Sunday, May 10, 2015

ለመጽደቅ እንደ “ጦጣ” ወይም ልዬ “ኮማንዶ” ወታደር በገመድ ተንጠላጥለን ቋጥኝ ላይ መውጣት አለብን? ለመጽደቅ በእንብርክክ የጉልበታችን ስጋ እየተገሸለጠ መሄድ አለብን? ለመጽደቅ ዋሻ ውስጥ መኖር አለብን? ለመጽደቅ ቅጠላ ቅጠልና ስራ ስር መብላት አለብን? ለመጽደቅ አገር አቆራርጠን በእግርም በእጅም በዳዴም መሔድ አለብን? ለመጽደቅ የእግራችን ተረከዝ በግፍ መሰነጣጠቅ አለብን?

debre

“ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው። መጻሕፍትንና የእግዚአብሔርን ኃይል አታውቁምና ትስታላችሁ።” ማቴ22:29
በበደላችሁና በኃጢአታችሁ ሙታን ነበራችሁ፤ በእነርሱም፥ በዚህ ዓለም እንዳለው ኑሮ፥ በማይታዘዙትም ልጆች ላይ አሁንለሚሠራው መንፈስ አለቃ እንደ ሆነው በአየር ላይ ሥልጣን እንዳለው አለቃ ፈቃድ፥ በፊት ተመላለሳችሁባቸው። በእነዚህምልጆች መካከል እኛ ሁላችን ደግሞ፥ የሥጋችንንና የልቡናችንን ፈቃድ እያደረግን፥ በሥጋችን ምኞት በፊት እንኖር ነበርን እንደሌሎቹም ደግሞ ከፍጥረታችን የቁጣ ልጆች ነበርን። ነገር ግን እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለ ጠጋ ስለ ሆነ፥ ከወደደን ከትልቅፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን፥ በጸጋ ድናችኋልና፥ በሚመጡ ዘመናትምበክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለ ጠግነት ያሳይ ዘንድ፥ ከእርሱ ጋር አስነሣንበክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን። ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔርስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም።” ኤፌ 2:1_9
ጻድቅ ባሪያዬም በእውቀቱ ብዙ ሰዎችን ያጸድቃል፥ ኃጢአታቸውን ከማል። ስለዚህም እርሱ ብዙዎችን ይወርሳል፥ከኃያላንም ጋር ምርኮን ይከፋፈላል፤ ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሰጥቶአልና፥ ከዓመፀኞችም ጋር ተቈጥሮአልና፤ እርሱ ግን የብዙሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ፥ ስለ ዓመፀኞችም ማለደ።” ኢሳ 53:11_12
ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ማንም እንዳይመካ ከሥራአይደለም።” ኤፌ 2:8_9
20-Pilgrims-clonbing-stairs-in-Lalibela
ከላይ ለዚህ ጽሁፍ መነሻ የተጠቀምኩበት የዚህ መልእክት ዋና ሀሳብ ያተኮረው በእንግሊዝኛው መጠሪያ ቃል Justification ወደ አማርኛው ስንተረጉመው “ጽድቀት” : “መንጻት” : “ደህንነት”: “ጥበቃ” እና “ከለላ” በሚሉ ቃሎች ትርጉም በሆነው በመደበኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል አጠራሩ “ጽድቅ” ስለሚባለው ክርስቲያናዊ አስተምህሮ ይሆናል :: ይህንን የጽድቀት አገልግሎት ለማግኘት ወይም ለመጽደቅ እንደ “ጦጣ” ወይም ልዬ “ኮማንዶ” ወታደር በገመድ ተንጠላጥለን ቋጥኝ ላይ መውጣት አለብን? ለመጽደቅ በእንብርክክ የጉልበታችን ስጋ እየተገሸለጠ መሄድ አለብን? ለመጽደቅ ዋሻ ውስጥ መኖር አለብን? ለመጽደቅ ቅጠላ ቅጠልና ስራ ስር መብላት አለብን? ለመጽደቅ አገር አቆራርጠን በእግርም በእጅም በዳዴም መሔድ አለብን? ለመጽደቅ የእግራችን ተረከዝ በግፍ መሰነጣጠቅ አለብን?
12_Pilgrims-worn-out-feet-in-Lalibela
ለ“መጽደቅ” ተብሎ የሚደረግ የስቃይ ሐይማኖታዊ ልማዶች ማለትም የመንፈሳዊ የሐይማኖት ንግስ በአሎች ጉዞ : የገዳም የዋሻ ተደብቆ ኑሮ : ስጋን ማጎሳቆል እና ሌሎችም ክፉ የሰው ሀሳብ የሆኑ ሐይማኖታዊ ጎጂ ልማዶች ሁሉም መነሻቸው ከዲያብሎስ ነው:: ለምሳሌ የንግስ ሐይማኖታዊ ጉዞ (paganism) ለዚህ አለም ያስተማረችው ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስትያን ስትሆን እስልምናን ጨምሮ ካቶሊክ : ኦርቶዶክስ እና ሂንዱዝም እና ሌሎችም በአለም ላይ ያሉ ልዩ ልዩ የሆኑ እንደ ሰው መልካም ሀሳብ የተፈጠሩ የሀሰት እምነት አስተምሮቶች የሚንቀሳቀሱት በሐይማኖት ሽፋን ስም ነው:: በሐይማኖት ሽፋን ስም የሚመለከውም ደግሞ ዲያብሎስ (pagan) ነው::
fatima_portugal_02fatima_portugal_05
ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስትያን በአመት አንድ ግዜ የኢስላም ነቢይ የሆነውን የነብዩ መሀመድ ልጅ የሆነችውን “ፈጢማ” ሁለተኛዋን “ማርያም” ንግስ ለማክበር በአለም የሚገኙ የካቶሊክ ምእመና ወደ ፖርቹጋል ጉዞ በማድረግ ታላቅ ሐይማኖታዊ ጉዞና ስርአት ያደርጋሉ:: እንዲሁም ኢስላም እምነት እንዲሁ የኢስላም እምነት ፈጣሪ የሆነው ነብዩ መሀመድ የትውልድ ቦታ የሆነችው “መካ” በአለም ላይ ያሉ ሙስሊሞች እንዲሁ በየአመቱ ሐይማኖታዊ ጉዞ ወደ መካ ያደርጋሉ:: ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን የቁጥሩ ብዛት የማይታወቅ ቦታ እና ስፍራ ሐይማኖታዊ ስርአት ያለው ጉዞ በብዛት ያደርጋሉ:: ሂንዱ እምነትም እንደ ሌሎቹ ሐይማኖቶች ሁሉ በየአመቱ በአለም ላይ የሚገኙ የ “ሂንዱ” እምነት ተከታዮች ሂንዱ ሀይማኖት በተፈጠረበት ወደ ህንድ ሐይማኖታዊ ጉዞ ያደርጋሉ:: ሌሎችም ቁጥራቸው የበዛ እንደ ሰው ሀሳብና እቅድ የተፈጠሩ ሰው ሰራሽ ሐይማኖቶችም ወደ ተፈጠሩባቸው አገሮችና ቦታዎች ሐይማኖታዊ ጉዞ ያደርጋሉ::
untitledsA submerged idol of Hindu Lord Shiva stands in the flooded River Ganges in Rishikesh
ይህ ሁሉ በሰዎች ላይ እየደረሰ ያለው ሰው ሰራሽ ስቆቃና ስቃይ የሐይማኖት ስርአቶች ያስፈለጉት ለአንድ ነገር ብቻ ነው:: እርሱም Justification “ጽድቀት” : “መንጻት” : “ደህንነት”: “ጥበቃ” እና “ከለላ” ከፈጣሪ ዘንድ ለማግኘት እንደ ሐይማኖቶቹ ፈጣሪዎቹ ሰዎች ሀሳብ መሰረት “ጽድቀት” የሚገኘው በሐይማኖታዊ እምነት በስቃይ ብቻ ነው::
indian-miracle-lake-1060328.jpg060343.jpg060315.jpg
ድሮ ድሮ ሳላውቀው ከቤተሰቦቼ እንደ እቃ ወርሼው የኖርኩበትን የኦርቶዶክስ ሐይማኖት ቤተክርስትያን ምክንያቱ ሳይገባኝ የንግስ ጉዞዎችን ከጓደኞቼ ጋር በቡድን ሆነን እንጓዝ ነበረ:: የምንጓዘው ግን ሁላችንም የሐይማኖት ጉዞው አላማው ገብቶን ሳይሆን ከቤት ወጥተን ውጭ በነጻነት እየጨፈርን ለማደር ነጻነቱን በሐይማኖት ስም ቤተሰቦቻችን ስለሚሰጡን የንግስ ጉዞ እና የቤተክርስትያን ሐይማኖታዊ አዳሮችን ሁላችንም ወንዶቹም ሴቶቹም እንወዳቸዋለን:: ምክንያቱም ነጻ ሆነን በሐይማኖት የንግስ ጉዞ ወይም የቤተክርስትያን አዳር ሐይማኖት ስርአት ስም ሁላችንም ለሊቱን ሙሉ እየጠጣን : እየጨፈርንና ተመራርጠን ከተፈቀድናት ሴት ጋር እንተኛ ነበረ:: ሲነጋ ነጠላችንን ጋቢያችንን ለብሰን ከቤተክርስትያን አድረን የወጣን ለማስመሰል ቤተክርስትያኑን በር ተሳልመን ወደ ቤታችን እንገባና ቀኑን ሙሉ ተኝተን እናሳልፍ ነበረ:: በተለይ የንግስ ጉዞው ራቅ ያለ ቦታ እና የተወሰኑ ጥቂት የሚባሉ ቀኖች የምንከርም ከሆነ አቤት ደስታችን ወደር የለውም ምክንያቱም ማን ከማን ጋር እንደምንሄድና እንዴት በሀጢያት እንደምንደሰት እቅድና ባጀት እናወጣለን እናወርዳለን ባቀድነው መሰረት እርኩስ የሆነው ሐይማኖታዊ ጉዞው እኛም ሀጢያታዊ እርኩሰትን ስራ ተግባራዊ እናደርገዋለን:: አንዳንዴ እዛው ቤተክርስትያን ውስጥ ከታቦቱ ካረፈበት ቦታ አጠገብ ሁላችንም ጥንድ ጥንድ በመሆን ሐይማኖቱ ስርአት የሚፈቅደውን የሀጢያት እርኩሰት ግዴታ እንፈጽማለን:: በተለይ በተለይ የ “ጥምቀት በአል” ልዩ የሆነ የሐይማኖት ኦርቶዶክስ እርኩሰተ ሀጢያትን ለመፈጸም ጥሩ ሐይማኖታዊ ስርአት ነው:: በተለይ በወጣቶችና በጎልማሶች በሌሎችም እድሜ ክልል ያሉ ወንዶችና ሴቶች ዘንድ የጥምቀት በአል እጅግ ይወደዳል:: ለዚህ ደግሞ አንድ አመት ወደ ጃን ሜዳ ብቅ ይበሉና በጥምቀት በአል አብሮ የሚሰራውን ጸያፍ የሀጢያት እርኩሰት በግልጽ ይመልከቱ ይህ ማለት የሐይማኖቱ የጽድቅ ስራ ተደርጎ ሁሉ በኦርቶዶክስ አማኞች ዘንድ ይቆጠራል:: ምክንያቱም የሚሰራው ጸያፍ ስራ እዚያው ከታቦቱ ማደሪያው አጠገብ ስለሆነ ነገሩን እውነት ያደርገዋል::
3898833EthiopianMonk2
በተለይ ረጃጅም ቀን ከአንድ ሳምንት በላይ የሚያቆዩ የሐይማኖታዊ የንግስ ጉዞዎች ማለትም “ቁልቢ ገብርኤል” : “ግሽን ማርያም” እና “አክሱም ጽዮን ማርያም” ንግስ ግዜ በባለ ትዳሮች ዘንድ እጅግ ተወዳጅ ጉዞዎች ናቸው:: ምክንያቱም አብዛኞቹ ባለትዳሮች ከትዳር ጓደኛቸው ውጭ በነጻነት የሚማግጡበት በዚህ ሐይማኖታዊ ጉዞ ወቅት ነው:: እኔ እራሴ ለሐይማኖታዊ ንግስ ጉዞ ባደረኩባቸው ቦታዎች ሁሉ በጣም የማከብራቸው በከፍተኛ ስፍራ ያሉ ትላላቅ ሰዎችና ባለትዳሮች በዚያ ወቅት ሲቀጥፉ ብዙ ሰዎችን አይቻለሁ:: አብዛኞቹ አንድ ቀን እንኳ በቤተክርስትያን በራፍ አልፈው የሚያውቁ ሰዎች አይደሉም:: እንደነዚህ ያሉ የንግስ ጉዞ ላይ ግን ግንባር ቀደም በመሆን አንደኛ ተሳታፊ እንደውም አብዛኞቹ የጉዞው አዘጋጅና ኮሚቴዎችም ጭምር ናቸው:: ይህ የሚያሳየው በሐይማኖት ስም የሚደረገው የንግስ ጉዞው ምን ያህል ከጸያፍ ኀጢያት ጋር ምን ያህል ቁርኝት እንዳለው የእኔ እና የጓደኞቼ ያሳላፍነው ህይወት ትልቅ ምስክር ነው::
197f8c98fbbd278c6a934a547fda4d96bahitawi-4
ሌላው ደግሞ እንደ ፍልፈልና አይጥ እንዲሁም እባብና የጦጣ ህይወት የጉርጋድ : የዋሻ እና የቋጥኝ ኑሮ ኖረው ለመጽደቅ የሚያስቡትን ሰዎች ስናያቸው በእውነት እነዚህ ጎስቋላ ህይወት የሚኖሩት ለመጽደቅ ፈልገው ነውን? ከተባለ ይሄንን ጥያቄ መመለስ ያለበት አንድ የመንግስት ክፍል አለ እርሱም የ“ፌደራል ፓሊስ የወንጀል ምርመራ ቡድን ክፍል” ብቻ ነው:: ብዙ ግዜ በአለም ላይ አስተውለን አይተነው ከሆነ በዋሻ እና ታላላቅ የተራራ አለቶች ላይ ሰው በቀላሉ ሊደርስባቸውና ሊኖሩባቸው የማይችሉባቸው ስፍራዎች ውስጥ ታላላቅ የሽብር ሴራዎች ይጠነሰሳሉ:: በአለም ላይ ያሉ አደገኛ ተፈላጊ ወንጀለኞች የሚደበቁትም የሚኖሩትም እየወጡ እየገቡም የሽብር ጥቃቶችን የሚያደርሱትም ከእዚሁ ከተለመደው ዋሻ እና ቋጥኝ የአለት ጉድጓድ ውስጥ ነው:: ለዚህም ደግሞ በአለም በሽብር ዝናኛው የሆነው የሳውዲው ተወላጅ “ኦሳማ ቢን ላዲን” እና ቤተሰቦቹ እንዲሁም የሽብር አጋሮቹ የሽብር ተግባር እየፈጸሙ የሚኖሩት በእዚሁ ለጽድቀት በሚኖርበት በዋሻ ውስጥ ነው:: ለዚህም ነው ብዙዎች ሴቶች እናቶችና አባቶች በልጆቻቸው : በትዳራቸው እና በኑሮዋቸው ሲበሳጩ ልብ ብለን ከሰማናቸው “አሁንስ ገዳም ግቢ ግቢ” አለኝ ሲሉ ይደመጣሉ:: እንዲሁም ሰው የገደሉ : በተለያዩ ወንጀሎች የሚፈለጉ ሰዎች እንዲሁ “ገዳም”ይገባሉ:: (ይሸፍታሉ) የዋሻ ወይም የገዳም (የሽፍትናት) ኑሮ በአብዛኛው የሽሽት የኑሮ ህይወት ነው:: የሚሸሹት ዋና ምክንያት የገዳሙንና ሐይማኖታዊ የሰው ስርአት የፈጠሩት ሰዎች ሲናገሩ ከሀጢያት ሸሽተው ለመጽደቅ ነው ይላሉ:: እነርሱ ይህንን ይላሉ:: ኑዋሪዎቹ ግን ከሰሩት ስራ ከፍርድና ከተጠያቂነት ለመሸሽ ቢሆንስ ማን ያውቃል ማስረጃቸው ምንድር ነው? ወይስ ገዳሙ ወይም ዋሻውን የሚያስተዳድሩት ሰዎች እንደ ሌሎቹ ድርጅቶች ከታወቀ የመንግስት አካል ከወንጀል ነጻ የሚያደርግ ማስረጃ አዲስ የሚቀላቀለው የዋሻ ነዋሪው በመጀመሪያ ለመኖር ሲመጣ እንዲያቀርብ ይጠይቁታል ወይ? እነዚህን ጥያቄዎች ለዋሻውና ለቋጥኙ አስተዳዳሪዎችና ለፌደራል ፓሊስ ወንጀል መከላከል ክፍል ትቼዋለሁ:: እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ የሐይማኖት እምነት መሰረት ለምሳሌ ዋሻዎችና ገዳሞች ለልማት አገልግሎት ቢውሉ “ጽድቅ” ቆመ ማለት ነው:: ምክንያቱም ለመጽደቅ እንደ ፍልፈልና እባብ እንዲሁም እንደ ጦጣ እንዲሁም እንደ አሸባሪና ሽፍታ በጉድጓድ ውስጥ በስቆቃ እና በችግር በእንግልት መኖር አለብን ማለት ነው::
ብዙ ግዜ ትንሽ ስለ ሐይማኖታቸው የሚያውቁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ የሐይማኖት እምነት አስተማሪዎችና ምእመናዎች ስለ ምድረ በዳና ስለ ዋሻ የጉርጓድ ህይወት አስፈላጊነቱን ሲናገሩ መጥመቁ ዮሐንስ ቅጠላ ቅጠልና አንበጣ እየበላ በበረሀ ተንከራቷል:: እንዲሁም ጌታችን መድሀኒታችን የማርያም ልጅ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ( የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ : ካቶሊክና ኢስላም አማኞች ሁል ግዜ የሚሉት ኢየሱስ ክርስቶስን የማርያም ልጅ እንጂ የእግዚያብሔር ልጅ አይሉም) 40 ቀን በበረሀ ዞሮ በዲያብሎስ ተፈትኗል:: ስለዚህ እኛም እንዲሁ እንደ እነርሱ ለመሆንና በዲያብሎስ ለመፈተን በበረሀና በስደት እንኖራለን ባለማወቅ ድፍረት ይላሉ::
የእግዚያብሔርም ልጅ የናዝሬቱ ጌታ ኢየሱስም ስለ እነዚህ ሰዎች እንዲህ በማለት እውነቱን ተናግሮዋል::
እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ አንድ ሰው ልታሳምኑ በባሕርና በደረቅ ስለምትዞሩ፥ በሆነም ጊዜ ከእናንተ ይልቅ ሁለትእጥፍ የባሰ የገሃነም ልጅ ስለምታደርጉት፥ ወዮላችሁ። “ ማቴ 23:15
"Following the Monk to Daniel Korkor Church - Gheralta Mountains
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሐይማኖት እምነት አስተምህሮ በምእመናው ዘንድ ታላቅ ሐይማኖታዊ ስርአትና እምነት የሆነው የንግስ ጉዞ እና የገዳም ቁርቁዝና ኑሮ እንዲሁም የዋሻና የጉድጓድ በኑሮዋቸው የተገለጠ ሀጢያት እርኩሰት ህይወት በግልጽ ይመለካል:: ለምሳሌ በጣም የታወቁ ሐይማኖተኛ ቄስ ታዋቂ ጠጅ ቤት ወይም ሚስታቸው አረቄ ወይም ጠላ ቤት አላቸው:: በግልጽም በውጭ ማስታወቂያ “የመምሬ” እከሌ ጠጅ ቤት በመባል በኦርቶዶክስ ሐይማኖት እምነት ዘንድ በክብር ይታወቃል:: ሁሉም ማለት ይቻላል የኦርቶዶክስ ሐይማኖት ምእመና የሐይማኖታዊ ንግስ በአሎችንና ደበር ለደበር እንደ ጦስ ዶሮ የሚዞሩ መእመናዎች ትልልቅ ግዙፍ ገቢ የሚያስገቡ የዝሙት አዳሪ ቤቶች (ቡና ቤትና ሆቴል) : ትልልቅ ጭፈራ ቤቶች : ትላላቅ የዝሙት መፈጸሚያ ቤቶች (አልቤርጎ) : ጫትን ጨምሮ ልዩ ልዩ አደንዛዥ እጽ መሸጫዎች : ልዩ ልዩ የአልኮል መሸጫ ቤቶች ባለቤቶች 90% የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ የሐይማኖት እምነት ተከታዮችና በየግዜው በሚደረገው የንግስ ጉዞ ለመጽደቅ ተጓዦች ናቸው:: በተጨማሪም በጥንቆላ : በድግምትና በሟርት መተዳደሪያ ያላቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ የሐይማኖት እምነት ተከታዮች ከላይ እንደተገለጡት የኦርቶዶክስ ምእመናዎች በተለየ መልኩ ለመጽደቅ የየትኛውንም የንግስ ጉዞ ይካፈላሉ::
የእግዚያብሔር የእምነት በስራ የተገለጠ ጽድቀት የሚጀምረው ከራሳችን ሲሆን የመጀመሪያውም በስራ የተገለጠ የጽድቀት ድርጊት እግዚያብሔር መንፈሱ ከሚጸየፋቸው የእርኩሰት ጸያፍ ሀጢያት በስራ (በድርጊት) መራቅ ሲሆን ሁለተኛው የእምነት ስራ (ድርጊት) የሚገለጠው ደግሞ ለሌሎች ያለንን በመስጠትና በማካፈል የጽድቅ ስራዎችን እንሰራለን:: ይህንንም የጽድቅ ስራ ስንሰራ እንዲታወቅልን ነጋሪት እያስመታን ለሰዎች እያወራን ወይም ስማችን እንዲጠራ እያደረግን ሳይሆን በስውር ማድረግ እንዳለብን ታላቁ መጽሐፍ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ይነግረናል:: ይሁን እንጂ ልክ የውጭ አገር አገር ጎብኚ ይመስል ለመጽደቅ በሚል ሐይማኖታዊ ስርአት ጋራ ለጋራ : ጥሻ ለጥሻ : ዋሻ ለዋሻ : አገር ላገር ቢዞሩ ቢዞሩ በሀጢያት ስራ የሰበሰቡት ገንዘባቸውን አጥፍተውት በስተመጨረሻ በእግዚያብሔር የቁጣ መቅሰፍት ይጠፋሉ እንጂ ጠብ የሚል ጽድቀት ስራ ደህንነት የለም !
ለሰዎች ትታዩ ዘንድ ምጽዋታችሁን በፊታቸው እንዳታደርጉ ተጠንቀቁ፤ ያለዚያ በሰማያት ባለው አባታችሁ ዘንድ ዋጋየላችሁም። እንግዲህ ምጽዋት ስታደርግ፥ ግብዞች በሰው ዘንድ ሊከበሩ በምኩራብ በመንገድም እንደሚያደርጉ በፊትህመለከት አታስነፋ፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋቸውን ተቀብለዋል። አንተ ግን ምጽዋት ስታደርግ ምጽዋትህ በስውር እንዲሆንቀኝህ የምትሠራውን ግራህ አትወቅ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል።” ማቴ 6:1_4
የሰውነት መብራት ዓይን ናት። ዓይንህ እንግዲህ ጤናማ ብትሆን፥ ሰውነትህ ሁሉ ብሩህ ይሆናል፤ ዓይንህ ግን ታማሚብትሆን፥ ሰውነትህ ሁሉ የጨለመ ይሆናል። እንግዲህ በአንተ ያለው ብርሃን ጨለማ ከሆነ፥ ጨለማውስ እንዴት ይበረታ!ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላል ሁለተኛውንም ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋልሁለተኛውንም ይንቃል፤ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።” ማቴ6:22_24
“የሰው ልጅ በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ ከእርሱም ጋር ቅዱሳን መላእክቱ ሁሉ፥ በዚያን ጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል፤አሕዛብም ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ፤ እረኛም በጎቹን ከፍየሎች እንደሚለይ እርስ በርሳቸው ይለያቸዋል፥ በጎችን በቀኙፍየሎችንም በግራው ያቆማቸዋል። ንጉሡም በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል። እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤ ዓለምከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ። ተርቤ አብልታችሁኛልና፥ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛልና፥እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛልና፥ ታርዤ አልብሳችሁኛልና፥ ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና።ጻድቃንም መልሰው ይሉታል። ጌታ ሆይ፥ ተርበህ አይተን መቼ አበላንህስ? ወይስ ተጠምተህ አይተን መቼ አጠጣንህ?እንግዳ ሆነህስ አይተን መቼ ተቀበልንህ? ወይስ ታርዘህ አይተን መቼ አለበስንህ? ወይስ ታመህ ወይስ ታስረህ አይተን መቼወደ አንተ መጣን? ንጉሡም መልሶ። እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት ይላቸዋል። በዚያን ጊዜ በግራው ያሉትን ደግሞ ይላቸዋል። እናንተ ርጉማን፥ ለሰይጣንናለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ። ተርቤ አላበላችሁኝምና፥ ተጠምቼ አላጠጣችሁኝምና፥ እንግዳ ሆኜአልተቀበላችሁኝምና፥ ታርዤ አላለበሳችሁኝምና፥ ታምሜ ታስሬም አልጠየቃችሁኝምና። እነርሱ ደግሞ ይመልሱና። ጌታሆይ፥ ተርበህ ወይስ ተጠምተህ ወይስ እንግዳ ሆነህ ወይስ ታርዘህ ወይስ ታመህ ወይስ ታስረህ መቼ አይተን አላገለገልንህም?ይሉታል። ያን ጊዜ። እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ለአንዱ ስላላደረጋችሁት ለእኔ ደግሞ አላደረጋችሁትምብሎ ይመልስላቸዋል። እነዚያም ወደ ዘላለም ቅጣት፥ ጻድቃን ግን ወደ ዘላለም ሕይወት ይሄዳሉ።” ማቴ25:31_46
ወንድሞቼ ሆይ፥ እምነት አለኝ የሚል፥ ሥራ ግን የሌለው ሰው ቢኖር ምን ይጠቅመዋልእምነቱስ ሊያድነው ይችላልን?ወንድም ወይም እኅት ራቁታቸውን ቢሆኑ የዕለት ምግብንም ቢያጡ፥ ከእናንተ አንዱም። በደኅና ሂዱ፥ እሳት ሙቁ፥ ጥገቡምቢላቸው ለሰውነት ግን የሚያስፈልጉትን ባትሰጡአቸው ምን ይጠቅማቸዋል? እንደዚሁም ሥራ የሌለው እምነት ቢኖርበራሱ የሞተ ነው። ነገር ግን አንድ ሰው። አንተ እምነት አለህ እኔም ሥራ አለኝ፤ እምነትህን ከሥራህ ለይተህ አሳየኝ፥ እኔምእምነቴን በሥራዬ አሳይሃለሁ ይላል። እግዚአብሔር አንድ እንደ ሆነ አንተ ታምናለህ፤ መልካም ታደርጋለህ፤ አጋንንት ደግሞያምናሉ ይንቀጠቀጡማል። አንተ ከንቱ ሰው፥ እምነት ከሥራ ተለይቶ የሞተ መሆኑን ልታውቅ ትወዳለህን? አባታችንአብርሃም ልጁን ይስሐቅን በመሠዊያው ባቀረበ ጊዜ በሥራ የጸደቀ አልነበረምን? እምነት ከሥራው ጋር አብሮ ያደርግ እንደነበረ፥ በሥራም እምነት እንደ ተፈጸመ ትመለከታለህን? መጽሐፍም። አብርሃምም እግዚአብሔርን አመነ ጽድቅም ሆኖተቈጠረለት ያለው ተፈጸመ፤ የእግዚአብሔርም ወዳጅ ተባለ። ሰው በእምነት ብቻ ሳይሆን በሥራ እንዲጸድቅ ታያላችሁ።እንደዚሁም ጋለሞታይቱ ረዓብ ደግሞ መልእክተኞቹን ተቀብላ በሌላ መንገድ በሰደደቻቸው ጊዜ በሥራ አልጸደቀችምን?ከነፍስ የተለየ ሥጋ የሞተ እንደ ሆነ እንዲሁ ደግሞ ከሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው።” ያእቆብ 2:14_26
በስተመጨረሻ መናገር የምፈልገው በሐይማኖታዊ የንግስ ጉዞ እና የቤተክርስትያን የአዳር ፕሮግራም ( እንደ ጥምቀትና ሌሎቹም ቤተክርስትያን ለንግስ በአል ተብሎ በሚታደርባቸው ግዜያቶች ) አብረውኝ ስንጓዝና ስናድር የነበሩ አብዛኛዎቹ ጓደኞቼ በሰራናቸው ጸያፍ የሀጢያት እርኩሰት ስራዎች ምክንያት አሁን በህይወት የሉም:: እኔ እራሴ ዛሬ ላይ ቆሜ ያሳለፍኩትን ጸያፍ የአመጻ የሀጢያት ህይወት ወደ ውኋላ ተመልሼ ሳስታውሰው አሁን ላይ ይዘገንነኛል:: መትረፌም ይደንቀኛል:: እንደ ጸያፍ የሀጢያት ስራዬና እንደ አመጻነቴ ብዛት ቢሆንማ ኖሮ ድሮ ገና በጠፋው ነበረ:: ድሮ ገና ጠፍቼ ሰጋዬ ወደ አፈር ተለውጦ አፈሩንም ንፋስ ወስዶት በተረሳው ነበረ:: ነገር ግን እንደ እግዚያብሔር ምህረት : ቸርነትና ፍቅር በዝቶልኝ የእግዚያብሔር ልጅ የናዝሬቱ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ መቃብሬን ከፍቶ ከሀጢያት ነጻ አወጣኝ ! የናዝሬቱ ጌታ ክርስቶስ ክርስቶስን ካገኘሁት ቡኋላ ሰው ሆኛለው ! የአምላኬ የአባቴ የኀያሉ የእግዚያብሔር ስም ከዘላለም እስከ ዘላለም የተበረከ ይሁን ! ዛሬ ከዘላለም ሞት ወደ ዘላለም ህይወት እንዲያው በጸጋው በእምነት ብቻ በሆነ ጽድቀት የናዝሬቱ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን በማመን ብቻ በእምነት ጸድቄያለሁ ! ይህንን ታላቅ ስራ ለዘላለም የሰራው ደግሞ የሰራዊት ጌታ እና አምላክ የሆነው ሀያሉ እግዚያብሔር በአንድያ ልጁ በናዝሬቱ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት ብቻ ነው !
DSC_7883
የእግዚአብሔርን ጽድቅ ሳያውቁ የራሳቸውንም ጽድቅ ሊያቆሙ ሲፈልጉ፥ ለእግዚአብሔር ጽድቅ አልተገዙም። የሚያምኑሁሉ ይጸድቁ ዘንድ ክርስቶስ የሕግ ፍጻሜ ነውና። ሙሴ ከሕግ የሆነውን ጽድቅ የሚያደርገው ሰው በእርሱ በሕይወትእንዲኖር ጽፎአልና። ከእምነት የሆነ ጽድቅ ግን እንዲህ ይላል። በልብህ። ማን ወደ ሰማይ ይወጣል? አትበል፤ ይህ ክርስቶስንለማውረድ ነው፤ ወይም። በልብህ። ወደ ጥልቁ ማን ይወርዳልአትበል፤ ይህ ክርስቶስን ከሙታን ለማውጣት ነው። ነገርግን ምን ይላል? በአፍህ በልብህም ሆኖ ቃሉ ቀርቦልሃል፤ ይህም የምንሰብከው የእምነት ቃል ነው። ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነበአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤ ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልናበአፉም መስክሮ ይድናልና። መጽሐፍ። በእርሱ የሚያምን ሁሉ አያፍርም ይላልና። በአይሁዳዊና በግሪክ ሰው መካከልልዩነት የለምና፤ አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና፥ ለሚጠሩትም ሁሉ ባለ ጠጋ ነው፤ የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናልና።እንግዲህ ያላመኑበትን እንዴት አድርገው ይጠሩታል? ባልሰሙትስ እንዴት ያምናሉ? ያለ ሰባኪስ እንዴት ይሰማሉ?መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ ናቸው ተብሎ እንደ ተጻፈ ካልተላኩ እንዴት ይሰብካሉ? ነገርግን ሁሉ ለምሥራቹ ቃል አልታዘዙም። ኢሳይያስ። ጌታ ሆይ፥ ምስክርነታችንን ማን አመነ? ብሎአልና። እንግዲያስ እምነትከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው።” ሮሜ 10
ሙሴም በምድረ በዳ እባብን እንደ ሰቀለ እንዲሁ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋየሰው ልጅ ይሰቀል ይገባዋል። በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔርአንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ፥ በዓለም እንዲፈርድእግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውምና። በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም፤ በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል። ብርሃንም ወደ ዓለም ስለ መጣ ሰዎችም ሥራቸው ክፉ ነበርና ከብርሃን ይልቅ ጨለማንስለ ወደዱ ፍርዱ ይህ ነው። ክፉ የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላልና፥ ሥራውም እንዳይገለጥ ወደ ብርሃን አይመጣም፤እውነትን የሚያደርግ ግን ሥራው በእግዚአብሔር ተደርጎ እንደ ሆነ ይገለጥ ዘንድ ወደ ብርሃን ይመጣል።” ዮሐ 1_21
የሕግን ሥራ በመሥራት ሥጋ የለበሰ ሁሉ በእርሱ ፊት ስለማይጸድቅ ነው፤ ኃጢአት በሕግ ይታወቃልና። አሁን ግን በሕግናበነቢያት የተመሰከረለት የእግዚአብሔር ጽድቅ ያለ ሕግ ተገልጦአል፥ እርሱም፥ ለሚያምኑ ሁሉ የሆነ፥ በኢየሱስ ክርስቶስበማመን የሚገኘው የእግዚአብሔር ጽድቅ ነው፤ ልዩነት የለምና፤ ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብርጎድሎአቸዋል፤ በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ። እርሱንም እግዚአብሔርበእምነት የሚገኝ በደሙም የሆነ ማስተስሪያ አድርጎ አቆመው፤ ይህም በፊት የተደረገውን ኃጢአት በእግዚአብሔር ችሎታስለ መተው ጽድቁን ያሳይ ዘንድ ነው፥ ራሱም ጻድቅ እንዲሆን በኢየሱስም የሚያምነውን እንዲያጸድቅ አሁን በዚህ ዘመንጽድቁን ያሳይ ዘንድ ነው። ትምክህት እንግዲህ ወዴት ነው? እርሱ ቀርቶአል። በየትኛው ሕግ ነው? በሥራ ሕግ ነውን?አይደለም፥ በእምነት ሕግ ነው እንጂ። ሰው ያለ ሕግ ሥራ በእምነት እንዲጸድቅ እንቆጥራለንና።” ሮሜ 3
fatima_portugal_17
ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እንዲጸድቅ እንጂ በሕግ ሥራ እንዳይሆን አውቀን፥ ሥጋን የለበሰ ሁሉ በሕግ ሥራስለማይጸድቅ፥ እኛ ራሳችን በሕግ ሥራ ሳይሆን በክርስቶስ እምነት እንጸድቅ ዘንድ በክርስቶስ ኢየሱስ አምነናል። ነገር ግንበክርስቶስ ልንጸድቅ የምንፈልግ ስንሆን ራሳችን ደግሞ ኃጢአተኞች ሆነን ከተገኘን፥ እንግዲያስ ክርስቶስ የኃጢአት አገልጋይነዋ? አይደለም። ያፈረስሁትን ይህን እንደ ገና የማንጽ ከሆንሁ ራሴ ሕግ ተላላፊ እንድሆን አስረዳለሁና። እኔ ለእግዚአብሔርሕያው ሆኜ እኖር ዘንድ በሕግ በኩል ለሕግ ሞቼ ነበርና። ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ፤ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርምክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል፤ አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለእምነት የምኖረው ነው። የእግዚአብሔርን ጸጋ አልጥልም፤ ጽድቅስ በሕግ በኩል ከሆነ እንኪያስ ክርስቶስ በከንቱ ሞተ።”     ገላ 2:16_21
ክርስቶስንም አገኝ ዘንድ፥ በክርስቶስም በማመን ያለው ጽድቅ ማለት በእምነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ያለው ጽድቅ እንጂከሕግ ለእኔ ያለው ጽድቅ ሳይሆንልኝ፥ በእርሱ እገኝ ዘንድ ሁሉን እንደ ጕድፍ እቈጥራለሁ::” ፊል 3:9
“ስለዚህ እያዩ ስለማያዩ እየሰሙም ስለማይሰሙ ስለማያስተውሉም በምሳሌ እነግራቸዋለሁ። መስማት ትሰማላችሁናአታስተውሉም፥ ማየትም ታያላችሁና አትመለከቱም። በዓይናቸው እንዳያዩ፥ በጆሮአቸውም እንዳይሰሙ፥ በልባቸውምእንዳያስተውሉ፥ ተመልሰውም እንዳልፈውሳቸው፥ የዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኖአልና ጆሮአቸውም ደንቁሮአል ዓይናቸውንምጨፍነዋል የሚል የኢሳይያስ ትንቢት በእነርሱ ይፈጸማል።” ማቴ 13:13_15
photos-christian-jerusalem-2010-11-15-0006
እናንተ ግብዞች፥ ኢሳይያስ ስለ እናንተ። ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል፥ ልቡ ግን ከእኔ በጣም የራቀ ነው፤ የሰውምሥርዓት የሆነ ትምህርት እያስተማሩ በከንቱ ያመልኩኛል ብሎ በእውነት ትንቢት ተናገረ።” ማቴ15:7_9

1 comment:

  1. የመድኃኒት ንግድ ሥራዬን ለማስፋፋት በተጠቀምኩበት ብድር ለመርዳት ሚስተር ቤንጃን ከሚያስፈልጓቸው በላይ አልፈዋል ፡፡
    እነሱ ለመስራት ወዳጃዊ ፣ ባለሙያ እና ፍጹም ዕንቁዎች ነበሩ ፡፡ እኔ ለማነጋገር ብድር የሚፈልግን ማንኛውንም ሰው እመክራለሁ ፡፡ Lfdsloans@outlook.com.WhatsApp ... +19893943740.

    ReplyDelete