና ጨቋኝ ህጎች የዚሁ አዲስ የሚመሰረተው የአለም መንግስት ህግ እንደሆነ ስንቶቻችን ነን የምናውቀው? ከአሁን ቡኋላ ይበልጥ ከምንግዜውም በላይ አፋኝ እና ጨቋኝ የኮሚኒስት ወታደራዊ ስርአት አገራችንን ኢትዮጵያ ጨምሮ በአለማችን ላይ በቅርቡ ሊነግስ እንደሆነ ስንቶቻችን ነን የምናውቀው? ከአሁን ቡኋላ በአለማችን ላይ ሰላም፣ፍቅር፣አንድነት፣ነጻነት እና እኩልነት የማይታሰብበት እና የማይገኝበት እንዲሁም በተቃራኒው የታላቅ መከራ ዘመን እንደሚሆን ስንቶቻችን ነን በጥልቀት የምናውቀው? አዲሱ የአለም መንግስት ስርአት ( New world order ) በአለማችን ላይ ከአሁን ቡኋላ በአለማችን ላይ ምን ሊሰራ አቅዷል? በአለም ላይ ያሉ ታዋቂ ሰዎች ስለ አዲሱ የአለም መንግስት ስርአት ( New world order ) ምን ይላሉ? መጽሐፍ ቅዱስ ስለ አዲሱ የአለም መንግስት ስርአት ( New world order ) ምን ይለናል? እኛ ሁላችን የመጨረሻው ዘመን ነዋሪዎች እንደሆንን ስንቶቻችን በጥልቀት ተረድተነዋል? የእነዚህን እና ሌሎችንም አንኳር የሁላችንም የውስጥ ጥያቄዎቻችንን በጥልቀት እንዳስሳለን በጥሞናና በትእግስት ይህንን መልእክት ያንብቡ ይጠቀሙበታል እንጂ አይጎዱበም። ያተርፉበታል እንጂ አይከስሩበትም ስለሆነም በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ በራዕይ መጽሐፍ ውስጥ በመጨረሻው ዘመን በክፉ ስራዋ ስለምትገለጠው በሴት ተመስላ ስለቀረበችው የግፍ ከተማ መነሻ በማድረግ ለአዲሱ የአለም መንግስት ስርአት ( New world order ) ሽፍጣዊ የዲያብሎስ ሴራን እንዲሁም መፍትሄውን በመጽሐፍ ቅዱስ በእግዚያብሔር ቃል አማካኝነት በጥልቀት በወደ ውስጥ በመግባት ጎልጉለን እናወጣዋለን።
ከእግዚአብሔር እንደ ሆንን ዓለምም በሞላው በክፉው እንደ ተያዘ እናውቃለን።” 1ዮሐ5፡19
በሚቀጥለው ጽሁፍ ቀጣዩ ክፍል ይቀጥላል…………………………………….

No comments:

Post a Comment